45 mins. ago
እነማን ተሾሙ ?
በዛሬው ዕለት ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚኒስትር ዴኤታነት ከሾሟቸው መካከል የቀድሞ የህወሓት አመራር እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ይገኙበታል።
ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም የሴቶችና የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተሹመዋል።
ሌላው፥ የኢዜማው መሪ አቶ እዮብ መሳፍንት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሹመዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት ፣ ከዛ በፊት በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ፣ በብሔራዊ መረጃና ደህነትም አመራር ሆነው ያገለገሉት እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር) የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ተደርገዋል።
ሌላው በሲዳማ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ አብርሃም ማርሻሎ የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሹመዋል።
የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) በፌዴራል ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሹመዋል።
ሌላው የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በነበረበት ወቅት ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት አቶ በረሆ ሀሰን የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ተደርገዋል።
የፋይዳ ቨርስ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ዮዳሄ አርአያስላሴ የቀድሞ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በሚመሩት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታነት ተሹመዋል።
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #ሹመት በዛሬው ዕለት 62 አመራሮችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚኒስትር ዴዔታነት ሾመዋል። (የተሿሚዎች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል) መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

6 hours ago
#getachewreda
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ አቶ ጌታቸው ረዳን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አድርገው በድጋሚ ሾመዋል።
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia Photo

5 hours ago
#moe
#tigray
የትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ ለነበሩ ነባር ተማሪዎች በጊዜያዊ ምደባ ሂደት ላይ የቀረቡ ቅሬታዎችን የማጣራት ሥራ አጠናቆ ምላሽ መስጠቱን አስታውቋል።
ተማሪዎቹ በዚህ ማስፈንጠሪያ https://student.ethernet.e... በመግባት የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ ማረጋገጥ እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ገልጿል።
የምደባ መረጃው በቀጥታ ለዩኒቨርሲቲዎቹ የሚላክ ሲሆን፣ ተማሪዎች ተቋማቱ በሚያወጡት የጥሪ መርሃ ግብር መሠረት በመሄድ ትምህርታቸውን መቀጠል ይችላሉ።
ሚኒስቴሩ የተስትካከለ ምደባ ሊኖር ስለሚችል ተማሪዎች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ከመሄዳቸው በፊት የምደባ መረጃቸውን በዚህ ገብተው https://student.ethernet.e... እንዲያረጋግጡ አሳስቧል።
በተጨማሪም አዲስ ተማሪዎች የተመደቡበትን ተቋም በዚህ ማስፈንጠሪያ https://student.ethernet.e...
ማየት እንደሚችሉ አስታውቋል።
ትምህርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ፤ አሁን ላይ ሁኔታዎች እየተሻሻሉ በመሆናቸው በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን መቀጠል የሚፈልጉ ተማሪዎች (ጊዜያዊ ምደባ የተሰጣቸውን ጨምሮ) የዩኒቨርሲቲዎቹን የጥሪ ማስታወቂያዎች በመከታተል ትምህርታቸውን በነበሩበት ተቋም መቀጠል ይችላሉ።
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia ምደባ ይፋ ሆነ። በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስደው በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የመግቢያ ውጤት ላስመዘገቡ እና በ2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደቡ ተማሪዎች ምደባ ይፋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋቃ። በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተመደቡበትን…

15 hours ago
#mekelle📍
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወደ መቐለ ከተማ ገብቶ ስምሪት ወስዶ የሰላም፣ የጸጥታና ማረጋጋት ሥራዎችን መስራት መጀመሩ ተሰምቷል።
አሶሼትድ ፕሬስ (AP) እንደዘገበው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የመቐለ ነዋሪዎች ፣ የከተማዋን ሰላምና መረጋጋት ወደነበረበት ለመመለስ እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርቧል።
ፖሊስ አዲስ አስተዳደር አዲቋቋም ለሚሰራው የማረጋጋት እና ጸጥታ የማስፈን ስራ ነዋሪዎች እንዲተባበሩ በድምፅ ማጉያ ጥሪ እንዳቀረበ ተዘግቧል።
መቐለ በአሁኑ ጊዜ አዲስ ባለስልጣናትን እየጠበቀች ሲሆን ዛሬም በከተማዋ የመንግስት ቢሮዎች ተዘግተው እንደዋሉ ዶቼ ቨለ ዘግቧል።
የፌደራል ፖሊስ እና የትግራይ የሰላም ሃይል ፤ የመቐለ ከተማ ፀጥታን እየጠበቁ ናቸው።
ይህን በእንዲህ እንዳለ ነዋሪዎች ዛሬ በሰጡን ቃል ፤ በከተማው የፌዴራል ፖሊስ መሰማራቱን አረጋግጠው የከተማዋ ትራፊክ ፖሊስ አባላት ሪፖርት አድርገው ወደመደበኛ ሥራ መግባታቸውን አመልክተዋል።
ሌሎች ቢሮዎችም ከሰኞ ጀምሮ ሪፖርት እያደረጉ እንዲገቡ ጥሪ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
የፌዴራል ፖሊስ የአውሮፕላን ማረፊያውን ጨምሮ ትልልቅ መንግሥታዊ ተቋማትን የመጠበቅ ኃላፊነት እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ/ም።

ፎቶ 📷 መቐለ በተሻለ መረጋጋት ላይ ብትሆንም አሁንም ግን በጠራራ ፀሀይ እና ጨለማን ተገን በማድረግ የሚፈጸም ዝርፊያ መኖሩን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠቁመዋል። ለአብነት ትላንት ለሊት ዘራፊዎች ወደ ትግራይ ጠቅላይ ፍ/ቤት ግቢ ጨለማን ተገን አድርገው ገብተው የህዝብ ንብረት ላይ ዝርፊያ ፈጽመዋል።
ፎቶ ባለቤት ፦ አብርሃ ኪሮስ
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #mekelle📍 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወደ መቐለ ከተማ ገብቶ ስምሪት ወስዶ የሰላም፣ የጸጥታና ማረጋጋት ሥራዎችን መስራት መጀመሩ ተሰምቷል። አሶሼትድ ፕሬስ (AP) እንደዘገበው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የመቐለ ነዋሪዎች ፣ የከተማዋን ሰላምና መረጋጋት ወደነበረበት ለመመለስ እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርቧል። ፖሊስ አዲስ አስተዳደር አዲቋቋም ለሚሰራው የማረጋጋት እና ጸጥታ የማስፈን ስራ ነዋሪዎች እንዲተባበሩ…

#adigrat 📍
ዓዲግራት ከተማ ዛሬም የሚጠብቃት ኃይል ሳይኖር ውላለች። ነዋሪዎች በየሰፈሩ ተደራጅተው አካባቢያቸውን ከዘራፊዎች እየጠበቁ ይገኛሉ።
የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ ዛሬ ቀን እንዲሁም አሁን በዚህ ሰዓት (በለሊት) " ተቋማችንን አናስደፍርም " በማለት ከዝርፊያ እየጠበቁ ይገኛሉ።
ከሀገር መከላከያ ጋር የሚንቀሳቀሰው የትግራይ ሰለም ኃይል ወደ ዓዲግራት መቃረቡንና ከተማዋ በከበባ ውስጥ መሆኗን አሳውቋል።
ፎቶ፦ ሳሚሀለፎም

14 hours ago
የሚዘጋ መንገድ ⚠️
#addisababa
ከመርካቶ - በመሣለሚያ ወደ 18 ቁጥር ማዞሪያ የሚወስደውን መንገድ እየተገነባ ሲሆን ይህ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 18 ቁጥር ማዞሪያ አካባቢ የላይ እና የታች የትራፊክ ማሳለጫ ድልድይ አካቶ የሚገነባ መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አሳውቋል።
ለግንባታው ሲባል የ 18 ቁጥር ማዞሪያ የቀለበት መንገድ ከቅዳሜ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ በጊዜያዊነት ለትራፊክ እንቅስቃሴ ዝግ ይሆናል።
ለከባድ፣ መካከለኛና ቀላል ተሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶች ተጠቁመዋል።
ሊንኩን 👇 ተጭነው ያንብቡ ፤ ሼር ያድርጉ !
https://telegra.ph/Addis-A... Ababaየ18 ቁጥር ማዞሪያ የቀለበት መንገድ ዝግ ይሆናል ! የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን፤ ከመርካቶ - በመሣለሚያ ወደ 18 ቁጥር ማዞሪያ የሚወስደውን መንገድ እየገነባ ነው። ይህ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 18 ቁጥር ማዞሪያ አካባቢ የላይ እና የታች የትራፊክ ማሳለጫ ድልድይ አካቶ የሚገነባ ነው። ለግንባታው መፋጠን ሲባል፤ የ18 ቁጥር ማዞሪያ የቀለበት መንገድ ከቅዳሜ ከመስከረም 30 ቀን 2019…

