Logo
Getu Temesgen
አቶ ገብረማርያም ይርጋ ዓለም አቀፍ የክብር ሽልማት ሊሰጣቸው ነው!
#ethiopia | በባህል አስተዳደር፣ በኪነ ጥበብ አመራር እና በዘርፉ ዲፕሎማሲያዊ ስራዎች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱት አቶ ገብረማርያም ይርጋ በታይላንዱ APA International Professional Management Award ተሸላሚ ሊሆኑ ነው።

ግለሰቡ በፈጠራ እና በዓለም አቀፍ የባህል ልውውጥ ረገድ ላሳዩት የላቀ አፈጻጸም ይህ እውቅና እንደተሰጣቸው ተገልጿል።

አቶ ገብረማርያም ላለፉት 15 ዓመታት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲሁም በአማራ ክልል ባህል ኪነ ጥበብና ዝክረ ታሪክ ጽ/ቤት በምክትል ኃላፊነት ውጤታማ ስራዎችን ሲያከናውኑ ቆይተዋል።

በቅርቡ ደግሞ በደቡብ ኮሪያ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የባህልና ኪነ ጥበባት ህብረት ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን መሾማቸው የሚታወስ ነዉ።
በቅርቡ ታይላንድ ሄደዉ እዉቅናዉን የሚቀበሉ ሲሆን ለዓለም አቀፍ ስኬታቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ተላልፎላቸዋል።

እንኳን ደስ አልዎት!
#culture #award #arts #leadership #internationalaward #achievement #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.