2 months ago
የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ጋር የሐዋሳን ከተማ ልማት ፕሮጀክት ለማፋጠን ያለመ ስትራቴጂካዊ ውይይት አደረጉ!
በዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ፍሬሕይወት ታምሩ የተመራው የኩባንያችን ከፍተኛ ማኔጅመንት ቡድን፣ ከሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ እና ከከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በከተማዋ እያስመዘገበችው የሚገኘውን ፈጣን የዲጂታል ዕድገት እንዲሁም የመጻኢ የቴክኖሎጂ ትስስርን ለማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ስትራቴጂካዊ ውይይት አካሂዷል።
ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ኩባንያችን እያከናወናቸው የሚገኙ መጠነ ሰፊ የሪፎርም ሥራዎችን በማድነቅ፤ በተለይም የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በማፋጠን ረገድ ኢትዮ ቴሌኮም እያበረከተ ለሚገኘው ቁልፍ ሚና እውቅና ሰጥተዋል፡፡
ክቡር ከንቲባው ቀደም ሲል በከተማዋ ለተከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች ኩባንያችን ላደረገው ሁለገብ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው፤ ሐዋሳ ከአዲስ አበባ በመቀጠል ዋነኛ የቱሪዝም እና የኮንፈረንስ መዳረሻ እንድትሆን ለማስቻል ያለመ አዲስ የሐዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ውጥን ይፋ ማድረጋቸውን ገልጸዋል። በመሆኑም በመካሄድ ላይ ያለውን የ"ስማርት ሲቲ" ፕሮጀክት እና የሐዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ለማፋጠን የኢትዮ ቴሌኮም ድጋፍ ቀጣይነት እንዲኖረው ጠይቀዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በበኩላቸው፤ ኩባንያችን መሰል የከተማ ልማት ውጥኖችን ለመደገፍ ያለውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል። ሐዋሳ በፋይበር መሰረተ ልማት እንዲሁም በ4ጂ እና በ5ጂ የሞባይል ቴክኖሎጂ የታጠቀች ከተማ መሆኗን ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅት አስተማማኝ የሆነ የኔትወርክ ሽፋን እና ጥራትን ማሳደግ ታሳቢ ያደረግ መጠነ ሰፊ የማስፋፋት እና የማዘመን ሥራ በተጠናከረ ሁኔታ በመካሄድ ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የከተማ አስተዳደሩን አገልግሎት በዲጂታል ቴክኖሎጂና በቴሌብር በማዘመን፣ የሥራ ቅልጥፍናንና የገቢ አሰባሰብን ማሳደግ እንደሚቻል ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ገልጸዋል። በተመሳሳይ፣ በዘመን ገበያ አማካኝነት ለነጋዴዎች የገበያ ትስስርን በማስፋፋት ረገድ ሰፊ የዲጂታላይዜሽን ዕድሎችና የሥራ ፈጠራ አጋጣሚዎች መኖራቸውን አስገንዝበዋል።
ሐዋሳን ንፁህ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና በዲጂታል የታገዘ የሕዝብ መዳረሻ ለማድረግ እንዲሁም የተቀናጀ የዲጂታል ሥነ-ምህዳርን ለመፍጠር ያለመ ሰፊ ስትራቴጂካዊ ውይይት ተደርጓል። በዚሁ መሠረት የኩባንያችንን አቅም በመጠቀም የሐዋሳ "ስማርት ሲቲ" ልማትን ለማፋጠን፣ የቴሌብር አገልግሎቶችን በሙሉ አቅም ማቀናጀት፣ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ማድረግ፣ የትራፊክ እና የሞቢሊቲ መፍትሔዎች፣ የመሠረተ ልማት ጥበቃ እንዲሁም የኔትወርክ ዝርጋታን የሚያቀላጥፉ የኮሪደር ልማት ትብብሮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል።
በመጨረሻም፣ የኩባንያችን ማኔጅመንት ለሐዋሳ ከተማ ዕድገትና ለአዲሱ የሐዋሳ ሐይቅ ልማት ፕሮጀክት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት ያረጋገጠ ሲሆን፤ ይህም ኢትዮጵያን በቴክኖሎጂ የማብቃትና ዲጂታል መጻኢን የመገንባት ትልቅ ራዕያችን አካል መሆኑ ተመላክቷል።
#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ !
