Logo
TIKVAH-ETHIOPIA
#mekelle📍

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወደ መቐለ ከተማ ገብቶ ስምሪት ወስዶ የሰላም፣ የጸጥታና ማረጋጋት ሥራዎችን መስራት መጀመሩ ተሰምቷል።

አሶሼትድ ፕሬስ (AP) እንደዘገበው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የመቐለ ነዋሪዎች ፣ የከተማዋን ሰላምና መረጋጋት ወደነበረበት ለመመለስ እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርቧል።

ፖሊስ አዲስ አስተዳደር አዲቋቋም ለሚሰራው የማረጋጋት እና ጸጥታ የማስፈን ስራ ነዋሪዎች እንዲተባበሩ በድምፅ ማጉያ ጥሪ እንዳቀረበ ተዘግቧል።

መቐለ በአሁኑ ጊዜ አዲስ ባለስልጣናትን እየጠበቀች ሲሆን ዛሬም በከተማዋ የመንግስት ቢሮዎች ተዘግተው እንደዋሉ ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

የፌደራል ፖሊስ እና የትግራይ የሰላም ሃይል ፤ የመቐለ ከተማ ፀጥታን እየጠበቁ ናቸው። 

ይህን በእንዲህ እንዳለ ነዋሪዎች ዛሬ በሰጡን ቃል ፤ በከተማው የፌዴራል ፖሊስ መሰማራቱን አረጋግጠው የከተማዋ ትራፊክ ፖሊስ አባላት ሪፖርት አድርገው ወደመደበኛ ሥራ መግባታቸውን አመልክተዋል።

ሌሎች ቢሮዎችም ከሰኞ ጀምሮ ሪፖርት እያደረጉ እንዲገቡ ጥሪ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የፌዴራል ፖሊስ የአውሮፕላን ማረፊያውን ጨምሮ ትልልቅ መንግሥታዊ ተቋማትን የመጠበቅ ኃላፊነት እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ/ም።

@tikvahethiopia Photo
12 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.