"አፍሪካ የሚያስፈልጋት ነፃና ገለልተኛ ተቋም ነው"
#ethiopia | አፍሪካ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ነፃነቷ የሚከበረው ጠንካራና ገለልተኛ ተቋማት ስትገነባ ብቻ ነው ሲሉ የፓን አፍሪካ አቀንቃኝ የሆኑት ፖሮፌሰር ተናገሩ።
የፓን አፍሪካ ሀሳብ አቀንቃኝ የሆኑት ፕሮፌሰር ሉሙሙባ አፍሪካውያን ጠንካራና ገለልተኛ አህጉራዊ ተቋማትን መገንባት ካልቻሉ የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ ነፃነታቸው ሙሉ በሙሉ ሊከበር እንደማይችል ገለፁ።
ምሁሩ አህጉሪቱ አሁንም ድረስ በውጭ ሀገራት የኢኮኖሚና የፖለቲካ ተፅዕኖ ስር የምትገኘው የራሷን የነፃነት የፍትህና የልማት ተቋማት በበቂ ሁኔታ ባለመገንባቷ እንደሆነ አስገንዝበዋል።
ምሁሩ አፍሪካ የራሷን ችግር በራሷ አቅም የምትፈታበትና መብቷን የምታስከብርበት ጠንካራ ተቋም ከሌላት የስም ነፃነት ብቻውን ትርጉም አይኖረውም ብለዋል።
የውጭ ሀገራት ጣልቃ ገብነት የሚያበቃው አፍሪካውያን በጋራ የተመሰረቱና የህዝቦቻቸውን ጥቅም የሚያስጠብቁ ተቋማትን ሲገነቡ ብቻ ነው።
ዘላቂ ነፃነትና እድገት ለማረጋገጥ የአፍሪካ ህብረትና ቀጣናዊ ተቋማት ከጥገኝነት ተላቀው በራሳቸው እግር መቆም አለባቸው ነው ያሉት።
አፍሪካውያን መብቶቻቸውን ለማስከበርና የወደፊት እጣ ፈንታቸውን በራሳቸው ለመወሰን የተቋማት ግንባታን ቀዳሚ ተግባራቸው ሊያደርጉት እንደሚገባ ምሁሩ አሳስበዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #africa #institution #freedom #economy #political #policy #panafricanist

2 months ago