#ethiotelecom #telebirr #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia #smartcity #hawassa #digitalethiopia

ከተማ ሲቀየር አኗኗርም ይቀየራል
***********
በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች እየተከናወነ ያለው የመሰረተ ልማት ግንባታ ሥራ የከተሞችን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ፣ ነዋሪዎችን ከዘመናዊ አኗኗር ጋር እያስተሳሰረ ይገኛል።
ከተሞች በግንባታ ውበት ብቻ ሳይሆን በ5ጂ ቴክኖሎጂ የታገዘ የስማርት ሲቲ አገልግሎትን በማስፋፋት ዘመናዊ የደህንነት ሥርዓት እንዲሁም የተቀናጀ የፍሳሽ አገልግሎት ባለቤት እየሆኑ ነው።
ለሕፃናት መጫወቻና ለመዝናኛ አገልግሎት የተገነቡ ስፍራዎችም ለትውልድ የሚተርፍ ታላቅ ዐሻራ እያሳረፉ ይገኛሉ።
ይህ ዘመናዊነት ምቹ የእግረኛ መንገዶችንና አረንጓዴ ስፍራዎችን ያጠቃለለ በመሆኑ፣ ነዋሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዲያደርጉና ንጹሕ አየር እንዲያገኙ በማስቻል ከፍተኛ የጤና ጥቅም እየሰጠ ይገኛል።
የከተሞች መዘመን የአእምሮ እርካታንና አካላዊ ጤንነትን በመጠበቅ የዜጎችን የኑሮ ጥራት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል።
ይህንን ዘመናዊነት በማሳደግና በተለያዩ አካባቢዎችም በማስፋፋት ለትውልድ የሚበጅ ታላቅ ዐሻራ ማኖር ይገባል።
#ethiopianbroadcastingcorporation #ethiopia #cities #development

በተግባር የተገለጠው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል - አዲስ አበባን የማዘመን ጉዞ ስኬት
**********************
ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "የዛሬ አምስት ዓመት አዲስ አበባ በአፍሪካ ውስጥ እጅግ ውብ ከሚባሉ ከተሞች አንዷ ትሆናለች" ሲሉ ተናግረው ነበር።
ያኔ ንግግራቸውን ከሰሙት መካከል የመዲናዋን የዛሬ ገጽታ በዐይነ ኅሊናቸው የሣሉት ጥቂቶች ነበሩ።
በወቅቱ ንግግሩ ከተራ የፖለቲካ ተስፋ በላይ ትርጉም አይኖረውም ብለው የተጠራጠሩ ቢኖሩም፣ ዛሬ ግን አዲስ አበባ በአጭር ጊዜ ውስጥ እጅግ ማራኪ፣ ጽዱ እና ዘመናዊ ዲፕሎማሲያዊ ማዕከል በመሆን ራዕዩን በተግባር አሳይታለች።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመዲናዋ ተበታትነው የሚገኙትን እምቅ አቅሞች ወይም "ያልተያያዙ ትላልቅ ዶቶችን" በማገናኘት ከተማዋን በአዲስ መልክ የመገንባት ዕቅድ እንዳላቸው አስረድተውም ነበር።
ይህ አርቆ አሳቢ የከተማ ልማት ፍልስፍና ታሪካዊ ክስተቶችን የሚያስታውስ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳስታወሱት፣ ንጉሥ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን መገንባት በጀመሩበት ወቅት "ድንጋይ መቆርቆር የስንፍና ምልክት ነው" በማለት ያሾፉባቸው ነበሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈጣሪዎች እና አልሚዎች ሁልጊዜም በዘመናቸው ካሉ "አውርቶ አደር" ተቺዎች ጋር መጋፈጣቸው አይቀርም የሚል እሳቤ አላቸው።
ዛሬ በኮሪደር ልማቱ እየታየ ያለውም ይኸው እውነታ ነው፤ "እኛ የምንሠራው ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነገ እና ለቀጣዩ ትውልድ ነው፤ ነገ የሚፈርስ ዳስ አንሠራም" በሚለው መርሐቸው ለትውልድ የሚሻገር ዘላቂ ሥራ እየተሠራ ይገኛል።
"የመደመር መንግሥት" መጽሐፍ ላይ እንደተብራራው፣ ከተሜነት የብልጽግና መዳረሻ እና የኢኮኖሚ ሞተር ነው።
ከተማን ማዘመን ረጃጅም ሕንፃዎችን ከመገንባት ባለፈ ሰፊ የእግረኛ እና የሳይክል መንገዶችን፣ አረንጓዴ ስፍራዎችን እና ምቹ መሠረተ ልማቶችን ማካተትን ይጠይቃል።
አዲስ አበባ ላይ በተግባር ሥራ ላይ ውሎ አዲስ አበባን ምርጥ የአፍሪካ ከተማ ያደረገው ይኸው ሰዎችን ማዕከል ያደረገው ፍልስፍና ነው።
ከዚህ ቀደም የተገነቡት አንድነት ፓርክ፣ እንጦጦ ፓርክ፣ ወዳጅነት አደባባይ እና የዓድዋ ድል መታሰቢያ የዚህ ዘመናዊ አስተሳሰብ ማሳያዎች ናቸው።