ትላንት የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ከኮዬ ወደ ጎሮ አደባባይ የሚወስደው አስፋልት መንገድ ተቆርጦ እየተሰራ መሆኑን ገልጾ ነበር።
በሥፍራው ላይ እየተካሄደ ባለው የግንባታ ሥራ ምክንያት ከነገ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ እሁድ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ፤ ከጎሮ አደባባይ - ኮዬ ፈጬ የሚወስደው መንገድ በከፊል ለትራፊክ ዝግ ይደረጋል ብሏል።
በዚህም ፦
👉 ከኮዬ ፈጬ ወደ ጎሮ አደባባይ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች በቡልቡላ በኩል - ቦሌ ኤርፖርት - ጎሮ አደባባይ የሚወስደውን አዲሱን መንገድ እንዲጠቀሙ፤
👉 ከጎሮ አደባባይ ወደ ኮዬ ፈጬ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች፣ የትራፊክ መጨናነቅ ሁኔታን ለመቀነስና ጊዜ ለመቆጠብ፤ ከጎሮ - በቦሌ ኤርፖርት አዲሱ መንገድ በመጠቀም በቡልቡላ በኩል ወደ ኮዬ አደባባይ መጓዝ እንደሚችሉ ተገልጿል።
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia 🚧 ከጎሮ አደባባይ-ኮዬ ፈጬ- ቱሉ ድምቱ አደባባይ በሚወስደው መንገድ የኮሪደር መሰረተ ልማት እየተከናወነ ሲሆን አይሲቲ ፓርክ አካባቢ በመሬት ውስጥ ለሚቀበሩ የመሰረተ ልማት ስራዎች ዝርጋታ ሲባል ዋናው አስፋልት መንገድ የተቋረጠ መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አሳውቋል። በዚህ ምክንያት የትራፊክ መዘጋጋት እንዳጋጠመ ተገልጿል። ከዛሬ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም…

Sponsored by
Surafel
17 hours ago
የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል።
በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተደረገውን የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ተከትሎ በርካታ ተማሪዎችና ተፈታኞች ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
አገልግሎቱ ባወጣው አዲስ የክፍያ ተመን፣ ቀደም ሲል 750 ብር የነበረው የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ክፍያ ወደ 2,000 ብር ከፍ ብሏል። በተጨማሪም በድህረ-ምረቃ መግቢያ፣ በ12ኛ ክፍል ፈተና እና በሌሎች የማረጋገጫ አገልግሎቶች ላይ ተመሳሳይ የክፍያ ጭማሪ ተደርጓል።
በጉዳዩ ላይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን የሰጡ ተማሪዎች፣ አዲሱ የክፍያ ተመን በተለይ ለሥራ አጥና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ተማሪዎችና ቤተሰቦች ተጨማሪ ጫና የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።
በ2017 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ወስዳ እንዳልተሳካላት የገለጸች አንዲት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪ፣ ለ16 ዓመታት የለፋችበት ትምህርት ውጤት አልባ ሆኖ እንዳይቀር በድጋሚ 750 ብር እየከፈለች ፈተናውን መውሰዷን ተናግራለች። አሁንም ስላልተሳካላት ለሦስተኛ ጊዜ ለመሞከር እያሰበች ቢሆንም፣ አዲሱ የክፍያ ተመን እንዳስደነገጣት ገልጻለች።
" 2,000 ብር መክፈል በጣም ከባድ ነው። ሥራ አጥ ነኝ፣ በጣም የሚያስጨንቅ ውሳኔ ነው። ለሦስተኛ ጊዜ ለመፈተን እያሰብኩ ነበር። አሁን ግን 2 ሺህ ከፍዬ ከመፈተን ይልቅ አለመፈተንን መርጫለሁ " ብላለች።
የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ለመጀመር እየሞከሩ ያሉ ተማሪዎችም የአገልግሎቱ አዲስ የክፍያ መጠን " ተስፋችንን የበለጠ አጨልሞታል፣ በትምህርት የሚያምኑ ሰዎችን ተስፋ የሚነጥቅ ነው " ብለዋል።
አንድ ተማሪ ለአገልግሎቱ 3,500 ብር እንዲከፈል መጠየቅ ምን ማለት ነው ? ሲሉ የጠየቁት ተማሪዎቹ ትምህርት የቅንጦት ጉዳይ ሳይሆን ራስን ለማሳደግና ለማሻሻል የሚደረግ ነው። ታዲያ የተጋነነ ዋጋ እንድንከፍል የምንደረገው ለምንድን ነው ? " ብለዋል።
" የፈተናው ይዘት በራሱ የተማሪዎችን ችሎታ ለመመዘን አይመስልም " ያሉት ተማሪዎቹ ከ750 ብር ወደ 3,500 ብር ማሳደጉ ተማሪዎች ፈተናውን ደጋግመው እንዳይወስዱ እንቅፋት እንደሚሆን ገልጸዋል።
" አንዳንዴ ገቢ መሰብሰብ ብቻ የሚመስሉ አጋጣሚዎች አሉ " ሲሉ ወቅሰዋል።
ለጤና ባለሙያዎች አሁን ያለው ጊዜ አስቸጋሪ መሆኑን የገለጸ ተማሪ ደግሞ " በኑሮ ውድነቱ ከዘርፉ እየወጣን ነበር፣ አሁን ጭራሽ በሙያው ላይ የበለጠ ተስፋ እንድንቆርጥ እያደረጉን ነው " ብሏል።
ሌላው ተማሪ ደግሞ፣ " 3,500 ብር ከፍሎ መፈተን በጣም ያስፈራል " ሲል፣ ለትምህርት የሚወጡ ወጪዎች ቢያንስ ሁሉንም ያማከሉ መሆን እንዳለባቸው ገልጿል።
" በፈተና መውደቅ አለመውደቅ የተፈታኙ ኃላፊነት ሊሆን ይችላል። ቢያንስ ለመሞከር ግን እንደዚህ በሩ መጥበብ የለበትም " ብሏል።
ሌላ ተማሪ ደግሞ ሰዎች ትምህርት መማር እየፈለጉ ባላቸው ገቢና በኑሮ ውድነት ምክንያት መማር ካልቻሉ፣ ይህ ለሚመጣው ትውልድ የመማር ፍላጎትን ሊያወርድ እንደሚችል ገልጿል።
" ሰዎች እንዳይማሩ በዚህ ልክ ክፍያ መጠየቅ እንዴት ሊብራራ እንደሚችል አላውቅም! " ሲል ተናግሯል።
" ክፍያ የተጨመረበት ዓላማ ራሱ ምን እንደሆነ አይታወቅም። ተማሪ መሆን የሚፈልግ ነው ሁለተኛ ዲግሪውን የሚማረው፣ ስለዚህ ክፍያው ሁሉን ያማከለ ቢሆን ጥሩ ነው " ሲልም ሌላ ተማሪ ገልጿል።
የፈተናዎች ኤጀንሲ ያወጣውን አዲሱን የአገልግሎት ክፍያ መረጃ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ላይ እንዳየ የገለጸ አንድ የ12ኛ ክፍል ተማሪ፣ መረጃውን በተመለከተበት ወቅት " እውነት ለመናገር ደንግጫለሁ፣ የማዘን ስሜትም ተሰምቶኝ ነበር፤ ያልጠበኩት ውሳኔ ነው " ብሏል።
ተማሪው ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 950 ብር መጠየቁን አግባብነት የሌለው እንደሆነ ገልጿል።
" የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሥራው ትምህርት ነው፣ ክፍያ የለውም፣ ገቢ ወደሚያስገኝ ሥራ አልገባም፣ በቤተሰብ ላይ ጥገኞች ነን። ለፈተና ይሄን ያህል ክፈሉ ብሎ ሌላ ጫና መፍጠር፣ መክፈል በማይችሉት ላይ ችግር መፍጠር ነው " ብሏል።
አክሎም፣ " ተማሪዎችን የሚያገል ደንብ ነው። ፍትሐዊና ሁሉን ያማከለ አይደለም። ትምህርት የመማር መብት አለን፣ እንዳንማር የሚያደርጉ ውሳኔዎች ሊኖሩ አይገባም። አሁን ላይ ትምህርት ከመሠረታዊ መብትነት ይልቅ የተወሰኑ ገንዘብ ያላቸው የሀብታም ልጆች ብቻ እንዲማሩ እየተደረገ ነው " ሲል ተናግሯል።
በተጨማሪም የስም ስህተትን ጨምሮ እንደዚህ ያሉ ስህተቶችን ለማስተካከል የሚጠየቁ ክፍያዎች ሙሉ በሙሉ መቅረት እንዳለባቸው ተማሪዎቹ ገልጸዋል።
" በተቋማት በኩል በሚፈጠሩ ስህተቶች ተማሪዎች ልንጨነቅ አይገባም " ሲሉ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ላይ ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምላሽ ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም ምላሽ ማግኘት ባለመቻሉ የአገልግሎቱ ምላሽ በዚህ ዘገባ ውስጥ አልተካተተም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#tikvahethiopia
@tikvahethiopia የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ክፍያ ከ750 ወደ 2,000 ብር ከፍ አለ። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለሚሰጣቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈል ክፍያን የሚያሻሽል አዲስ ደንብ ወጥቷል። በዚህም ቀደም ሲል 750 ብር የነበረው የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) ክፍያ ወደ 2,000 ብር ከፍ ብሏል። ከዚህ ውስጥ 500 ብር የምዝገባ፣ 1,500 ብር ደግሞ የፈተና ክፍያ ሲሆን፣ ለውጭ ዜጎች…

