6 months ago
🐎አጅባር ከሜዳው ስር እትብቴ ተቀብሮ፣
ደብረ ታቦር ያድራል ልቤ ዞሮ ዞሮ
* ከአጅባር ሜዳ እስከ ዴንሳ ግርጌ... ሰማይና ምድሩ የደመቀበት የቅዱስ መርቆሬዎስ ንግሥ! ⛪️🇪🇹
#ethiopia | ዛሬ የደቡብ ጎንደር ምድር በልዩ ድምቀት ታጅባ ዋለች። በታሪካዊቷ ደብረ ታቦር (አጅባር) እና በአምሳለ-አንበሳው እስቴ (ዴንሳ) ግርጌ የተከበረው የቅዱስ መርቆሬዎስ በዓል፤ ኢትዮጵያዊነትን፣ ጀግንነትንና እምነትን አስተሳስሮ አሳይቷል።
📍 ደብረ ታቦር - አጅባር ሜዳ
ምድሩ በጀግኖቹ የፈረስ ግልቢያ ሲናወጥ፣ ሰማዩ በምስጋና እና በዘመናዊ የአየር ትርኢት ደምቆ ታይቷል። የበጌምድር መገለጫ የሆኑት ፈረሰኞች የሽምጥ ግልቢያ እና የጦር ውርወራ ጥበባቸውን ሲያሳዩ፤ የቀደሙት ነገሥታት ታሪክ በህያውነት ተመስሏል። ነዋሪዎቹም "እልፍኙ ተውቦ ነጭ ጤፍ እንጀራ እየተጋገረ" እንዲሉ፤ እንግዳን በክብር ተቀብለው አስተናግደዋል።
📍 እስቴ - የዴንሳ ግርጌ
"የአንች ሀገር ወዴት ነው የእኔስ ሀገር እስቴ" የተባለላት እስቴ መካነ ኢየሱስ፤ ከ8 የፈረስ ማኅበራት በተውጣጡና "ፈረስ እንደ አሞራ" በሚያበሩ ጀግኖች ተሞልታለች። ከባለግርማው ዴንሳ ተራራ ግርጌ የታየው ትዕይንት ለዓይን የሚማርክ ነበር።
ዛሬ ፈረሰኛው ፈረሰኛውን ሰማዕት (ቅዱስ መርቆሬዎስን) አጅቦ፤ ጥርን በድምቀት ሸኝቷል።
ይህቺ ናት አገሬ፤ ይህቺ ናት ኢትዮጵያ! 💚💛❤️
#debretabor #ajbar #este #densa #stmerkorios #gugs #culture #ethiopia #amhara #tourism #tradition #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

"ይህንን ነባር ባህል አቀናጅተን አንድ ትልቅ ብሔራዊ የፈረስ ፌስቲቫል እንፍጠር"
#ethiopia | ዛሬ በታሪካዊቷ ደብረታቦር ከተማ በአጅባር ሜዳ፤ በደማቅ የፈረስ ጉግስ ትርኢት የሚታጀበውን የቅዱስ መርቆርዮስን በዓለ ንግሥ ታድመናል።
ይህ በዓል ሃይማኖታዊ እሴቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የጀግንነት መገለጫ የሆነው የፈረስ ጉግስ ባህላችን በልዩ ድምቀት የሚታይበት ነው። ይህንን ነባር እና ድንቅ ባህል ከሌሎች የሀገራችን የባህል ጨዋታዎች ጋር በማስተባበር "አንድ ትልቅ ብሔራዊ የፈረስ (የባሕል) ፌስቲቫል" ቢፈጠር ለቱሪዝም እና ለሀገር ገጽታ ግንባታ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው።
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እና ለደብረ ታቦር ነዋሪዎች እንኳን አደረሳችሁ! መልካም በዓል!
- አገኘሁ አዳነ (ድልነሣሁ)
#debretabor #stmerkorios #gugs #horseriding #culture #ethiopia #nationalfestival #agagnehuadane #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

Comments