በዚህም የኮሪደር ልማቱ በግንባታው ሂደት ለበርካታ ዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ፣ የካርቦን ልቀትን በመቀነስ የነዋሪዎችን ጤና እና ደኅንነት የሚጠብቅ ንፁህ አካባቢን መፍጠር ችሏል።
እነዚህ ስልታዊ ለውጦች አዲስ አበባን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለበርካታ ሽልማቶች አብቅተዋታል።
በ2015 ዓ.ም በናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ ስማርት ሲቲዎች ኢንቨስትመንት ጉባኤ ላይ 36 የአፍሪካ ከተሞችን በመብለጥ ‘የዓመቱ ምርጥ ስማርት ሲቲ' ሽልማትን አሸንፋለች።
እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ አዳራሽ (Historic Africa Hall) እድሳት ፕሮጀክት የሞደርኒዝም ጥበቃ ሽልማትን (World Monuments Fund/Knoll Modernism Prize) ተቀዳጅቷል።
ይህ ሽልማት ከተመሠረተበት እ.ኤ.አ. 2008 ጀምሮ በአፍሪካ አህጉር ሲሰጥ አዲስ አበባ የመጀመሪያዋ ነች።
እነዚህ ስኬቶች ከተማዋ እ.አ.አ በ2027 የዓለም አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን (COP32) እንድታስተናግድ ትልቅ መተማመኛ ፈጥረዋል።
በአዲስ አበባ የተመዘገበው ይህ ስኬታማ የከተማ ማዘመን ልምድ በአሁኑ ወቅት ከ70 በላይ ወደሚሆኑ የሀገራችን ከተሞችም እንዲስፋፋ ተደርጓል።
ይህ አዲስ የከተማ ማሻሻያ ፍልስፍና በቱሪዝም ዘርፉ ላይም ታይቶ የማይታወቅ መነቃቃት ፈጥሯል።
በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ወራት ብቻ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ከሚሆኑ የውጭ ቱሪስቶች ከ2.6 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል።
በተባበሩት መንግሥታት የቱሪዝም ድርጅት (UN Tourism) መረጃ መሰረትም ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2025 የዓለም አቀፍ ቱሪስቶችን ፍሰት በ15 በመቶ በማሳደግ ፈጣን ዕድገት እያስመዘገቡ ካሉ የቱሪዝም መዳረሻዎች ተርታ ተሰልፋለች።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይህን ግዙፍ ልማት ሲያከናውን ያጋጠሙትን ማኅበራዊ እና ሕጋዊ ተግዳሮቶች ሰብአዊነትን በተላበሰ መንገድ ለመፍታት ያደረገው ጥረት የልማቱን ፍትሐዊነት ያረጋግጣል።
ከተማዋን ለሕፃናት፣ ለወጣቶች እና ለአካል ጉዳተኞች ጭምር ምቹ በማድረግ የቦታ ፍትሐዊነትን ማረጋገጥ ተችሏል።
ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም የተነገረው ራዕይ ዛሬ እውን ሆኖ፣ አዲስ አበባ በምድረ አፍሪካ ውብ፣ ተመራጭ እና የሁሉንም ነዋሪዎቿን ፍላጎት ያማከለች መዲና መሆኗን በተግባር እያረጋገጠች ትገኛለች።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #addisababa #corridordevelopment #smartcity

5 months ago
የመንግሥት አገልግሎት ወደ ደጃፍዎ ሊመጣ ነው
#ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ወደ መንግሥት ቢሮዎች በመሄድ ፈንታ፣ ቢሮዎቹ ወደ ነዋሪው መንደር የሚመጡበት "ተንቀሳቃሽ የመሶብ አገልግሎት" ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ሥራ እንደሚጀምር ተበሰረ።
የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ እንደገለጹት፣ በቀጣዮቹ ከ20 እስከ 25 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ አገልግሎቱ በይፋ ይጀመራል።
የተንቀሳቃሽ አገልግሎቱ ዋና ዋና ገጽታዎች
ይህ አዲስ አሠራር በዋናነት የሚከተሉትን አገልግሎቶችና ዝግጅቶች ያካተተ ነው፦
* ዘመናዊ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች፦ ለአገልግሎቱ የሚውሉ ትላልቅ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች የተዘጋጁ ሲሆን፣ በውስጣቸውም ልክ እንደ መደበኛ ቢሮ የተሟላ ቁሳቁስና የዲጂታል መሠረተ ልማት ተገጥሞላቸዋል።