18 hours ago
የቀድሞ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በአፋር ክልል ሹመት ተሰጣቸው።
የክልሉ ፕሬዜዳንት ሀጂ አወል አርባ፣ ኢንጂነር አይሻ መሀመድን የአፋር ክልል የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ኃላፊ አድርገው ሹመዋል።
ኢ/ር አይሻ የመጀመሪያዋ ሴት የሀገር መከላከያ ሚኒስትር እንዲሁም በተለያዩ የፌዴራል መስሪያ ቤቶች ውስጥ በአመራርነት አገልግለዋል።
ትላንትና በነበረው የሚኒስትሮች ካቢኔ ሹመት ውስጥ ያልተካተቱ የቀድሞዋ ሚኒስትር ወደ ክልል አምርተዋል።
በሌላ በኩል፤ ፕረዚዳንት ሃጂ አወል አርባ ዛህራ ሁመድ አሊን የክልሉ የውሃና ኢነርጂ ቢሮ የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አድርገው ሾመዋል።
#tikvahethiopia
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia

20 hours ago
#ehrc
በአፋር ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፣ ጋምቤላ ፣ ሶማሊ ፣ ትግራይ ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በኢስመኮ ዓመታዊ ሪፖርት #ehrc
@tikvahethiopia #oromiaregion ⬆️ ኢስመኮ ከሰኔ ወር 2017 ዓ/ም - ሰኔ ወር 2018 ዓ/ም ድረስ ባለው ዓመታዊ ሪፖርቱ በኦሮሚያ ክልል በመንግስት እና በክልሉ በሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች ስለተፈጸሙ የግድያ ጨምሮ ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል። @tikvahethiopia

1 day ago
#tecno_pova_curve2_5g
TECNO እጅግ ቀጭኑን እና በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የታጀበውን አዲሱን TECNO POVA CURVE 2 5G ይዞላችሁ መቷል፡፡ 7 ነጥብ 42 ሚሊ ሜትር ብቻ የሆነ ቀጭን ስልክ፣ ከርቭ AMOLED ጥርት ያለ ስክሪን እና ሌሎችም በርካታ ቴክኖሎጂዎችን የያዘውን ይሄን ድንቅ ስልክ ዛሬውኑ የራሶት ያድርጉት!!
#tecno #povacurve2_5g #tecnoai #tecnoet
tecno_et

#update
በአዲስ ዌስት ማከፋፈያ ጣቢያ ጉዳት የደረሰበትን ትራንፎርመር በሌላ ለመተካት ከአርባምንጭ ተነስቶ ሲጓጓዝ የነበረው ትራንስፎርመር ዛሬ ጠዋት ከቢሾፍቱ ተነስቶ አዲስ አበባ ገብቷል።
" ትራንስፎርመሩ ማከፋፈያ ጣቢያው ወደሚገኝበት ኮልፌ አካባቢ እየተጓጓዘ ቢሆንም ሆላንድ ኤምባሲ አካባቢ ደርሶ ዳገቱ ላይ ቆሟል " ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገልጿል።
ትራንስፎርመሩ ማከፋፈያ ጣቢያው ሲደርስ መልሶ የመገጣጠም ሥራዎች ወዲያውኑ የሚጀመሩ ይሆናል ተብሏል።
በአዲስ ዌስት ማከፋፈያ ጣቢያ ጉዳት ከ15 ቀናት በላይ በርካታ የአዲስ አበባ ከተማ አከባቢዎች በመደበኛነት የኤሌክትሪክ ኃይል እያገኙ አይደለም።
Update : 8:30 ላይ ትራንስፎርመር የማጓጓዙ ስራ መጠናቀቁ ተገልጿል።
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #update የአዲስ ዌስት ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያን ወደ አገልግሎት ለመመለስ አማራጭ የመፍትሔ እርምጃዎች በትይዩ እየተከናወኑ መሆኑ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። • የተበላሸውን ትራንስፎርመር በሌላ ለመተካት የሚያስችል ተለዋጭ ትራንስፎርመር ከአርባ ምንጭ የማጓጓዝ ሥራ ከተጀመረ ሁለት ቀናት መቆጠሩንም ተገልጿል። በቴክኒክ ብልሽት ምክንያት አገልግሎት መስጠት ያቆመውን የአዲስ…

ወደ መቐለ ጥቅምት 1 በረራ ይጀመራል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረው ወደ መቐለ ከተማ የሚያደርገው መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የሚጀምር መሆኑን አሳውቋል።
ደንበኞች በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ በመሄድ ወይም ወደ ጥሪ ማዕከሉ 6787 በመደወል የጉዞ ምዝገባ ማስያዝ እንደሚችሉ ገልጿል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia " ሁኔታዎች ሲስተካከሉ አየር መንገዱ በ24 ሰዓት ውስጥ በረራዎችን በድጋሚ ለማስጀመር ዝግጁ ነው " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ (ለቲክቫህ ኢትዮጵያ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ዳግም የሚጀምርበት ቀን እስካሁን ድረስ እንዳልተወሰነ የአየር መንገዱ ከፍተኛ ኃላፊ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። በአየር መንገዱ የቲኬት መቁረጫ የኦንላይን ሲስተም ላይ…

