Logo
Getu Temesgen
የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ቡድን በዓለም ሻምፒዮና ላይ ደማቅ ድል አስመዘገበ

‎#ethiopia | ​በደቡብ ኮሪያ ጊምቺዮን ከተማ ከሐምሌ 3 እስከ 6 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው የዓለም ሻምፒዮና ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ብሔራዊ ቡድን፣ በአጠቃላይ ዘጠኝ ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ታሪካዊ ውጤት አስመዝግቧል።

‎ከ46 አገራት የተውጣጡ ከ2 ሺህ በላይ ስፖርተኞች በተሳተፉበት በዚህ ጠንካራ ውድድር ላይ፣ ለአምስት ወራት ያህል ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው የሀገራችን ስብስብ ባሳየው አስደናቂ ብቃት የኢትዮጵያን ስም በዓለም አደባባይ ከፍ ማድረግ ችሏል።

‎​የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ እና የልዑኩ መሪ ኢንተርናሽናል ኢንስፔክተር ማስተር ኤልያስ ኩመል እንደገለጹት፣ ውድድሩ እጅግ ፈታኝና አድካሚ የነበረ ቢሆንም ካደረጉት ጥልቅ ዝግጅት አንጻር የተጠበቀውን ስኬት ማምጣት ተችሏል።

‎ቡድኑ በአራት ተወዳዳሪዎች ብቻ በኢንተርናሽናል እና በኮፖት ቴኳንዶ የውድድር ዘርፎች የቀረበ ሲሆን፣ ሁሉም ተሳታፊዎች በየምድባቸው ሜዳሊያ ውስጥ መግባት ችለዋል። በዚህም ቡድኑ ሁለት የወርቅ፣ ሦስት የብር እና አራት የነሐስ ሜዳሊያዎችን በድምሩ ማሸነፍ ችሏል።

‎Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

‎#getutemesgen #getu #ጌጡ

‎#ethiopia #taekwondo #worldchampionship #gimcheon2026 #teamethiopia #ethiopiansports



25 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.