* ሁሉንም አካታች የሆነ አገልግሎት፦ በተለይም ለአረጋውያን፣ ለአካል ጉዳተኞችና በተለያዩ ምክንያቶች ከቤት መውጣት ለማይችሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎቱን በቅርበት ለማግኘት ያስችላቸዋል።
* ተደራሽነት፦ አገልግሎቱ በአንድ ቋሚ ቢሮ ብቻ ሳይወሰን በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች እየተንቀሳቀሰ በርካታ የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል ይሰጣል።
ከራዕይ ወደ ተግባር
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቀደም ሲል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የመሶብ አገልግሎት ተደራሽነቱ ሰፍቶ በተንቀሳቃሽ ቢሮዎች ጭምር መሰጠት እንዳለበት አሳስበው ነበር። አሁን ይፋ የተደረገው ዝግጅትም ይህንኑ የዲጂታል ኢትዮጵያ ራዕይ መሬት ለማውረድ የታለመ መሆኑ ተገልጿል።
አውቶቡሶቹ በአሁኑ ወቅት የዲዛይንና የመካኒካል ማስተካከያ ሥራቸውን አጠናቅቀው ወደ ተግባር ለመግባት የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ይገኛሉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #amn #አዲስ_አበባ #አዲስ_መሶብ #ዲጂታል_አገልግሎት #ስማርት_ሲቲ #ኢትዮጵያ #smartaddis #digitalgovernance

6 months ago
የአፍሪካ መዲና በላብራቶሪ መነጽር፦ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናት የነዋሪውን እንግልት ይፈታዋል?
የከተማዋ ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት ከሀገሪቱ አንጋፋ የጥናት ተቋም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በ2018 በጀት ዓመት የሚጠናቀቁ ሁለት ግዙፍ ስልታዊ ጥናቶችን ለማካሄድ ተፈራርሟል።
ስምምነቱ "Building Urban Resilience" (የከተማ መቋቋም አቅምን መገንባት) እና "Counting Every Life" (ዲጂታል የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ) በሚሉ መጠሪያዎች የቀረቡ ናቸው።
ነገር ግን ጥያቄው፦ ይህ ስምምነት የከተማዋን ነዋሪ ሕይወት በእርግጥ ይለውጠዋል ወይንስ ሌላ የቢሮክራሲ ሰነድ ሆኖ በመደርደሪያዎች ላይ ይከመራል? ይህ ዘገባ የዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን፣ የምሁራን የሰላ ትችቶችን እና የወደፊት ስጋቶችን በጥልቀት ይፈትሻል።
1. የአደጋ ስጋት መከላከል፡ ከ"እሳት አጥፊነት" ወደ "አደጋ መከላከል"
አዲስ አበባ በየዓመቱ በአማካይ ከሺ በላይ ድንገተኛ አደጋዎች (በተለይም የእሳት ቃጠሎ) ያስተናግዳል። እነዚህ አደጋዎች የሚከሰቱት ደግሞ በአብዛኛው መሠረተ ልማት ባልተሟላላቸው፣ የቤት አሰራራቸው ለቃጠሎ በሚያመቹ እና የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓታቸው ባልተስተካከለ ሰፈሮች ነው።
🌍 የዓለም ተሞክሮ፦ የቶኪዮ እና የሜክሲኮ ሲቲ ትምህርት
እንደ ቶኪዮ ያሉ ከተሞች አደጋ ከመከሰቱ በፊት "Micro-Zoning" የተባለ ስልት ይጠቀማሉ። ይህም እያንዳንዱ ወረዳ የራሱ የሆነ የአደጋ ስጋት ካርታ (Hazard Map) እንዲኖረው ያደርጋል። አዲስ አበባ አሁን የጀመረችው ጥናት ይህንን በወረዳ ደረጃ ያለውን ስጋት የመለየት ስራ የሚያከናውን ከሆነ፣ ግዙፍ እመርታ ነው። ነገር ግን እንደ ሜክሲኮ ሲቲ ሁሉ፣ ጥናቱ በወረቀት ላይ ብቻ ቢሰፍርና በቂ በጀት ካልተመደበለት፣ አደጋው ሲመጣ መከላከል አይቻልም።
🎓 የምሁራን እይታ፦
የከተማ ፕላን ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ አዲስ አበባ "Reactive" (አደጋ ሲመጣ የምትደነግጥ) ከተማ ነች። "ጥናቱ በወረዳ ደረጃ መውረዱ መልካም ነው፤ ነገር ግን ወረዳዎች አደጋን ለመከላከል የሚያስችል ራሱን የቻለ ስልጣንና በጀት የላቸውም። ጥናቱ ይህንን መዋቅራዊ ለውጥ ካላመጣ፣ ሰነዱ ብቻውን ህንፃዎችን ከአደጋ አይታደግም" ይላሉ።
2. ዲጂታል ማንነት፡ የቢሮክራሲው ሞት ወይንስ አዲስ መልክ?
