5 months ago
የፕሬዚዳንት ኪም ትዕዛዝ
#ethiopia | ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን በደቡባዊ የአገራቸው ድንበር መከላከያው እንዲጠናከር ትዕዛዝ ሰጡ።
ከሰሜን ኮሪያ የተለያዩ ዕዞች ከተውጣጡ ወታደራዊ ሀላፊዎች ጋር ስለዝግጁነት መክረዋል ኪም ጆንግ ኡን።
ከዕዝና ብርጌድ አዛዦች ጋር የተወያዩት ኪም በደቡባዊ የሰሜን ኮሪያ ክፍል ያለው ድንበር ላይ ዝግጅት እንዲደረግ ማሳሰባቸው ለደቡብ ኮሪያ ፖለቲከኞች አዲስ ወታደራዊ ስጋት ጋርጦባቸዋል ።
ሊቀሰቀስ የሚችልን ማንኛውንም ጦርነት ለመቀልበስ የጦሩን ትጥቅ ማዘመን፣ቁልፍ ዕዞችን ማጠናከር እና መሰል ዝግጅቶች እንዲደረጉም ጥሪ ቀርቧል።
በደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ መካከል ያለው ወታደራዊ ትስስር ስጋት የሆነባቸው ኪሞቹ በተለያየ ጊዜ የሚፈፀምብንን ወታደራዊ ትንኮሳ መመከት አለብን የሚል ዕምነት አላቸውም ተብሏል።
በፒዮንግያንግ እና ሴዑል መካከል ያለው ወታደራዊ ውጥረት መልኩን እየለወጠ መምጣቱን የሚጠቁም ትዕዛዝ ሆኖም ተመዝግቧል።
ኪም ጆንግ ኡን አዳዲስ የጦር መሳሪያ ስርዓቶች ወደ ውጊያ አውድ እንዲገቡ ተደጋጋሚ ማሳሰቢያ መስጠታቸውም አይዘነጋም።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #nbcethiopia #skorea #leader #sk

6 months ago
ሳካ ከኤምሬትስ ጣራ ስር
#ethiopia | የመድፈኞቹ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ሳካ ወደ ልምምድ መመለሱ ለቡድኑ ትልቅ አቅም እንደሚሆን ገልጸዋል። ኮከቡ በካራባኦ ዋንጫ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ከተደረገው ጨዋታ ጀምሮ በጉዳት ምክንያት ከሜዳ ርቆ የቆየ ቢሆንም፣ አሁን ግን ለጨዋታ ዝግጁ መሆኑን አሰልጣኙ አረጋግጠዋል።
አርቴታ "ለሳካ ትክክለኛውን የእረፍት እና የህክምና ጊዜ ሰጥተነዋል። አሁን ግን ቡድኑ በከፍተኛ ሁኔታ ይፈልገዋል፤ መመለሱም ለእኛ መልካም ዜና ነው" ብለዋል።
ምንም እንኳን ሳካ በዚህ የውድድር ዘመን በሁለት የተለያዩ ጉዳቶች ቢፈተንም፣ ካለፉት 32 የሊግ ጨዋታዎች በ27ቱ ላይ በመሰለፍ የቡድኑ የጀርባ አጥንት መሆኑን አስመስክሯል።
የሌሎች ተጫዋቾች ሁኔታ
ሪካርዶ ካላፊዮሪ፦ ጣሊያናዊው ተከላካይ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ከስፖርቲንግ ሊዝበን ጋር ከተደረገው ጨዋታ በኋላ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ ተነግሯል።
ጁሪየን ቲምበር፦ ለደጋፊዎች ጥቂት የማይዋጥ ዜና፣ ኔዘርላንዳዊው ተከላካይ ቲምበር አሁንም ከጉዳቱ ባለማገገሙ የነገው ጨዋታ እንደሚያመልጠው ታውቋል። ቲምበር ካለፉት ሰባት ጨዋታዎች ውጪ መሆኑ ይታወሳል።
አርሰናል ዛሬ ምሽት 1:30 ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ኒውካስልን ያስተናግዳል። ይህ ጨዋታ ለመድፈኞቹ እጅግ ወሳኝ ነው፤ ጨዋታውን ማሸነፍ ከቻሉ የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት ዳግም ለመረከብ ትልቅ እድል ይፈጥርላቸዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#nbcethiopia #ethiopia #arsenal #premierleague #bukayosaka #mikelarteta #coyg

11 months ago
📌 የግብጽ ናሽናል ኢንተረስት ፤ ኢትዮጵያ ናሽናል ኢንተረስት እንዳይኖራት ማድረግ ነው
📌 ኦሮሚያ ውስጥ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት ያለፈውን ስርዓት ከሆነ የሚጠይቁት ... ሄደዋል
ጊዜ ግስ ከ ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ ጋር
ዛሬ ምሽት 1:00 ላይ በኤንቢሲ ኢትዮጵያ ቲቪ እና በማህበራዊ የትስስር ገፆቻችን ላይ ይጠብቁን።
። ። ።
ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) በመጫን NBC ኢትዮጵያን ይጎብኙ ይወዳጁ
https://linktr.ee/NBCEthio...
#nbcethiopia #ሆኖ_መገኘት #ethiopia

Comments