የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ አረንጓዴ አሻራን ተቀላቀሉ
📌 ዢ ጂንፒንግ "ውብና አረንጓዴ ቻይናን" ለመገንባት የችግኝ ተከላ ጥሪ አቀረበዋል
#ethiopia | የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ መላው የሀገሪቱ ዜጋ በአረንጓዴ አሻራ እና በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሮች ላይ በነቃ ሁኔታ እንዲሳተፍ ጥሪ አቀረቡ።
ፕሬዝዳንቱ ይህንን ጥሪ ያስተላለፉት በቤጂንግ በተካሄደ የበጎ ፈቃድ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው በተሳተፉበት ወቅት ነው።
በመርሃ ግብሩ ላይ ለህዝቡ አርአያ የሚሆኑ ሀገር በቀል ችግኞችን የተከሉት ፕሬዝዳንቱ፣ የነገዋን ውብ ቻይና ለመገንባት እያንዳንዱ ዜጋ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የነገዎቹ ተረካቢዎችና የአረንጓዴው ጉዞ
በዕለቱ በተካሄደው ስነስርዓት ላይ አዳጊ ተማሪዎችም የተሳተፉ ሲሆን፣ ዢ ጂንፒንግ ከተማሪዎቹ ጋር በነበራቸው ቆይታ በስፖርት፣ በትምህርትና በተፈጥሮ ጥበቃ ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል። ፕሬዝዳንቱ ለልጆቹ በለገሱት ምክር፦
* ትልቅ ህልም እንዲኖራቸው፤
* ለትምህርትና ለስራ ትጋት እንዲኖራቸው፤
* ተፈጥሮን የሚወዱና የሚንከባከቡ
የህብረተሰቡ አለኝታ እንዲሆኑ አሳስበዋል። ቻይና በአረንጓዴ ልማት ያስመዘገበችው ስኬት
ፕሬዝዳንት ዢ እንደገለጹት፣ ቻይና ደኖችን በማስፋትና በረሃማነትን በመከላከል ረገድ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ስኬት እያስመዘገበች ትገኛለች። ይህም ሀገሪቱን በአረንጓዴ ልማት ረገድ ከአለም ቀዳሚ ተርታ እያሰለፋት መሆኑን ጠቁመዋል።
ቤጂንግ በአየር ንብረት ለውጥና በስነ-ምህዳር ጥበቃ ዙሪያ የምትከተለው ጠንካራ ህግና መመሪያ ለቀጣዩ ትውልድ የምትመችና ውብ ቻይናን ለመፍጠር መሰረት እየጣለ መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው አረጋግጠዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #china #xijinping #greendevelopment #afforestation #climateaction #sustainability #environment #globalnews

4 months ago