ሁለተኛው ጥናት "Counting Every Life, Securing Every Right" የሚል ሲሆን፣ ዓላማው የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባን (ልደት፣ ጋብቻ፣ ሞት) ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ ማድረግ ነው። በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ አንድ ነዋሪ የልደት ምስክር ወረቀት ለማውጣት ቢያንስ ከ3-5 ቀናት እንግልትና በወረቀት የተሞላ ፋይል ይገጥመዋል።
🌍 የዓለም ተሞክሮ፦ የኢስቶኒያ ተአምር
ኢስቶኒያ 99% የመንግስት አገልግሎቶችን በዲጂታል ትሰጣለች። አንድ ዜጋ በህይወቱ ወረቀት የሚፈርመው ሲጋባ እና ቤት ሲገዛ ብቻ ነው። አዲስ አበባ ይህንን ልምድ ለመቅሰም የጀመረችው ጥናት፣ ዜጎች ከወረዳ ወረዳ መረጃ ፍለጋ እንዳይመላለሱ የሚያደርግ "Interoperable" (ተሳሳቢ) ዳታቤዝ መፍጠር ይኖርበታል።
ዲጂታላይዜሽን ማለት "የወረቀት ፎርምን ወደ ኮምፒውተር መተየብ" ማለት አይደለም። አሰራሩን (Process) መቀየር ማለት ነው። ምሁራን እንደሚጠቁሙት፣ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያለው "የመረጃ ምስጢራዊነት አባዜ" እና የተቋማት መረጃን አለማጋራት (Data Silos) ለጥናቱ ትግበራ ትልቅ እንቅፋት ናቸው። በተጨማሪም፣ 80% የሚሆነው የከተማዋ ነዋሪ የዲጂታል እውቀት (Digital Literacy) በሌለበት ሁኔታ፣ ሲስተሙ ለጥቂቶች ብቻ እንዳይሆን ያሰጋል።
3. የጥናት አባዜ እና የትግበራ ድርቅ (Implementation Gap)
ኢትዮጵያ ውስጥ በየዓመቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጥናቶች በከፍተኛ በጀት ይከናወናሉ። ይሁን እንጂ ብዙዎቹ ጥናቶች "የፖለቲካ ፍጆታ" ተደርገው ይወሰዳሉ።
የዳታ ጥራት ስጋት፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናቱን ሲያደርግ የሚጠቀመው መረጃ ከወረዳዎች የሚሰጠውን ነው። ወረዳዎች ደግሞ ሪፖርታቸውን "ለማሳመር" ሲሉ የተጋነነ ወይም የተሳሳተ መረጃ የመስጠት ዝንባሌ አላቸው። "Garbage in, Garbage out" እንደሚባለው፣ መነሻው የተሳሳተ ዳታ ከሆነ፣ የጥናቱ ውጤትም የተሳሳተ ይሆናል።
የሰው ኃይል ዝግጁነት፦ ዘመናዊ ሲስተም ቢገነባም፣ ያንን ሲስተም የሚረከበው የመንግስት ሰራተኛ በአሮጌው የቢሮክራሲ አስተሳሰብ የተተበተበ ከሆነ፣ ለውጥ ማምጣት አይቻልም። ቴክኖሎጂው ሳይሆን "አስተሳሰቡ" (Mindset) ይቀድማል።
4. የወደፊት ዕጣ-ፈንታ፦ ምን መደረግ አለበት?
ይህ ስምምነት ታሪካዊ ሊባል የሚችለው የሚከተሉት ነጥቦች ሲሟሉ ብቻ ነው፡
ግልጽነትና ተጠያቂነት፦ ጥናቱ በየደረጃው ያለውን ግስጋሴ ለህዝብ ይፋ ማድረግ አለበት። በ2018 መጨረሻ ምን ተሳካ? ምን ቀረ? የሚለው በግልጽ መታወቅ ይኖርበታል።
የግል ዘርፉ ተሳትፎ፦ መንግስትና ዩኒቨርሲቲ ብቻቸውን ከተማዋን ሊቀይሩ አይችሉም። የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች (Startups) በዲጂታላይዜሽን ሂደቱ ውስጥ የራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱ መፈቀድ አለበት።
የዜጎች ዳታ ደህንነት፦ የነዋሪዎች የግል መረጃ (Privacy) በህግ መጠበቅ አለበት። መረጃው ለክትትል ሳይሆን ለአገልግሎት መሆኑን ህዝቡ ካላመነበት፣ ለዲጂታል ምዝገባው ያለው ትብብር ዝቅተኛ ይሆናል።
ማጠቃለያ
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ለከተማዋ "የተስፋ ጭላንጭል" ነው። ነገር ግን ይህ ጭላንጭል ወደ ደማቅ ብርሃን የሚቀየረው በጥናቱ ውጤት ሳይሆን በጥናቱ ተፈጻሚነት ነው።
ከተማዋ በወረቀት ላይ ሳይሆን በመሬት ላይ፣ በሪፖርት ሳይሆን በነዋሪው እርካታ መመዘን አለባት። አዲስ አበባ በ2018 "ስማርት ሲቲ" (Smart City) ለመሆን የመጀመሪያውን እርምጃ ትረምዳለች ወይንስ በቢሮክራሲው አዙሪት ውስጥ ትቀጥላለች? መልሱ የሚገኘው ከጥናቱ መጠናቀቅ በኋላ በሚወሰዱት ደፋር የፖሊሲ እርምጃዎች ላይ ነው።

Sponsored by
Surafel
9 months ago
አዲስ አበባ ... ከውበትም በላይ!