2 days ago
" ለፍርድ ቤት አመልክቻለሁ " - ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ
ከነበሩበት የእስር ቦታቸው ወደ "መቅጫ ቤት" መዛወራቸውና የተወሰኑት "የት እንደተወሰዱ አልታወቀም" የተባሉት የይቅርታ ሰነድ ላይ "አንፈርምም" ብለው እስር ላይ የቆዩ እስረኞች ስላሉበት ሁኔታ ታሳሪ ቤተሰብና ጠበቃቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አቶ ዮሐንስን ቧያሌውን ጨምሮ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና እሱባለው በለጠ፣ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት "ቅጣት ቤት" በተለምዶ "ታንከር" በሚባል ቦታ እንዲገቡ መደረጋቸው ከሳምንት በፊት ተገልጾ ነበር።
• ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም፣
• ዶ/ር ወንዶሰን አሰፋ፣
• ፕ/ር ሲሳይ አውግቸው፣
• መንበር አለሙ፣
• ጠበቃ አለልኝ፣
• ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፣
• ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱን ደግሞ " የጸጥታ አካላት የት እንደወሰዷቸው አይታወቅም " ነበር የተባለው።
ጠበቃ ሰለሞን አቶ ገዛኸኝ በበኩላቸው ይህንኑ መረጃ ከታሳሪ ቤተሰቦች እንደሰሙና የእስረኞቹን ሁኔታ በአካል ለማየት ወደ ማረሚያ ቤት እንደሚሄዱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መናገራቸው ይታወሳል።
ስለተከሳሾቹ አሁንስ ምን ተባለ ?
እስረኞቹ ከዚያ በኋላ ያሉበት ሁኔታ በተመለከተ የነገሩን አንድ የታሳሪ ቤተሰብ፣ " ቅጣት ቤት እንዲገቡ የተደረጉት አሁንም እዛው ናቸው " ብለዋል።
" የት እንደተወሰዱ አልታወቀም " የተባሉትም እስር ቤት ነው የሚገኙት ሲሉ ገልጸዋል።
" መብራት እና ውሃ በሌለው በዚህ ቅጣት ቤት ከሁለት ቀናት በላይ እስረኛ ታስሮ አያውቅም። በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው ያሉት " ሲሉም ተናግረዋል።
" ዶክተር ወንዶሰን አሰፋን ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ዞን 6 ቅጣት ቤት ነው ያስገቡት " ብለዋል።
ወደ አባ ሳሙኤል ማረሚያ ቤት የተወሰዱ እንዳሉም ገልጸዋል።
" ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ፣ ዶክተር ሲሳይ አውግቸው እና ዶክተር ቴዎድርስ ኃይለማርያምን ወደ ሌላ ክፍል አዘዋውረዋቸዋል። አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ እሱባለው በለጠ አሁንም በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ቅጣት ክፍል ውስጥ ናቸው " ብለዋል።
" ጉዳዩን ለመከታተል እስረኞቹን በአካል ጠይቄያለሁ " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጹት ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ በበኩላቸው፣ " አሁንም እዛው ናቸው፤ ዶክተር ወንዶሰንም ቂሊንጦ ቅጣት ቤት ውስጥ ነው " ብለዋል።
" አቶ ዮሐንስ ቧያሌው፣ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና እሱባለው በለጠ ቃሊቲ 'ታንከር' የሚባለው ቦታ ናቸው " ያሉ ሲሆን " ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ እና ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ በተለየ ክፍል ለብቻቸው ናቸው " ሲሉ ተናግረዋል።
ከላይ የተጠቀሱት እዛው ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የተበተኑ ሲሆኑ፣ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የተወሰዱ እንዳሉም ተጠቁሟል።
በዚህም፦
- ዶ/ር ወንዶሰን አሰፋ ዞን 6 የቅጣት ቦታ፣
- ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው እና ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም ዞን 4፤
- አለልኝ ምህረቱ ዞን 1፤
- አሳምነው ታደሰ መለሰ ቸሩ ዞን 3
- መንበር አለሙ እና እስክንድር ሽፈራው ዞን 5 አይጠ መጎጥ እና ተባይ ያለበት ቦታ ውስጥ ነው ያደረጓቸው ሲሉ ጠበቃ ሰለሞን ተናግረዋል።
በተያያዘ፥ ጠበቃ ሰለሞን በላኩልን ሰነድ፦
° ሚካኤል መላክ፣
° ፍርዱ ተፈራ፣
° ያሬድ ግርማ የሚባሉ እስረኞች ወደ አባሳሙኤል እስር ቤት መወሰዳቸውን ያስረዳል።
እንዲሁም፣ ሕይወት አለማየሁ እና ሐሊማ ሙሐመድ የሚባሉ እስረኞች " ወደ ሌላ ቦታ ተወስደው ጠያቂ ቤተሰባቸውን ልክ እንደ በፊቱ ማግኘት አልቻሉም። ሕይወት አለማየሁ የኩላሊት፣ ሐሊማ ሙሐመድ ከፍተኛ የእግር ህመም ያለባቸው በመሆኑ የተቀየሩበት ቦታ ህመሙን አባብሶባቸዋል " ሲልም ይገልጻል።
የቅጣት ቦታ ያሉ ተከሳሾቹ ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ መፍትሄ እንዲሰጥ ለፍርድ ቤት ማመልከታቸውንም ጠበቃ ሰለሞን ነግረውናል።
ጠበቃው ለፍርድ ቤት ያስገቡት ሰነድ፥ ተከሳሾቹ ደረሰብን ያሉት የመብት ጥሰት እና ያሉበትን ሁኔታ በመዘርዘር፣ ቅጣት ቦታ ያሉት እንዲወጡ እንዲደረግ፣ ተከሳሾች ላይ ይህን ያደረጉ ኃላፊዎች እንዲጠየቁ እና የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ያሳስባል።
የማረሚያ ቤት ኃላፊዎች እና የጸጥታ አካላት ማብራሪያ አለን ካሉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሚያስተናግዳቸው ይሆናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia " እነዚህ ሰዎች ክሳቸውን እየተከታተሉ ያሉ ናቸው። ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ሳይላቸው ነው እንዲህ የሚደረጉት " - የታሳሪ ቤተሰብ የይቅርታ ሰነድ ላይ "አንፈርምም" ብለው እስር ላይ የቆዩ ታሳሪዎች ከነበሩበት እስር ቤት እንዲወጡ ተደርገው ወደ ሌላ ቦታ መወሰዳቸውን አንዳንዶቹ የት እንዳሉ ለማወቅ እንዳልተቻለ የታሳሪ ቤተሰቦች እና ጠበቃ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ። አንድ የታሳሪ ቤተሰብ ፥ " ማረሚያ ቤት…

Tigray Region 📍
መቐለ
እስከ ጥቅምት 05 ቀን 2019 ዓ.ም. ባሉት ቀናት ውስጥ የመቐለ ከተማ መደበኛ የፖሊስ አባላት ወደ መደበኛ የሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።
የመቐለ ከተማ ፖሊስ፣ አባላቱ በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ሪፖርት ካላደረጉ በራሳቸው ፍላጎት ከሥራ እንደለቀቁ እንደሚቆጠሩ አሳውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባገኘው መረጃ ዛሬ አንዳንድ ፖሊስ አባላት በቀረበው ጥሪ መሰረት ወደ ስራቸው ለመመለስ ሪፖርት ማድረግ መጀመራቸውን ተረድቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ መቐለ አሁን ላይ ካለፉት ቀናት በተሻለ መረጋጋት እና ወደ መደበኛው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ እየገባች ትገኛለች።
ቃለቸውን የሰጡን ነዋሪዎች፤ የሚፈጸሙ ዝርፊያዎች እና የፀጥታ ስጋቶች በእጅጉ መሻሻል አሳይተዋል።
የሀገር መከላከያ እና የትግራይ ሰላም ኃይል እንቅስቃሴ
የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ የሰላም ኃይል የደቡባዊ እና ደቡብ ምስራቅ አካባቢዎችን ከተቆጣጠሩ በኋላ ወደ ሰሜናዊ ምዕራብ፣ ምስራቃዊ እና ማዕከላዊ ዞኖች አምርተዋል።
በማዕከላዊ ዞን ሶስተኛዋ ትልቅ ከተማ የሆነችው ዓብዪ ዓዲን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በኩል፥ የዞኑን መቀመጫ የሆነችው የእንዳስላሴ (ሽረ) ከተማን ለመቆጣጠር በቅርብ ርቀት ላይ እንደሚገኙ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በምስራቃዊ ዞን የአጉላዕ እና ውቕሮ ከተሞችን በቁጥጥር ሥር በማዋል ወደ ዞኑ ዋና መናገሻ ዓዲግራት ከተማ እያመሩ መሆኑ ተነግሯል።
የኤርትራ (ሻዕቢያ) ሰራዊት
የኤርትራ (ሻዕቢያ) ሰራዊት ወደ ኢትዮጵያ ምድር ትግራይ ክልል ዘልቆ መግባቱ ይታወቃል።
ኤጀንሲ ፋራንስፕሬስ (AFP) በርከታ ምንጮች የኤርትራ ወታደሮች ዓዲግራት ከተማ ዙሪያ መሰማራታቸውን እንደገለጹለት ዘግቧል።
የግጭት ክትትል ተቋም የሆነው ACLED ይፋ ባደረገው መረጃ፤ በዓዲግራት አካባቢ "የኤርትራ ወታደሮች" ላይ ያነጣጠሩ በርካታ የድሮን ጥቃቶች መፈጸማቸውንና ኃይሎቹ መመታታቸው ተገልጿል።
በስማቸው እንዳይገለጹ የጠየቁ የዓይን እማኞች ለAFP እንደተናገሩት፤ " ትናንት በርካታ የድሮን ጥቃቶች ነበሩ። የኤርትራ የጭነት መኪኖች ወድመዋል። ከዛ በኋላ በጎዳናዎች ላይ አልታዩም " ሲሉ አስረድተዋል።
ሌላው እማኝ በሌሊት ከፍተኛ ፍንዳታዎችን መስማቱን እና በድሮን ጥቃት የተመቱ የኤርትራ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን በአይኑ መመልከቱን ገልጿል።
ሦስተኛ እማኝ ደግሞ ከጥቃቶቹ በኋላ የኤርትራ ወታደሮች ወደ ሰሜን አቅጣጫ እያፈገፈጉ የሚመስል እንቅስቃሴ ላይ ናቸው ብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ደግሞ " የሻዕቢያ ሰራዊት " በዛላንበሳ መስመር ማፈግፈጉን ጠቁመዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከርም 28 ቀን 2019 ዓ/ም

