Logo
Getu Temesgen
የባልቻ አባ ነፍሶ ታሪካዊ ቴአትር ሊመረቅ ነው
#ethiopia | በሁለት ጦር አውድማዎች ላይ ጀብድ የሰራው ደጃዝማች ባልቻ ሳፎን ጀግንነት፣ ፍቅር፣ ሰብዓዊነትና መስዋዕትነትን የሚተርከው ባልቻ አባ ነፍሶ ታሪካዊ ቴአትር ለመድረክ ሊበቃ መሆኑ ተገልጿል።

በደራሲ ብርሃኑ ዘሪሁን ተደርሶ በዶክተር ተሻለ አሰፋ አዘጋጅነት ለመድረክ የተሰናዳው ባልቻ አባ ነፍሶ ታሪካዊ ቴአትር አንጋፋና ወጣት ተዋንያን ተሳትፈውበታል።

እንዲሁም ከአራት ወር በላይ በልምምድ መቆየቱም ታውቋል።

የቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ዘገዬ በበኩላቸው የባልቻ አባ ነፍሶ ታሪካዊ ቴአትር ዝግጅትንና ኪነጥበባዊ እና ማህበራዊ ፋይዳውን አብራርተዋል።

የባልቻ አባ ነፍሶ ታሪካዊ ቴአትር ከማዝናናት በላይ ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከርና ትውልዱ ታሪኩን እንዲያውቅ የሚረዳ የጥበብ ስራ መሆኑን ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ቴአትር እና ባህል አዳራሽ በእድሳት ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የጥበብ አገልግሎት ባልቻ አባ ነፍሶ በተሰኘው ታሪካዊ ቴአትር ዳግም ወደስራ መመለሱ ለብዙዎች ደስተን እንደፈጠረ ከታዳሚያኑ ለመረዳት ተችሏል።

አቶ ፍፁም የቴአትር ቤቶች አስተዳደር ዋና አላማ ጥበብን ለማህበረሰቡ ማዳረስ እና ከወጣቱ ትውልድ ጋር ተቀራርቦ የተለያዩ የኪነ ጥበብ ስራዎችን መስራትና ማህበራዊ ለውጥ ማምጣት መሆኑን ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ዘገዬ፣ የአዲስ አበባ ቴአትር እና ባህል አዳራሽ ዳይሬክተር አርቲስት ካሳዬ ገበየሁ በመግለጫው ተገኝተዋል።

የቴአትሩ አዘጋጅ ዶክተር ተሻለ አሰፋ፣ አንጋፋው ተዋናይ አብራር አብዶ እና ተዋናይት ቅድስት ሲሳይ ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡ ሲሆን በጋዜጣዊ መግለጫው ጥሪ የተደረገላቸው የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ ወጣት ተፅኖ ፈጣሪ ቲክቶከሮች እና የሚዲያ ተቋማት ተገኝተዋል።

በሁለት ጦር አውድማዎች ላይ ጀብድ የሰራው ደጃዝማች ባልቻ ሳፎን ጀግንነት፣ ፍቅር፣ ሰብዓዊነትና መስዋዕትነትን የሚተርከው ባልቻ አባ ነፍሶ ታሪካዊ ቴአትር ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት እሁድ መጋቢት 20/07/2018 ዓ.ም ይመረቃል።

ጌጡ ተመስገን (Getu Temesgen)
#getutemesgen #spotlightcommunications #sabreawards #publicrelations #marketingsuccess #ethiopia #eastafrica #safaricomethiopia #awardwinner

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.