#ethiopia | የአፍሪካ ከተሞች በቅኝ ግዛት ዘመን ተቀይረዋል። በተለይ ፍራንኮፎን የሚባሉ ሀገራት ከተሞች አገር በቀል ቅርጾች ተቀይረው የተውሶ ካባ እንዲለብሱ ተደርጓል። ፈረንሳይ አይቮሪኮስትን ቅኝ ይዛ በነበረችበት ግዜ፣ ዋና ከተማዋ አቢጃንን የ”አፍሪካዋ ፓሪስ” ስትል ታቆላምጣት ማቆላመጥዋ፣ ዶሮን ሲያታልሏት... አይነት መሆኑ ገፅታው ዛሬም ድረስ አፍ አውጥቶ ይናገራል። ቅርፅና ገፅታው ባሻገር ሆን ተብሎ በከተሞቹ የተሰሩ አድሏዊነት የፈጠሩት ልዩነቶች ከተሞቹን ለወንጀል አጋልጧቸዋል።
መዲናችን አዲስ አበባ ከሌሎች እህት ከተሞች የሚለያት ከቅኝ ገዢዎች ንክኪ የፀዳች መሆንዋ ብቻ አይደለም። ዛሬ ሌላ ልዩነት መፍጠርዋን ከራሳቸው ከአፍሪካውያን አንደበት መስማት ጀምረናል።
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች በነፃነት እየተራመዱ፣ ስለደህንነቷ፣ ንፅህናዋ እና ደማቅ ድባብ አድንቀው መናገራቸው አንዱ ማመሳከሪያ ይሆናል። የ”ስማርት ሲቲ” ቴክኖሎጂን የተላበሰች ከተማችንን ለመጎብኘት እድል ያገኙት የኬንያ፣ የአልጄሪያ እና የዛምቢያ መሪዎች የአዲስ አበባን ጉልህ ለውጥ፣ ደማቅ ድባብ ከመመስከርም ባለፈ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አርአያ መሆንዋን ተናግረዋል።
አዲስ አበባ ዛሬ ከምን ጊዜውም በላይ የአለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ኮንፈረንሶች የስበት ማእከል መሆንዋ በራሱ አንዱ የስኬት ቁልፍ ነው። በዓለም ላይ ካሉ ተወዳጅና ተመራጭ ከተሞች ተርታ ለመሰለፍ የበቃችበት ምስጢር ስሟን የሚመጥን የእድገት እርከን ላይ መድረሷ መሆኑን ላፍታም አንዘነጋውም። ፀጥታዋ አስተማማኝ፣ ገፅታዋም ፍፁም ማራኪ ሆኗል። ለውጡ “ተአምር” ያስብላል። የምእራባውያን ከተሞች ምእተ አመት የፈጀባቸው ለውጥ፣ አምስት አመት ባልሞላው ግዜ በዚህ ልክ መታደስዋ ያስደምማል። የቆሸሹ ወንዞች ለአይን ማራኪ ታክመዋል፣ የወዳደቁ ቤቶች ተቃንተዋል፣ የፈራረሱ ህንፃዎች ተጠግነዋል፣ የቆረቆዙ መንገዶች ዛሬ ቀን ወጥቶላቸዋል።
ከአድዋ መታሰቢያ እስከ ኮንቬንሽን ማእከል፣ ከአዋሬ እስከ ገላን፣ ከካዛንቺዝ እስከ እንጦጦ .... ፅዳትን፣ ውበትን፣ ታሪክን፣ ኢኮኖሚን ልክ-በልክ እየሰፉ አሮጌ ወይን በአዲስ አቁማዳ ተሞልቶ ይታያል። ዛሬ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ሰው ከተሽከርካሪ ጋር ሲጋፋ አናይም።
መስመር ተለይቶለት፣ እግረኛው ንፁህ አየር እየተመገበ ይጓዛል፣ ሳይክሎች በነፃነት ይርመሰመሳሉ ፣ ህፃናት ስኩተር እያንከባለሉ ይቦርቃሉ....
