"ማንችስተር ሲቲን የማንረታበት ምክንያት የለም" ሊያም ሮሴንየር
#ethiopia | የቼልሲው አሰልጣኝ ሊያም ሮሴንየር ቡድናቸው ከማንችስተር ሲቲ ጋር ከሚያደርገው ወሳኝ የሊግ ፍልሚያ በፊት ለተጋጣሚያቸው ያላቸውን አክብሮት ቢገልጹም፣ በድል ላይ ያላቸው እምነት ግን ፍጹም አልተናወጠም።
ሮሴንየር በሰጡት መግለጫ ላይ ያተኮሩባቸው ዋና ዋና ነጥቦች እነሆ፦
"ለፔፕ ትልቅ ክብር አለኝ፤ እሱ የማይታመንና ለሁላችንም መነሳሳት የሆነ አሰልጣኝ ነው" በማለት ለተቃራኒው ጎራ አድናቆታቸውን ችረዋል።
ምንም እንኳን ጨዋታው ከባድ ፈተና እንደሚሆን ቢገነዘቡም፣ ቡድናቸው እሁድ ዕለት በሜዳ ላይ ምን መስራት እንደሚችል ለማሳየት በጉጉት እንደሚጠብቁ ገልጸዋል።
አሰልጣኙ በልበ ሙሉነት "ማንችስተር ሲቲን ማሸነፍ እንችላለን" በማለት ለተጫዋቾቻቸውና ለደጋፊዎቻቸው የድል መልእክት አስተላልፈዋል።
ከዚህ ቀደም ከሲቲ ጋር የነበራቸው ሪከርድ ለአሁኑ ጨዋታ ምንም አይነት ጥቅም እንደሌለውና ትኩረታቸው በአሁኑ 90 ደቂቃ ላይ ብቻ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ሮሴንየር እና ልጆቻቸው የፔፕን ስብስብ በመግጠም ጥንካሬያቸውን ለማሳየት ቆርጠው የተነሱ ይመስላሉ። እሁድ የሚደረገው ጨዋታ የሮሴንየር ታክቲክ በሲቲ ላይ ይሰራ እንደሆነ የሚታይበት ይሆናል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#tikvahsport #getutemesgen #getu #chelseafc #mancity #liamrosenior #premierleague #footballnews #matchday #ethiopia

2 months ago