Logo
Getu Temesgen
የኢትዮጵያ የርምጃ አትሌቶች ብራዚል ገቡ

​#ethiopia | በደቡብ አሜሪካ ምድር የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ለማውለብለብ የጀግኖቹ ጉዞ ተጀምሯል!

​በብራዚል በሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ የእርምጃ ውድድር ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ጠዋት ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቷል። ቡድኑ በፌዴሬሽኑ አመራሮች ደማቅ ሽኝት ተደርጎለታል።

​ኢትዮጵያን የሚወክሉ ጀግኖች፦

​አትሌት ምስጋና ዋቁማ
በፓሪስ ኦሎምፒክ ድንቅ ብቃት ያሳየውና በ20 ኪ.ሜ የሚወዳደረው።

​አትሌት ህይወት አምባው
የአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት (በ10 ኪ.ሜ ሴቶች)።

​አትሌት አቡዱሰላም አቡዱልወሀብ፦ በድሬደዋና በአዲስ አበባ የወጣቶች ሻምፒዮና አሸናፊ (በ10 ኪ.ሜ ወንዶች)።

​ውድድሩ መጪው እሁድ በብራዚል የሚካሄድ ሲሆን፣ አትሌቶቻችን በድል ተመልሰው ሀገራዊ ኩራት እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

​ለመላው የልዑካን ቡድን መልካም ዕድል እንመኛለን!

​#getu #ethiopianathletics #racewalking #worldathletics #brazil2026 #misganawakuma #teamethiopia #sportsnews #addisababa #አትሌቲክስ #እርምጃ #ኢትዮጵያ #ብራዚል #ጌጡተመስገን #getutemesgen

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.