በሰለጠነው አለም እየተመለከትን፣ በኋላ ቀርነታችን ያስቆጨን የነበረውን ታሪክ እንድንረሳው ሆኗል።
የከተማችን ማማር ሁሉም የሚጋራው ሕልም ቢሆንም በአጭር ግዜ እውን የመሆኑን ጉዞ ጊዜ ፈንቆል አደባባይ እስኪያወጣው ትጋትና ቁርጠኝነትን ይጠይቅ ነበር።
ህልሙ ከውበትም በላይ ነው። በአዲስ አበባችን የተሻሻለው መሠረተ ልማት ተረስተው የነበሩ እሴቶቻችንን በእጅጉ የማሳደጉን አቅም ፍንትው አድርጎ አሳይቷል፣ ከተማዋን አነቃቅቷል፣ የአገልግሎት ተደራሽነትን አሻሽሏል፣ የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን በከፍተኛ ፍጥነት አሳድጓል። መዲናችን ለነዋሪዎችዋ የተሟላ አገልግሎት እንድትሰጥ በመተግበር ላይ ያለችው አስተዳደርን ማቀላጠፍ፣ ሥራ አጥነትን መቀነስ፣ አረንጓዴ ልማትን ማስፋፋትና ቴክኖሎጂና ፈጠራን ማሳደግ አሌ የማይባል እመርታ ነው።
ሰዎች አካባቢያቸውን ይመስላሉ። አመለካከታቸውም የሚቀረፀው በአካባቢያቸው ሁኔታ ነው። በቆሸሸ ገፅታና ለኑሮ ምቹ ባልሆነ አካባቢ የሚኖር ህዝብ የፀዳ አመለካከት ሊኖረው አይችልም። ለዚህም ነው
ከተሞች አንዱ የሥልጣኔ መግለጫ የሚሆኑት። እንደ ፓሪስ እና ሲንጋፖር ያሉ ከተሞች ለህዝባቸው ብሄራዊ ኩራትና የቱሪዝም መስህብ የሆኑበት ምስጢር ይኸው ነው።
ውቢቷ አዲስ አበባ ዛሬ የዲፕሎማቶች መነሀሪያ ሆናለች። በርካታ አለምአቀፍ ስብሰባዎች፣ ኮንፈረንሶችና ወርክሾፖች እያስተናገደች ነው። የንግድ፣ የጤና እና የኢንቨስትመንት ተቋማት መወያያ መድረክ ልትሆን የበቃችበት ዋነኛው ምክንያት ኮሪደር ልማትን ጨክና መተግበርዋ መሆኑን ልብ ይሏል።
የከተማዋ እድገት በአፍሪካ ሳይሆን በዓለም ላይ ካሉ ከተሞች ተወዳዳሪ እንዳደረጋት የአፍሪካ መሪዎች ጭምር መስክረዋል። ለአይን ማራኪ እና በፀጥታው አስተማማኝ ከተማ መሆንዋ ተመራጭ አድርጓታል።
መዲናችን ዛሬም በማያቋርጥ የስኬት ጉዞ ላይ ናት። ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዳሉት፣ "ለዛሬዉ ትዉልድ ብቻ ሳይሆን ለቀሪዉ ትዉልድ የሚተላለፍ ዘመኑን የዋጀ ሁሉን አካታች የልማት ስራ እንካችሁ ብለናልና በተገቢዉ ልንጠቀምበት ይገባል፡፡”
በነዋሪው አንደበት

11 months ago
የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በአዲሱ ዓመት ይጀምራል ተባለ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ ፕላንና ልማት ቢሮ በአዲስ ዓመት መጀመሪያ ወራት “አዲስ መሶብ” የተባለ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንደሚጀምር አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ይህ ማዕከል የከተማዋን የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ለማቀላጠፍ ያለመ ነው።
ማዕከሉ ሥራ ለመጀመር እንዲችል የቢሮ ምደባ፣ መዋቅር ማጽደቅ፣ ሕጋዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀት እና የሰው ኃይል ማደራጀት ስራዎች እየተከናወኑ ነው። የከተማዋን የስማርት ሲቲ ግንባታ ለማጠናከር እና አገልግሎቶችን ዲጂታል ለማድረግም ጥረት እየተደረገ ነው።
በአጠቃላይ፣ የመንግስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት ምቹ የስራ ሁኔታ አፈጻጸም ሽፋን ከታቀደው 91.2 በመቶ ደርሷል ተብሏል። በተጨማሪም፣ 347 አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ እንዲደገፉ መደረጉም ተገልጿል።
