4 months ago
ታሳ ታሳ ጋሞ
የሲሲአርዲኤ (CCRDA) አመታዊ ጉባኤ ተካሄደ
* ጋሞ በመሬት መንሸራተት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የአንድ ደቂቃ የሕሊና ጽሎት ተደርጎ ጉባኤው ተከፍቷልዠ
#ethiopia | የሲሲአርዲኤ (CCRDA) አባላት አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን አካሂደዋል።
በጉባኤው ላይ የድርጅቱ የጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ አቶ መላኩ ስብሀት እንደገለጹት፤ ስብሰባው ያለፈውን አመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለመገምገም እና ለማጽደቅ ያለመ ነው። ከዚህ ባለፈም በዘርፉ ያሉ ተግዳሮቶች ላይ ውይይት ተደርጓል።
በዋና ዋና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ያለው ተሳትፎ የሲቪክ ማህበራት በሃገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑ በጉባኤው ተመላክቷል።
በተለይም በሃገራዊ ምክክር ሂደት ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንዲሁም በምርጫ ወቅት መራጮችን በማስተማር ገለልተኛ ሚና ለመወጣት ይተጋል ተብሏል።
ሰብአዊ ድጋፍ እና ልማት🔎
ማህበራቱ በተጠናቀቀው አመት በበርካታ የልማት ስራዎች ላይ የተሳተፉ ሲሆን፣ በተለይም ከግጭት ጋር ተያይዞ ለተፈናቀሉ ወገኖች አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ በማቅረብ ረገድ ከፍተኛ ስራ ሰርተዋል። በጤና፣ በትምህርት እና በመልካም አስተዳደር ረገድም ማህበረሰብ ተኮር ስራዎች መከናወናቸው ተገልጿል።
የጋሞ አደጋ እና ቀጣይ እቅዶች🔎
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ – የሲቪል ማህበረሰብ አስተባባሪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማሞ ሞሊሶ በጋሞ ዞን ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ጋጮባባ፣ ከምባ ዙሪያ ወረዳ፣ አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ፣ አርባምንጭ ከተማ፣ ቦንኬ ወረዳ፣ ጨንቻ፣ ገረሴ ዙሪያ እና ገረሴ ከተማ በጎርፍ፣ በናዳ እና አውሎ ንፋስ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰብአዊ እና የንብረት ጉዳት ማድረሱን አብራርተዋል፡፡
አደጋው ጋጮባባ ፣ ከምባ ዙሪያ ወረዳ ፣ አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፣አርባምንጭ ከተማ ፣ ቦንኬ ወረዳ ፣ጨንቻ ፣ ገረሴ ዙሪያ ምእራብ አባያ እና ገረሴ ከተማ ላይ የደረሰ ሲሆን የጉዳቱ መንስኤም በጎርፍ ፣ በናዳ እና አውሎ ንፋስ ሰፊ ሞትና የንብረት ጉዳት ደርሷል ፡፡
በዚህም በአደጋ አባወራ 2644 እማወራ 376 በድምሩ 302ዐ እና ወንድ 8261 ሴት 10310 በድምሩ 18571 ቤተሰብ አባላት ተፈናቅለዋል፡፡
አደጋው በደረሰባቸው ወረዳዎች በተከሰተው አደጋ 1271 ሄር በላይ የሙዝ ፣ የሰብል ጉዳት ደርሷል ፤ 1100 የመኖሪያ ቤቶች የወደሙ ሲሆን በተያያዘም በአርባ ምንጭ ከተማ የኩልፎ ወንዝ በመሙላት ተፈጥሮአዊ አቅጣጫውን ለቆ በመሄድ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ 31 በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ ማህበራት፣ 2 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችና 1 የግብረ ሰናይ ድርጅት ንብረት ወድሟል አቶ ማሞ አስረድተዋል።
አያይዘውም በዞኑ አደጋ በደረሰባቸው ወረዳዎች ከ 125 በላይ ከፍተኛ ሞት የተመዘገበበት ነው፡፡ በዚህም 81 አስክሬን በቁፋሮ ተገኝቶ በክብር እንዲያርፉ መደረጉን አስታውቀዋል።
የሲሲአርዲኤ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ንጉሱ ለገሰ በጋሞ አካባቢ በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ሲሲአርዲኤ (CCRDA) አባላቱን በማስተባበር እና ድጋፎችን በማሰባሰብ በኩል ኃላፊነት ወስዶ እየሠራ መሆኑን አውስተዋል።
የክርስትያን በጎ አድራጎት እና ልማት ማህበራት ኅብረት (CCRDA) ከ500 በላይ አገር በቀልና ዓለም አቀፍ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን አባል ይዟል።
ሲሲአርዲኤ(𝐂𝐂𝐑𝐃𝐀)
LinkedIn: www.linkedin.com/in/ccrda-...
