Logo
TIKVAH-ETHIOPIA
🚧

ከጎሮ አደባባይ-ኮዬ ፈጬ- ቱሉ ድምቱ አደባባይ በሚወስደው መንገድ የኮሪደር መሰረተ ልማት እየተከናወነ ሲሆን አይሲቲ ፓርክ አካባቢ በመሬት ውስጥ ለሚቀበሩ የመሰረተ ልማት ስራዎች ዝርጋታ ሲባል ዋናው አስፋልት መንገድ የተቋረጠ መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አሳውቋል።

በዚህ ምክንያት የትራፊክ መዘጋጋት እንዳጋጠመ ተገልጿል።

ከዛሬ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ፡-

👉 ከጎሮ አደባባይ ወደ ኮዬ ፈጬ አደባባይ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች ፣ በጎሮ - ቦሌ ኤርፖርት መንገድ አቅጣጫ ወደ ቡልቡላ በመጓዝ ወደ ኮዬ ፈጬ እና አካባቢው፤

👉 ከኮዬ ፈጬ ወደ ጎሮ አደባባይ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች ደግሞ ፤ ከኮዬ ፈጬ አደባባይ -  በቡልቡላ በኩል ወደ ጎሮ አደባባይ የሚወስደውን የቦሌ ኤርፖርት - ጎሮ አዲሱን መንገድ እና ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልክዕክት ተላልፏል።

መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
3 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.