እነማን ተሾሙ ?
በዛሬው ዕለት ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚኒስትር ዴኤታነት ከሾሟቸው መካከል የቀድሞ የህወሓት አመራር እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ይገኙበታል።
ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም የሴቶችና የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተሹመዋል።
ሌላው፥ የኢዜማው መሪ አቶ እዮብ መሳፍንት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሹመዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት ፣ ከዛ በፊት በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ፣ በብሔራዊ መረጃና ደህነትም አመራር ሆነው ያገለገሉት እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር) የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ተደርገዋል።
ሌላው በሲዳማ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ አብርሃም ማርሻሎ የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሹመዋል።
የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) በፌዴራል ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሹመዋል።
ሌላው የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በነበረበት ወቅት ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት አቶ በረሆ ሀሰን የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ተደርገዋል።
የፋይዳ ቨርስ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ዮዳሄ አርአያስላሴ የቀድሞ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በሚመሩት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታነት ተሹመዋል።
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #ሹመት በዛሬው ዕለት 62 አመራሮችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚኒስትር ዴዔታነት ሾመዋል። (የተሿሚዎች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል) መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

1 day ago