አንድን ሹፌር በሰደፍ ሲመታ እና ሲደበድብ የሚታየው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በርካቶችን ያስቆጣ አንድ ቪድዮ እየተዘዋወረ ይገኛል።
ይህ ቪድዮ ሁለት የጭነት መኪናዎች በቆሙበት ለዜጎች የሕግ ከለላና ሰላም መስጠት የነበረበት አንድ የፖሊስ አባል አንድ ግለሰብ ላይ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እና ድብደባ ሲፈጽም የሚያሳይ ነው።
በርካታ ሰዎች የተፈጸመውን ድርጊት " ከህግ የወጣ እና ኢሰብዓዊ ፤ በየቦታው በሹፌሮች ላይ የሚፈጸመውን በደል ጭምር በገሃድ የሚያሳይ " ሲሉ ኮንነውታል።
" አልተቀረጸ እንጂ ሹፌሮች በየቦታው ይህን መሰል ተግባር ነው የሚገጽማቸው " ሲሉም ገልጸዋል።
ድርጊቱ መቼ እና የት ተፈጸመ ?
ብዙሃንን ያስቆጣው ድርጊት የተፈጸመው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጋሞ ዞን፣ ቦረዳ ወረዳ " ጠንጠሌ " ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በጋሞ ዞን የቦረዳ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ም/ኢንስፔክተር አብረሃም አየለን አነጋግሯቸዋል።
አዛዡ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ድርጊቱ የተፈፀመው መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ/ም ከሰዓት በኋላ ነው።
" በወረዳው ጠንጠሌ አከባቢ ' ዮ ሆልዲንግ ' ከተሰኘ የድንጋይ ከሰል አቅራቢ ድርጅት ሳይት ከሰል ጭነው በመውጣት ላይ የነበሩ የዳንጎቴ የጭነት መኪና አሽከርካሪዎች በአከባቢው ከነበሩ የፖሊስ አባላት ጋር ያለመግባባት ተፈጥሮ ነበር " ብለዋል።
" የፖሊስ አባሉ ፍጹም ተገቢ ባልሆነ መንገድ አሽከርካሪውን ሲመታው የሚያሳይ ምስል በዚያው ቅፅበት በማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጭቶ መረጃው በስልክ ነው የደረሰኝ " ሲሉ ገልጸዋል።
" መረጃው እንደደረሰን በዕለቱ ድርጊቱ በተፈፀመ 30 ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ነው አባሉን በቁጥጥር ስር ያዋልነው " ያሉት አዛዡ " በአሁኑ ወቅት ምርመራ ተጀምሯል የፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ እየተጠበቀ ነው " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" ድርጊቱ በየትኛውም አይነት መመዘኛ ትክክል አይደለም " ያሉ ሲሆን " የተፈጸመው ድርጊት ግለሰቡን እንጂ የወረዳውን ፣ የዞኑንና የክልሉን ፖሊስ የማይወክል ሆኖ ሳለ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሳራጩት አንዳንድ ማብራሪያና ፍረጃዎች ተገቢነት የላቸውም " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ከዳንጎቴ ተቋም በኩል መረጃ ለማግኘት ሙከራ አድርጎ አልተሳካም።
አንድ በተቋሙ ለዞኑ የተፃፈ ደብዳቤን ግን ተመልክቷል።
" ይህ የአሁኑን ጨምሮ በሌሎችም ጊዜያት የተለያዩ ክፍያዎችን እየከፈሉ ቢሆንም የድርጅቱን አሽከርካሪዎች እና መኪኖች ላይ ያለአግባብ የማንገላታት ሁኔታዎች አሉ " ይላል።
ድርጅቱ " ለልማት ማህበር፣ ለፋይናንስ ቢሮ፣ ለከተማ ልማት እንዲሁም ያለደረሰኝ 'የተራ እና ሽራ አሰራ' በሚል በድምሩ እስከ 27,100 ብር ህጋዊና ህገ-ወጥ ክፍያዎችን እየከፈለ " መሆኑን ጠቁሟል።
በተጨማሪም "ፓርኪንግ" በሚል ያልቆሙበትን ክፍያ ለመጠየቅ ሲባል ወጣቶች በመደራጀት ሾፌሮቹን ከ3 እስከ 4 ቀናት በማስቆም ከፍተኛ እንግልት እንደሚያደርሱባቸው ገልጿል።
" በመንገድ ላይ የተመደቡ ፖሊሶች ያለአግባብ ከሾፌሮች ከ200 እስከ 500 ብር ይጠይቃሉ " የሚለው የድርጅቱ ደብዳቤ " ክፍያውን ያልፈጸሙ አሽከርካሪዎችን በማንገላታትና በመደብደብ ጉዳት መድረሱን " አመልክቷል።
አንድ አሽከርካሪ በደረሰበት ከፍተኛ ድብደባ ምክንያት ደብዳቤ እንደተፃፈለትም ጠቅሷል።
እነዚህ አሰራሮች በአስቸኳይ እንዲቆሙ፣ የህግ የበላይነት እንዲከበር፣ አሽከርካሪዎች ያለስጋት ስራቸውን እንዲያከናውኑ እና ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀም ህገ-ወጥ ድርጊት የፈጸሙ አካላት በህግ እንዲጠየቁ ጠይቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ

የተባበሩት መንግስታት (UN) ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና ጄን ሙሀመድ አዲስ አበባ ይገኛሉ። ዛሬ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ጋር ተገናኝተው መክረዋል።
ሚኒስትሩ፥ ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ እየፈጸመች ስላለው ቀጣይነት ያለው የጠብ አጫሪነት ተግባና ይህም በቀጠናው ሰላምና ጸጥታ ላይ ሊያስከትለው ስለሚችለው አደጋ ጥልቅ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ለጉዳዩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግልጽና መርህን የጠበቀ አቋም ይዞ አስቸኳይ ምላሽ ሊሰጥበት እንደሚገባ ጌዲዮን (ዶ/ር) አጽንኦት ሰጥተዋል።
የኤርትራ ወታደራዊ ኃይሎች ከኢትዮጵያ ግዛት በአስቸኳይ እንዲወጡም አስጠንቅቀዋል።
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሕግን መሠረት በማድረግ ሉዓላዊነቷን እና የግዛት አንድነቷን የመከላከልና የማስጠበቅ ሕጋዊ መብት እንዳላት አረጋግጠዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia Photo
2 days ago
#adigrat
" ተቋማችን አይደፈርም ! " - የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ አባላት
ከኤርትራ ድንበር በ35 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ዓዲግራት ከተማ ከከሰዓት ጀምሮ የህወሓት ኃይል የለም፤ ከተማውን ለቆ ሄዷል።
በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን የአጉላዕ፣ ወቕሮ ከተሞችን የተቆጣጠሩት ሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ሰላም ኃይል ወደ ዓዲግራት እያመሩ መሆኑ ተነግሯል።
በአሁን ሰዓት ከተማዋን የሚጠብቅ ማንኛውም ኃይል ባለመኖሩ ነዋሪዎች በየሰፈሩ ተደራጅተው ከተማቸውን ከዘራፊዎች እየጠበቁ ይገኛሉ።
ልክ ህወሓት መቐለን ለቆ ሲወጣ እንደታየው በዓዲግራት ከተማ ዛሬ ቀን ላይ አንዳንድ የዘረፋ ምልክቶች ታይተው ነበር።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ " ተቋማችን አይደፈርም " በሚል ጥብቅ ጥበቃ እያደረገ ይገኛል።
የዩኒቨርሲቲ አመራሩ፣ ሠራተኞች፣ የጸጥታ አካላት እና የአካባቢው ማህበረሰብ ተቀናጅተው ተቋማቸውን በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ።
የአይሲቲ ሠራተኞች በደህንነት ካሜራ የታገዘ ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ። በድሮን ካሜራ ጭምር ክትትል እየተደረገ ነው።
ለመስረቅ ሙከራ የሚያደርግ አካል ከካሜራ ዓይን እና ከጥበቃዎች ማምለጥ አይችልም።
" ተቋማችን አይደፈርም " ያሉት መምህራን ፣ የአስተዳደር ሠራተኞች እና አመራሮችን በምሽት ጭምር ነው ጥበቃ እያደረጉ የሚገኙት።
Photo Credit - SamiHalefom

" በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ የላትም " - ጌዲዮን ጤሞቲዮስ (ዶ/ር)
👉 " ሁለቱን አገራት በእኩል ሚዛን ለማስቀመጥ የሚሞክር ማንኛውም አቋም ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኅንነት አይጠቅምም ! "
ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት በመግለጽ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) በደብዳቤ አሳወቀች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጤሞቲዮስ (ዶ/ር) ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ለመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አባላት ደብዳቤ መጻፋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
በዚህም ደብዳቤ፤ የኤርትራ ሠራዊት ድንበር አልፎ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት መግባቱን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በሁለት የተለያዩ ጊዜያት ለፀጥታው ም/ቤት አባላት በላከችው ደብዳቤ " ኤርትራ በተደጋጋሚ በፈጸመችው ጸብ አጫሪነት እና ድንበር ጥሶ የመግባት እርምጃ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት ላይ አደጋ መደቀኑን " በመጥቀስ ትኩረት እንዲሰጠው መጠየቃቸውን አስታውሰዋል።
" ኤርትራ የፀብ አጫሪነት ድርጊቷን በአሁኑ ጊዜ ከፍ ወዳለ ደረጃ አሸጋግራ ሜካናይዝድ ክፍሎችን ጨምሮ ወታደሮቿን በጥልቀት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት አሰማርታለች " ያሉት ጌዲዮን (ዶ/ር) ፥ " ይህም ሦስት የትግራይ ዞኖችን በማካተት በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ከ30 አስከ 60 ኪሎ ሜትር በሚደርስ ርቀት ወደ ውስጥ ገብተዋል " ብለዋል።
ሚኒስትር ጌዲዮን የኤርትራ ድርጊት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር ውስጥ የሰፈሩትን መሠረታዊ መርሆዎች በግልጽ የሚጥስ ነው በማለት " ይህም ኢትዮጵያ ራሷን የመከላከል ሕጋዊ መብት እንድትጠቀም የሚያስገድድ ነው " ሲሉ ጽፈዋል።
ለፀጥታው ም/ቤት የጻፉት ደብዳቤ የተፈጸመውን ወረራ ለማሳወቅ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ለምትወስደው የመከላከል እርምጃ ድጋፍ ጠይቀዋል።
" በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ የላትም " በማለት ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ የገጠማትን ሁኔታ በመረዳት ድጋፍ እንዲደያርግላት እና ከጎኗ እንዲቆም ጠይቀዋል።
ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ ከኤርትራ በኩል ለረዥም ጊዜ ሲፈጸሙ ለነበሩ ትንኮሳዎች በትዕግሥት እና ራስን በመቆጠብ መቆየቷን አመልክተዋል።
በመሆኑም " ሁለቱን አገራት በእኩል ሚዛን ለማስቀመጥ የሚሞክር ማንኛውም አቋም ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኅንነት አይጠቅምም " ብለዋል።
" ኤርትራ ወራሪ ናት፤ ኢትዮጵያ ደግሞ የወረራ ሰለባ ናት። ኤርትራ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እየጣሰች ነው " ሲሉም አሳውቀዋል።
ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ እንደሌላትም ገልጸዋል።
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሕግን መሠረት በማድረግ ሉዓላዊነቷ እና የግዛት አንድነቷን የመከላከልና የማስጠበቅ ሕጋዊ መብት እንዳላት አሳወቀች። የተባበሩት መንግስታት (UN) ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና ጄን ሙሀመድ አዲስ አበባ ይገኛሉ። ዛሬ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ጋር ተገናኝተው መክረዋል። ሚኒስትሩ፥ ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ እየፈጸመች ስላለው ቀጣይነት ያለው የጠብ አጫሪነት ተግባና…
👉 " ሁለቱን አገራት በእኩል ሚዛን ለማስቀመጥ የሚሞክር ማንኛውም አቋም ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኅንነት አይጠቅምም ! "
ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት በመግለጽ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) በደብዳቤ አሳወቀች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጤሞቲዮስ (ዶ/ር) ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ለመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አባላት ደብዳቤ መጻፋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
በዚህም ደብዳቤ፤ የኤርትራ ሠራዊት ድንበር አልፎ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት መግባቱን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በሁለት የተለያዩ ጊዜያት ለፀጥታው ም/ቤት አባላት በላከችው ደብዳቤ " ኤርትራ በተደጋጋሚ በፈጸመችው ጸብ አጫሪነት እና ድንበር ጥሶ የመግባት እርምጃ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት ላይ አደጋ መደቀኑን " በመጥቀስ ትኩረት እንዲሰጠው መጠየቃቸውን አስታውሰዋል።
" ኤርትራ የፀብ አጫሪነት ድርጊቷን በአሁኑ ጊዜ ከፍ ወዳለ ደረጃ አሸጋግራ ሜካናይዝድ ክፍሎችን ጨምሮ ወታደሮቿን በጥልቀት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት አሰማርታለች " ያሉት ጌዲዮን (ዶ/ር) ፥ " ይህም ሦስት የትግራይ ዞኖችን በማካተት በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ከ30 አስከ 60 ኪሎ ሜትር በሚደርስ ርቀት ወደ ውስጥ ገብተዋል " ብለዋል።
ሚኒስትር ጌዲዮን የኤርትራ ድርጊት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር ውስጥ የሰፈሩትን መሠረታዊ መርሆዎች በግልጽ የሚጥስ ነው በማለት " ይህም ኢትዮጵያ ራሷን የመከላከል ሕጋዊ መብት እንድትጠቀም የሚያስገድድ ነው " ሲሉ ጽፈዋል።
ለፀጥታው ም/ቤት የጻፉት ደብዳቤ የተፈጸመውን ወረራ ለማሳወቅ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ለምትወስደው የመከላከል እርምጃ ድጋፍ ጠይቀዋል።
" በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ የላትም " በማለት ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ የገጠማትን ሁኔታ በመረዳት ድጋፍ እንዲደያርግላት እና ከጎኗ እንዲቆም ጠይቀዋል።
ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ ከኤርትራ በኩል ለረዥም ጊዜ ሲፈጸሙ ለነበሩ ትንኮሳዎች በትዕግሥት እና ራስን በመቆጠብ መቆየቷን አመልክተዋል።
በመሆኑም " ሁለቱን አገራት በእኩል ሚዛን ለማስቀመጥ የሚሞክር ማንኛውም አቋም ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኅንነት አይጠቅምም " ብለዋል።
" ኤርትራ ወራሪ ናት፤ ኢትዮጵያ ደግሞ የወረራ ሰለባ ናት። ኤርትራ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እየጣሰች ነው " ሲሉም አሳውቀዋል።
ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ እንደሌላትም ገልጸዋል።
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia
Sponsored by
Surafel
2 days ago
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥
16ኛ ዙር የዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን። በስልጠናው፦
👉 መሠረታዊ የዲጂታል ማርኬቲንግ ፅንሰ ሀሳቦች ጀምሮ Affilate Marketing, Content Marketing, Email Marketing, Search Engine Optimization (SEO), Social Media Marketing (SMM), Meta Ads, Marketing Analytics አካቶ ይሰጣል።
👉 Content Creation እንዲሁም ማስታወቂያ አሰራርን አካቶ ይሰጣል።
👉 ግራፊክስን በCanva እና ኤዲቲንግን በCapcut ይሰለጥናሉ።
👉 በተጨማሪም ድረ-ገፅ አሰራር በ wordpress በስልጠናው ተካተዋል።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ፣ ቁ.2: መገናኛ ደራርቱ ህንፃ 5ኛ ፎቅ እና ቁ.3: አዳማ ራስ ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ለመመዝገብ ድረ-ገጽ 👇 www.sageethiopia.com
Telegram: https://t.me/sagetrainingi...

