Logo
Getu Temesgen
የፕሬዚዳንት ኪም ትዕዛዝ
#ethiopia | ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን በደቡባዊ የአገራቸው ድንበር መከላከያው እንዲጠናከር ትዕዛዝ ሰጡ።

ከሰሜን ኮሪያ የተለያዩ ዕዞች ከተውጣጡ ወታደራዊ ሀላፊዎች ጋር ስለዝግጁነት መክረዋል ኪም ጆንግ ኡን።

ከዕዝና ብርጌድ አዛዦች ጋር የተወያዩት ኪም በደቡባዊ የሰሜን ኮሪያ ክፍል ያለው ድንበር ላይ ዝግጅት እንዲደረግ ማሳሰባቸው ለደቡብ ኮሪያ ፖለቲከኞች አዲስ ወታደራዊ ስጋት ጋርጦባቸዋል ።

ሊቀሰቀስ የሚችልን ማንኛውንም ጦርነት ለመቀልበስ የጦሩን ትጥቅ ማዘመን፣ቁልፍ ዕዞችን ማጠናከር እና መሰል ዝግጅቶች እንዲደረጉም ጥሪ ቀርቧል።

በደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ መካከል ያለው ወታደራዊ ትስስር ስጋት የሆነባቸው ኪሞቹ በተለያየ ጊዜ የሚፈፀምብንን ወታደራዊ ትንኮሳ መመከት አለብን የሚል ዕምነት አላቸውም ተብሏል።

በፒዮንግያንግ እና ሴዑል መካከል ያለው ወታደራዊ ውጥረት መልኩን እየለወጠ መምጣቱን የሚጠቁም ትዕዛዝ ሆኖም ተመዝግቧል።

ኪም ጆንግ ኡን አዳዲስ የጦር መሳሪያ ስርዓቶች ወደ ውጊያ አውድ እንዲገቡ ተደጋጋሚ ማሳሰቢያ መስጠታቸውም አይዘነጋም።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #nbcethiopia #skorea #leader #sk

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.