አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የረዳት ኮሚሽነርነት ከፍተኛ የማዕረግ ዕድገት ተሰጣት
#ethiopia | ታዋቂዋ እና ተወዳጇ የረጅም ርቀት አትሌት ኮማንደር ጥሩነሽ ዲባባ የረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረግ ተሸላሚ ሆናለች።
ይህ የሹመት መርሃ ግብር የተከናወነው የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የስፖርት ክለብ እንዲሁም የሙዚቃና ቴአትር ቡድን የተመሰረተበትን 40ኛ ዓመት በዓል ባከበረበት ወቅት ነው።
በዛሬው ዕለት ሰኔ 6 ቀን 2018 ዓ.ም በአድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደው የክብር ስነ ሥርዓት ላይ የፍትህ ሚኒስትሯ ሀና አርዕያ ስላሴን ጨምሮ በርካታ የሀገር መሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የስፖርትና የኪነጥበብ ዘርፍ ተወካዮች ታድመዋል።
ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ላይ የሀገሯን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጋ ያወለበለበች መሪ አትሌት ናት።
በአራት የኦሎምፒክ መድረኮች ላይ በመሳተፍ 3 የወርቅ እና 1 የነሀስ ሜዳሊያዎችን ያስመዘገበች ሲሆን በአጠቃላይ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ከ15 በላይ የወርቅ ሜዳሊያዎችን ለሀገሯ በማበርከት ስሟ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ጀግና ናት።
ይህ አሁን የተሰጣት የረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረግ በተቋሙ ውስጥ የሚሰጥ ከፍተኛ የማዕረግ ዕድገት መሆኑ ተገልጿል።
በዚሁ ታላቅ መርሃ ግብር ላይ ከጥሩነሽ ዲባባ በተጨማሪ ለሌሎች የሀገር ባለውለታ የሆኑ አንጋፋ ስፖርተኞች እና የኪነጥበብ ባለሙያዎች የዕውቅና እና የሽልማት ስነ ሥርዓት ተካሂዶላቸዋል።
በዚህም መሰረት በአትሌቲክስ ታሪክ የመጀመሪያዋ ጥቁር አፍሪካዊት የኦሎምፒክ አሸናፊ የሆነችው ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፣ የማራቶን ጀግናዋ ኮማንደር ፋጡማ ሮባ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንትና የሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ እንዲሁም የሦስት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ባለቤቱ አትሌት ስለሺ ስህን፣ ኮማንደር ሰለሞን ባረጋ እና ምክትል ኮሚሽነር ሰንበሬ ተፈሪ የክብር ሽልማታቸውን ተቀብለዋል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ውስጥ ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ በማሰልጠን ያገለገለው፣ በ7 ኦሎምፒክ እና በ12 የዓለም ሻምፒዮናዎች ላይ በመሳተፍ በርካታ ስኬታማ አትሌቶችን ያፈራው አዳኙ አሰልጣኝ ረዳት ኮሚሽነር ሁሴን ሸቦ የኒሻን ሽልማት ተበርክቶለታል።
በኪነጥበብ ዘርፍም የኮሚሽኑ የሙዚቃና ቴያትር ቡድን አባላት የነበሩት ድምፃዊ ደመረ ለገሰ፣ ድምፃዊ ተፈራ ነጋሽ፣ ድምፃዊ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ እንግዳ፣ አርቲስት ፍሬህይወት ስዩም፣ ሳክስፎኒስት ዘሪሁን በለጠ እና ሌሎች ባለሙያዎች ላበረከቱት አስተዋጽኦ ተገቢው ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።
#tiruneshdibaba #athletics #sport #ethiopianathletics #news #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

1 day ago