Logo
Getu Temesgen
"ይህንን ነባር ባህል አቀናጅተን አንድ ትልቅ ብሔራዊ የፈረስ ፌስቲቫል እንፍጠር"
#ethiopia | ​ዛሬ በታሪካዊቷ ደብረታቦር ከተማ በአጅባር ሜዳ፤ በደማቅ የፈረስ ጉግስ ትርኢት የሚታጀበውን የቅዱስ መርቆርዮስን በዓለ ንግሥ ታድመናል።

​ይህ በዓል ሃይማኖታዊ እሴቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የጀግንነት መገለጫ የሆነው የፈረስ ጉግስ ባህላችን በልዩ ድምቀት የሚታይበት ነው። ይህንን ነባር እና ድንቅ ባህል ከሌሎች የሀገራችን የባህል ጨዋታዎች ጋር በማስተባበር "አንድ ትልቅ ብሔራዊ የፈረስ (የባሕል) ፌስቲቫል" ቢፈጠር ለቱሪዝም እና ለሀገር ገጽታ ግንባታ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው።

​ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እና ለደብረ ታቦር ነዋሪዎች እንኳን አደረሳችሁ! መልካም በዓል!

​- አገኘሁ አዳነ (ድልነሣሁ)

​#debretabor #stmerkorios #gugs #horseriding #culture #ethiopia #nationalfestival #agagnehuadane #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.