Telegram: https://t.me/ccrda_et
Twitter: https://x.com/CCRDA454972
Website: https://ccrdaeth.org/
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ccrda #civilsociety #ethiopia #humanitarianaid #nationaldialogue #development #civicengagement #etbusinessview

የሲሲአርዲኤ (CCRDA) የ53 ዓመታት የልህቀት አሻራ
የሲአርዲኤ በኢትዮጵያ የማህበረሰብ ለውጥና ልማት ላይ የሚሰራ አንጋፋ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት (ኮንሶርትየም) ሲሆን፣ ላለፉት ግማሽ ክፍለ ዘመናት በሀገሪቱ የልማት ስራዎች ላይ ጉልህ አሻራ አሳርፏል።
እ.አ.አ በ1973 በኢትዮጵያ ተከስቶ በነበረው ረሃብ ወቅት፣ የእርዳታ እና መልሶ ማቋቋም ስራዎችን ለማከናወን በልበ ቀናዎች የተመሰረተ ተቋም ነው።
ዛሬ ላይ የ53 ዓመታት የልህቀት እና የለውጥ ጉዞን አስቆጥሯል።
ራዕይ፦
ድህነት ተወግዶ ማየት።
ተልዕኮ፦
ማህበራዊ ፍትሕ እንዲሰፍን ከአባላት ጋር በትጋት መስራት።
በአሁኑ ወቅት ከ500 በላይ አባላት ያሉት ሲሆን፣ አባላቱም በሀገሪቱ አራቱም ማዕዘናት በሚከተሉት ዘርፎች ይሰማራሉ፦
ሰብዓዊ ድጋፍ እና ጤና
ልጆች፣ ወጣቶች እና ስነ-ፆታ
አካባቢ ጥበቃ እና የውሃ ንፅህና
ኤች አይ ቪ መከላከል
መልካም አስተዳደር እና ዲሞክራሲያዊ ባህል ግንባታ
ሲሲአርዲኤ አባላቱ ተሞክሮ የሚለዋወጡባቸው መድረኮችን በማዘጋጀት፣ በፖሊሲ ውትወታ (Advocacy) እና በሀብት ማሰባሰብ ረገድ የአባላቱን ተፅዕኖ የማሳደግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
𝐅𝐚𝐜𝐞𝐛𝐨𝐨𝐤: https://web.facebook.com/c...
𝐋𝐢𝐧𝐤𝐞𝐝𝐈𝐧: www.linkedin.com/in/ccrda-...
𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦: https://t.me/ccrda_et
𝐘𝐨𝐮𝐓𝐮𝐛𝐞: https://www.youtube.com/@c...
𝐗 (𝐓𝐰𝐢𝐭𝐭𝐞𝐫): https://x.com/CCRDA454972
𝐖𝐞𝐛𝐬𝐢𝐭𝐞: https://ccrdaeth.org/
#ccrda #ሲሲአርዲኤ #ethiopia #ngos #civilsociety #development #socialjustice #53yearsofservice #impact #humanitarianaid #policyadvocacy #communitydevelopment #ethiodevelopment

Comments