Seledadotio

በአራት ወራቶች የተጠናቀቁት የጋር መኖሪያ ቤቶች በአዳማ
#ethiopia | በአዳማ ከተማ ጂ+5 27 ብሎክ የጋራ መኖርያ ቤቶች በዘመናዊ መልኩ በአራት ወራት ውስጥ ተገንብተው ተጠናቀው ተመርቀዋል።
በአዳማ ከተማ አንዶዴ መንደር ተገንብተው በዛሬው ዕለት የተመረቁት የጋራ መኖሪያ ቤት ሕንፃዎች በውስጣቸው 815 የመኖሪያ ክፍሎችን መያዛቸው የተገለፀ ሲሆን የሚ'ሰጡትም በልማት ምክንያት ከከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች ከመኖሪያቸው ለተነሱ ነዋሪዎች መሆኑ ተገልጿል።
አራት ወራትን እንደፈጀ በተገለጸው በዚሁ የግንባታ ሥራ ሂደት ከሦስት ሺ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር መ'ቻሉን የአዳማ ከተማ ከንቲባ ኃይሉ ጀልዴ ተናግረዋል።
ከተማዋን ወደ ስማርት ሲቲነት ለመለወጥ እየተሠራ መሆኑም በዚሁ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገለፀ ሲሆን የዛሬው የመኖሪያ መንደር ግንባታም የዚሁ ፕሮጀክት አንዱ አካል ነው ተብሏል።
ሷሊህ መሐመድ
ከአዳማ

1 year ago
አብረን እንሩጥ
አብረን እንለወጥ።
ይህ የአዲሱ ትውልድ ድምፅ ነው።
ድሬ በልጆቿ ከፍ እንዳለች
የስማርት ሲቲነት ግስጋሴዋን ቀጥላለች።
ወርሀ ነሀሴ በ 17/ 2017 ዓ.ም ከ10,000 በላይ ነዋሪዎች በድሬ ጎዳና ላይ ይሮጣሉ፤
ዲጂታል ድሬን እውን ያደረጋሉ።
አንድም ለጤናቸው
አንድም ለከተማቸው።
በድሬ ሱፐርአፕ ጉዳያችንን ሁሉ በስልካችን እንጨራርሳለን።
በቴክኖሎጂው ረገድ እንደሀገር ፈር ቀዳጅ እንሆናለን።
ድሬዳዋ የስልጣኔ ምድር ነበረች፤ አሁንም ነች፤ ወደፊትም የስልጣኔ ምድር ሆና ትቀጥላለች።
ሩጫው ላይ እንገናኝ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ኮሚሽን።

በአዲስ አበባ ቆሻሻን ወደ ሀብት በመቀየር ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ ተገኘ
#ethiopia | በአዲስ አበባ በ2017 በጀት ዓመት ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ሥራ ላይ የተሰማሩ 325 ማህበራት ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸውን፤ የአዲስ አበባ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ኃላፊ ሙላት ተገኝ ለኢቢሲ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ተናግረዋል።
በመዲናዋ የነዋሪው የቆሻሻ አወጋገድ ባህል በየጊዜው እየተሻሻለ ቢሆንም፤ አሁንም የሚቀሩ ተግባራት መኖራቸውንም ነው ኃላፊው የተናገሩት።
ቆሻሻን ለይቶ በማስወገድ ረገድ ከ200 ሺህ በላይ አባወራዎችን ተገቢውን ግንዛቤ እንዲጨብጡ ማድረግ መቻሉንም በቆይታቸው አንስተዋል።
አሁን እየተሰሩ ካሉ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ጋር የተናበበ ዘመናዊ የፅዳት አሰራር በመዘርጋት ላይ መሆኑንም ያነሱት አቶ ሙላት፥ የተጨማሪ የማፅጃ ማሽኖች ግዢ በ2018 ዓ/ም እንደሚፈፀም ተናግረዋል።
ከዛም ባለፈ ስማርት ሲቲ ለመሆን እየተጋች ላለችው አዲስ አበባ የሚመጥን ቀልጣፋ የፅዳት ስራ ለማከናወን፤ የግል አጋርነት በሙከራ ደረጃ በተመረጡ አካባቢዎች ተግባራዊ መደረጉን አመላክተዋል።
ከኤጀንሲው ባሻገር ነዋሪው ስልጡን የፅዳት ባህል ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዝ አቶ ሙላት ጥሪ አቅርበዋል። #ebc

Comments