ለፍጆታ ሒሳብ ክፍያዎ... ሁነኛ ምርጫ!
የትምህርት ቤት ፣ የውሃ፣ የአየር መንገድ ትኬት እና ሌሎች ልዩ ልዩ የፍጆታ ክፍያዎችዎን በእጅዎ ባለው በአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ በቀላሉ ይክፈሉ!
አሁኑኑ መተግበሪያውን ያውርዱ፣ ህይወትዎን ያቃልሉ!ለመጀመር 👉https://bit.ly/BOAmbt

🚧
ከጎሮ አደባባይ-ኮዬ ፈጬ- ቱሉ ድምቱ አደባባይ በሚወስደው መንገድ የኮሪደር መሰረተ ልማት እየተከናወነ ሲሆን አይሲቲ ፓርክ አካባቢ በመሬት ውስጥ ለሚቀበሩ የመሰረተ ልማት ስራዎች ዝርጋታ ሲባል ዋናው አስፋልት መንገድ የተቋረጠ መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አሳውቋል።
በዚህ ምክንያት የትራፊክ መዘጋጋት እንዳጋጠመ ተገልጿል።
ከዛሬ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ፡-
👉 ከጎሮ አደባባይ ወደ ኮዬ ፈጬ አደባባይ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች ፣ በጎሮ - ቦሌ ኤርፖርት መንገድ አቅጣጫ ወደ ቡልቡላ በመጓዝ ወደ ኮዬ ፈጬ እና አካባቢው፤
👉 ከኮዬ ፈጬ ወደ ጎሮ አደባባይ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች ደግሞ ፤ ከኮዬ ፈጬ አደባባይ - በቡልቡላ በኩል ወደ ጎሮ አደባባይ የሚወስደውን የቦሌ ኤርፖርት - ጎሮ አዲሱን መንገድ እና ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልክዕክት ተላልፏል።

በሚኒስትርነት ያልተሾሙ / ከካቢኔ አባልነት የተነሱ እነማን ናቸው ?
1. በለጠ ሞላ (ዶ/ር)
2. አቶ መላኩ አለበል
3. አብርሃም በላይ (ዶ/ር)
4. ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)
5. ኢ/ር አይሻ መሀመድ
6. አቶ አህመድ ሽዴ
7. ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
8. ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)
9. ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ
10. ኢ/ር ሃብታሙ ተገኝ
11. አለሙ ስሜ (ዶ/ር)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia የሚኒስትሮች ሹመት ፀደቀ። ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህ/ ተ/ም/ቤት ያቀረቧቸው ዕጩ ሚኒስትሮች በሙሉ ድምጽ ፀድቀዋል። በዚህም መሰረት፦ 1. አቶ ተመስገን ጥሩነህ - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር 2. ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር 3. አቶ አዲሱ አረጋ (ዶ/ር) - የግብርና ሚኒስትር 4. ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) - የገንዘብ ሚኒስትር 5. አቶ መሃመድ እድሪስ - የመከላከያ ሚኒስትር…

" ሚኒስትሮች እና ሚኒስትር ዴኤታዎች ከፍተኛ ሚስጥራዊ ክትትል ሲደረግባቸው ነበር ! " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ስለ ሹም ሽሩ ምን አሉ ?
" ሌብነትን በሚመለከት ሁሉም ሚኒስትሮች እና ሚኒስትር ዴኤታዎች ቢያንስ ላለፈው አንድ ዓመት ከፍተኛ ሚስጥራዊ ክትትል ሲደረግባቸው ነበር።
በኢንተለጀንስ የተደገፈ፣ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ያላቸው እንቅስቃሴ ፣ በልጆቻቸው፣ በሚስቶቻቸው፣ በአጎቶቻቸው ፣ ከሚገናኟቸው ሀብታሞች ጋር በሙሉ የመረጃ ክትትል ይደረግባቸው ነበር። በዚያ መሰረት ሲሪየስ ግምገማዎች አድርገናል። ዝም ብሎ አይደለም ሹም ሽሩ የተደረገው።
አንድ ሚኒስትር እራሱ ሌባ ላይሆን ይችላል። በአካባቢው ያለውን ሌብነት የመቆጣጠር በአካባቢው ያለውን ሌብነት ጥቆማ ሲሰጠው እንደ ግብአት ወስዶ የመፈተሽ ' አትድረሱብኝ ፣ አትንኩኝ እኔ አካባቢ ' ከሚል እሳቤ አለመውጣትም ጭምር የዚያ መመዘኛ አንዱ አካል ነበር።
ክትትል ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ ግለሰብ መጥቶ በሚታማበት ፣ በሚጠረጠርበት ጉዳይ እራሱን እንዲከላከል ተገምግሟል።
- ' ትጠረጠራለህ '
- ' ትጠጣለህ '
- ' ሀብታሞች ጋር ያልተገባ ግንኙነት አለህ '
- ' ደጋፊ ሳይሆን ትሻጠራለህ '
- ' በውስጥ አትከታተልም '
- ' ቢሮ አትገኝም '
ሰው እራሱን ዲፌንድ አድርጓል / ተከላክሏል።
አንዳንዱ ስሞታ፣ ወቀሳ ብቻ ሊሆን ይችላል አንዳንዱ ደግሞ በቂ ኢቪደንስ/ማስረጃ ያልተገኘባቸው ሊሆን ይችላል ፤ ምንም አይነት የጥርጣሬ ዝንባሌ ያለባቸውን ግን በነሱም ይሁን በአካባቢያቸው የካቢኔ አባላት አላደረግናቸውም።
ያ ጉዳይ ተገምግሞ ተፈትሾ ከዚያ በኋላ ቢያንስ አንድ ወር አንድ ወር ተኩል በጣም ሲሪየስ የሆነ ስልጠና ነበር በዚህ ስልጠና ውስጥ ተደጋጋሚ ፈተናዎች ነበሩ። ባለፉት 2 ወራት ሚኒስትሮች 2 ሰዓት እና 3 ሰዓት በላይ ተኝንተው አያውቁም።
የተሰጠን ኃላፊነት ትልቅ ነው ፤ የሚጠበቅብን ነገር ትልቅ ነው። በመድከም ብቻ ነው የምናሳካው የሚል እምነት ነው ያለው።
ሚኒስትሮች እውነት ለመናገር ከፊታቸው የሚጠብቃቸው የስቃይ ዘመን ነው። መተኛት ፣ ማላገጥ የሚባል ነገር አይፈቀድም። መስራት ካልሰራን ደግሞ መውጣት። "

ተጨማሪ ሹመቶሽ ተሰጡ።
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የተለያዩ ተጨማሪ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡
በዚህም መሰረት ፡-
1) አቶ አደም ፋራህ በም/ጠ/ሚ ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ አስተባባሪ
2) አምባሳደር በትረ መንግስቱ የጠ/ሚ ፅ/ቤት ሃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር
3) ወ/ሮ እናትአለም መለሰ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር
4) አቶ ፍቃዱ ተሰማ የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር

የሚኒስትሮች ሹመት ፀደቀ።
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህ/ ተ/ም/ቤት ያቀረቧቸው ዕጩ ሚኒስትሮች በሙሉ ድምጽ ፀድቀዋል።
በዚህም መሰረት፦
1. አቶ ተመስገን ጥሩነህ - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
2. ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
3. አቶ አዲሱ አረጋ (ዶ/ር) - የግብርና ሚኒስትር
4. ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) - የገንዘብ ሚኒስትር
5. አቶ መሃመድ እድሪስ - የመከላከያ ሚኒስትር
6. ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) - የትምህርት ሚኒስትር
7. ወ/ሮ ሃና አርአያሥላሴ - የፍትሕ ሚኒስትር
8. ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
9. ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር) - የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
10. ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) - የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር
11. መቅደስ ዳባ (ዶ/ር) - የጤና ሚኒስትር
12. አቶ አወሉ አብዲ- የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
13. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ - የገቢዎች ሚኒስትር
14. አቶ በረከት ፍስሃጽዮን - የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር
15. ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ- የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር
16. ወ/ሮ ዓለምጸሃይ ጳውሎስ - የማዕድን ሚኒስትር
17. አቶ ሳዳት ነሻ - የሎጂስቲክስ ሚኒስትር
18. ወ/ሮ ሻዊት ሻንካ - የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
19. አቶ ሙሳ አደም - የሰላም ሚኒስትር
20. ወ/ሮ ፍሬሕይወት ታምሩ - የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
21. መሃመድ አብዱራሃማን (ኢ/ር) - የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር
22. ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) - የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር
23. አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር) - የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።

