" ሚኒስትሮች እና ሚኒስትር ዴኤታዎች ከፍተኛ ሚስጥራዊ ክትትል ሲደረግባቸው ነበር ! " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ስለ ሹም ሽሩ ምን አሉ ?
" ሌብነትን በሚመለከት ሁሉም ሚኒስትሮች እና ሚኒስትር ዴኤታዎች ቢያንስ ላለፈው አንድ ዓመት ከፍተኛ ሚስጥራዊ ክትትል ሲደረግባቸው ነበር።
በኢንተለጀንስ የተደገፈ፣ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ያላቸው እንቅስቃሴ ፣ በልጆቻቸው፣ በሚስቶቻቸው፣ በአጎቶቻቸው ፣ ከሚገናኟቸው ሀብታሞች ጋር በሙሉ የመረጃ ክትትል ይደረግባቸው ነበር። በዚያ መሰረት ሲሪየስ ግምገማዎች አድርገናል። ዝም ብሎ አይደለም ሹም ሽሩ የተደረገው።
አንድ ሚኒስትር እራሱ ሌባ ላይሆን ይችላል። በአካባቢው ያለውን ሌብነት የመቆጣጠር በአካባቢው ያለውን ሌብነት ጥቆማ ሲሰጠው እንደ ግብአት ወስዶ የመፈተሽ ' አትድረሱብኝ ፣ አትንኩኝ እኔ አካባቢ ' ከሚል እሳቤ አለመውጣትም ጭምር የዚያ መመዘኛ አንዱ አካል ነበር።
ክትትል ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ ግለሰብ መጥቶ በሚታማበት ፣ በሚጠረጠርበት ጉዳይ እራሱን እንዲከላከል ተገምግሟል።
- ' ትጠረጠራለህ '
- ' ትጠጣለህ '
- ' ሀብታሞች ጋር ያልተገባ ግንኙነት አለህ '
- ' ደጋፊ ሳይሆን ትሻጠራለህ '
- ' በውስጥ አትከታተልም '
- ' ቢሮ አትገኝም '
ሰው እራሱን ዲፌንድ አድርጓል / ተከላክሏል።
አንዳንዱ ስሞታ፣ ወቀሳ ብቻ ሊሆን ይችላል አንዳንዱ ደግሞ በቂ ኢቪደንስ/ማስረጃ ያልተገኘባቸው ሊሆን ይችላል ፤ ምንም አይነት የጥርጣሬ ዝንባሌ ያለባቸውን ግን በነሱም ይሁን በአካባቢያቸው የካቢኔ አባላት አላደረግናቸውም።
ያ ጉዳይ ተገምግሞ ተፈትሾ ከዚያ በኋላ ቢያንስ አንድ ወር አንድ ወር ተኩል በጣም ሲሪየስ የሆነ ስልጠና ነበር በዚህ ስልጠና ውስጥ ተደጋጋሚ ፈተናዎች ነበሩ። ባለፉት 2 ወራት ሚኒስትሮች 2 ሰዓት እና 3 ሰዓት በላይ ተኝንተው አያውቁም።
የተሰጠን ኃላፊነት ትልቅ ነው ፤ የሚጠበቅብን ነገር ትልቅ ነው። በመድከም ብቻ ነው የምናሳካው የሚል እምነት ነው ያለው።
ሚኒስትሮች እውነት ለመናገር ከፊታቸው የሚጠብቃቸው የስቃይ ዘመን ነው። መተኛት ፣ ማላገጥ የሚባል ነገር አይፈቀድም። መስራት ካልሰራን ደግሞ መውጣት። "
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia Photo

2 days ago