Logo
TIKVAH-ETHIOPIA
የቀድሞ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በአፋር ክልል ሹመት ተሰጣቸው።

የክልሉ ፕሬዜዳንት ሀጂ አወል አርባ፣ ኢንጂነር አይሻ መሀመድን የአፋር ክልል የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ኃላፊ አድርገው ሹመዋል።

ኢ/ር አይሻ የመጀመሪያዋ ሴት የሀገር መከላከያ ሚኒስትር እንዲሁም በተለያዩ የፌዴራል መስሪያ ቤቶች ውስጥ በአመራርነት አገልግለዋል።

ትላንትና በነበረው የሚኒስትሮች ካቢኔ ሹመት ውስጥ ያልተካተቱ የቀድሞዋ ሚኒስትር ወደ ክልል አምርተዋል።

በሌላ በኩል፤ ፕረዚዳንት ሃጂ አወል አርባ ዛህራ ሁመድ አሊን የክልሉ የውሃና ኢነርጂ ቢሮ የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አድርገው ሾመዋል።

#tikvahethiopia
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
19 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.