3 days ago
ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት
8ኛ ዙር የእንግሊዘኛ ቋንቋ ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን። የስልጠናው ይዘቶች:
👉 English Grammar
👉 Professional English Speaking & Pronunciation
👉 Business & Workplace Communication
👉 Professional Writing & Email Etiquette
👉 Listening & Comprehension Skills
👉 Public Speaking & Presentation Skills
👉 Interview Preparation & Confidence Building
👉 Conversational Fluency Practice
ስልጠናዎቹ በሶስት ደረጃ ተከፍለው መሰረታዊ (A1 and A2)፣ ማዕከላዊ (B1 and B2) እና በከፍተኛ ደረጃ (C1 and C2) ተብሎ የሚሰጥ ይሆናል።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ፣ ቁ.2: መገናኛ ደራርቱ ህንፃ 5ኛ ፎቅ እና ቁ.3: አዳማ ራስ ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ለመመዝገብ ድረ-ገጽ 👇 www.sageethiopia.com
Telegram: https://t.me/sagetrainingi...
8ኛ ዙር የእንግሊዘኛ ቋንቋ ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን። የስልጠናው ይዘቶች:
👉 English Grammar
👉 Professional English Speaking & Pronunciation
👉 Business & Workplace Communication
👉 Professional Writing & Email Etiquette
👉 Listening & Comprehension Skills
👉 Public Speaking & Presentation Skills
👉 Interview Preparation & Confidence Building
👉 Conversational Fluency Practice
ስልጠናዎቹ በሶስት ደረጃ ተከፍለው መሰረታዊ (A1 and A2)፣ ማዕከላዊ (B1 and B2) እና በከፍተኛ ደረጃ (C1 and C2) ተብሎ የሚሰጥ ይሆናል።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ፣ ቁ.2: መገናኛ ደራርቱ ህንፃ 5ኛ ፎቅ እና ቁ.3: አዳማ ራስ ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ለመመዝገብ ድረ-ገጽ 👇 www.sageethiopia.com
Telegram: https://t.me/sagetrainingi...
3 days ago
" ከዚህ ቀደም በነበረ ጦርነት ወቅት የኤርትራ ወታደሮችን አልባሳትና ተሽከርካሪዎቻቸውን ስለምናውቅ በቀላሉ ለመለየት ችለናል " - ነዋሪዎች
የ2013ቱን የትግራይ ጦርነት ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ፣ ትግራይ ክልል ገብተው የነበሩትና ከዛ በኋላ የኢትዮጵያን የተለያዩ አካባቢዎች ይዘው የሚገኙ የኤርትራ (ሻዕቢያ) ወታደሮች አሁን ላይ ወደ ትግራይ ክልል ዘልቀው እየገቡ ናቸው።
ከህወሓት ጋር የተሰለፉት የሻዕቢያ ወታደሮች ትግራይ ክልል ውስጥ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ።
ቢቢሲ ዛሬ ያነጋገራቸው የዓዲግራት ነዋሪዎች ትግራይ ውስጥ ዘልቀው ገብተዋል።
" ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኤርትራ ወታደሮች ከረቡዕ መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም ማለዳ ጀምሮ በዓዲግራት በኩል ወደ ሌሎች የትግራይ አካባቢዎች በጭነት ተሽከርካሪዎችና በእግራቸው ሲያቋርጡ ተመልክተናል " ብለዋል።
ነዋሪዎች ከኤርትራ ድንበር 40 ኪሎ ሜትር የምትርቀውን ዓዲግራት ከተማን በማለፍ የኤርትራ ወታደሮች ወደ መቐለ አቅጣጫ ሲጓዙ ማየታቸውን ገልጸዋል።
" ወታደሮቹ በጭነት መኪኖችና በእግራቸው ወደ መቐለ መስመር ወዳለችው እዳጋ ሐሙስ አልፈው ሲሄዱ ተመልክተናል " ብለዋል።
በአካባቢው የትግራይም ሆነ የፌደራሉ መንግሥት ሠራዊት አባላት ባለመኖራቸውና ከዚህ ቀደም በነበረው ጦርነት ወቅት የኤርትራ ወታደሮችን አልባሳትና ተሽከርካሪዎቻቸውን ስለሚያውቁ በቀላሉ ለመለየት እንደቻሉ ገልጸዋል።
ወታደሮቹ ከመኪና በተጨማሪ በእግርም የሚጓዙ ስለነበሩ ለመለየት ያልተቸገሩት ነዋሪዎቹ፣ ነጣ ያለ እና ቅጠልያ ወደታራዊ ልብስ የለበሱ ናቸው።
" መኪኖቻቸው ሲኖ የሚመስሉ የጭነት መኪኖች እና የኤርትራ የሰሌዳ ቁጥር ያላቸው ናቸው " ብለዋል።
በቀደሙት ቀናት ከኤርትራ ተነስተው በዛላምበሳ በኩል ፋጺ ወደሚባል አካባቢ የኤርትራ ወታደሮች መግባታቸውን ሲሰሙ እንደነበርም አመልክተዋል። ዛሬ ደግሞ ዓዲግራትን ሲተልፉ ነበር።
ነዋሪዎቹ ወታደሮቹን ጭነው የገቡት የጭነት መኪኖች "በግምት ከ40 በላይ" እንደሚሆኑና በእግር ሲጓዙ የነበሩት "ብዙ" መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
አንድ የዓዲግራት ከተማ ባለሥልጣን ስማቸው ሳይጠቀስ ለኤኤፍፒ እንደተናገሩት፣ የኤርትራ ወታሮች ለቀናት በአካባቢው እንደነበሩና " ሕዝቡ ስጋት እንደተፈጠረበት " ገልጸዋል።
አንድ የዐይን ምስክር ደግሞ " በትላልቅ የጭነት መኪኖች፣ በክፍት መኪኖች እና በሌሎች ተሽከርካሪዎች የተጫኑ የኤርትራ ወታሮች ከከባድ መሣሪያዎች ጋር " ከዓዲግራት በስተደቡብ እያመሩ መሆናቸውን ለኤኤፍፒ ተናግረዋል።
በተመሳሳይ ሮይተስ ያነጋገራቸው የዓዲግራት ነዋሪዎች በከተማዋ በኩል በሁለት የጭነት መኪኖች የተጫኑ በርካታ የኤርትራ ወታደሮችን ረቡዕ ጠዋት ማየታቸውን ገልጸዋል።
ለሮይተርስ ቀላቸውን የሰጡ የታጠቁ ግጭቶች ቦታና ክስተቶች መረጃ ፕሮጀክት (ACLED) የምስራቅ አፍሪካ ባለሙያ የኤርትራ ኃይሎች በዛላምበሳ በኩል ድንበር አልፈው ዓዲግራት መድረሳቸውን ገልጸዋል። እንደ ባለሙያው ገለጻ፣ የኢትዮጵያ ጦር እነዚህ ወታደሮችን የጫኑ ተሽከርካሪዎችን በጉዋዳ አካባቢ በድሮን መምታቱን ተናግረዋል።
የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የሆኑት የማነ ገብረመስቀል ፤ የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ድንበር ተሻግረው ተገኝረዋል መባሉን ውድቅ አድርገዋል።
በከዚህ ቀደሙ ጦርነት ወቅትም ኤርትራ ሰራዊቷ በኢትዮጵያ እንደሌለ፣ ጦሯ የሚወነጀልባቸውን ግፎች እንዳልፈጸመ በተደጋጋሚ ስትክድ እነደነበር የሚዘነጋ አይደለም።
ቢቢሲ፣ ሮይተርስ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia የዓዲግራት ከተማ ነዋሪዎች የኤርትራ (ሻዕቢያ) ጦር ሠራዊት ወደ ከተማቸው እንደገባ አሳወቁ። የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ምድር፣ ትግራይ ክልል ወደ ምትገኘው የዓዲግራት ከተማ መግባቱን ነዋሪዎች ለጀርመን ድምጽ ሬድዮ ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ ፥ ወታደሮቹ ወደ መቐለ መስመር / አቅጣጫ ሲያመሩ እንደተመለከቱ ገልጸዋል። በመቐለ ከተማ የሚገኙ የመረጃ ምንጭ የኤርትራ ወታደሮች " በበርካታ ከባድ ተሽከርካሪዎች…

ኢትዮጵያ ኤርትራን ወራር በመፈጸም የከሰሰች ሲሆን ወታደሮቿ በአስቸኳይ የኢትዮጵያን ምድር ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።
የኤርትራ ወታደሮች ወደ ሉዓላዊ የኢትዮጵያ ግዛት መግባታቸውን ኢትዮጵያ አሳውቃለች።
እነዚህ የኤርትራ ኃይሎች በአስቸኳይ ከሀገሪቱ ግዛት እንዲወጡ አስጠንቅቃለች።
ለ ' ብሉምበርግ ' ቃላቸውን የሰጡት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትአለም መለሰ፣ " በሉዓላዊ ግዛታችን ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሁሉም የውጭ ኃይሎች በአስቸኳይ ሊወጡ ይገባል " ብለዋል።
በተለይም በትግራይ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የኤርትራ ኃይሎች የኢትዮጵያን ግዛት ሳይዘገዩ በፍጥነት ለቀው መውጣት እንዳለባቸው አስጠንቅቀዋል።

Comments