የታሪክና የማንነት ጥሪ ከከረዩ ምድር❤
#ethiopia | የኩራትና የጥንታዊው የገዳ ሥርዓት መገለጫ የሆነው ታላቁ የከረዩ "ሚቺሌ ገዳ" የቡታ ሥነ-ሥርዓት እሁድ ታህሳስ 26እና 27 በድምቀት ይከበራል!
፨የከረዩ ገዳ ስርዓት፨
የከረዩ ገዳ ስልጣን ሽግግር፦ የጥበብ፣ የልምድ ልውውጥና የዲሞክራሲ ተምሳሌት!
በኢትዮጵያ ቀደምት ታሪክና ባህል ውስጥ ስር የሰደደው የከረዩ ኦሮሞ የገዳ ስልጣን ሽግግር ስነ-ስርዓት ዛሬ በደመቀ ሁኔታ ተጀምሯል። ይህ ለሁለት ሳምንታት የሚዘልቀው ታላቅ ክውን ልዩ የሚያደርገው አንድ ድንቅ ጥበብ አለው፤ እርሱም "የስልጣን መጋራት" ነው።
የከረዩ ገዳ ስርዓት፦ በቡታ ቀላ ስነ-ስርዓት የታሪክና የወግ ትውስታ
የከረዩ ኦሮሞ ህዝብ የ"ቱታ ገዳ ሚቺሌ" ለገዳ ስርዓት እጅግ ቅዱስና ትርጉም ያለው "የቡታ ቀላ" ስነ-ስርዓትን ለማከናወን በሚያደርገው ዝግጅት፤ የራሱን ጥንታዊና ተወላጅ የዲሞክራሲ ስርዓት ጥንካሬ፣ ጽናትና ቀጣይነት በድጋሚ እያረጋገጠ ይገኛል።
ባለፉት ስድስት ዓመታት የገዳ ስልጣንን (ባሊ) በታማኝነት ሲመራ የቆየው የ"ገዳ ሚቺሌ" ትውልድ፣ አሁን ላይ ወሳኝ ወደሆነው የሽግግር ስነ-ስርዓት ምዕራፍ ተሸጋግሯል። ይህ የ"ቡጣ ቀሉ" ስነ-ስርዓት ያለፈውን የአመራር ዘመን መቃኛና ራስን የማደሻ ወቅት ሲሆን፤ በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ሙሉ ስልጣኑን ለሚረከበው ቀጣዩ የገዳ ተረኛ ቡድን ስልጣኑ በሰላም እንዲሸጋገር መሰረት የሚጣልበት ታሪካዊ ክውን ነው።
"ቡጣ ቀሉ" ከመደበኛ ስነ-ስርዓት ባለፈ ተጠያቂነትን፣ የአመራር ቀጣይነትንና ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገር መሪነትን የሚወክል ታላቅ ምልክት ነው። ይህም የኦሮሞ ህዝብ ለዲሞክራሲያዊ አስተዳደር፣ ለባህላዊ ማንነትና ለማህበራዊ ስምምነት ያለውን ጥልቅ ቁርጠኝነት የሚያንጸባርቅ ሲሆን፤ እነዚህ እሴቶች የገዳ ስርዓት ለዘመናት ጸንቶ እንዲቆይ ያደረጉ ምሰሶዎች ናቸው።
የከረዩ ማህበረሰብ ለዚህ ታሪካዊ ክስተት በሚዘጋጅበት በዚህ ወቅት፣ ስነ-ስርዓቱ የኦሮሞ ባህል ምን ያህል ጠንካራ መሆኑንና ለሰላም፣ ለአንድነት እንዲሁም ለመልካም አስተዳደር እያበረከተ ያለውን ዘላቂ አስተዋጽኦ ለዓለም የሚያሳይ ህያው ምስክር ነው።
ይህ በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚዲያ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ድንቅ የዲሞክራሲ ትምህርት ቤትም ነው። ይህንን ታሪካዊ ኩነት በቦታው ተገኝታችሁ ለዓለም ለማስተዋወቅ ለምትተጉ በሙሉ ትልቅ ምስጋና ይገባችኋል!
ይህ በዓል የከረዩ ኦሮሞዎች ለዘመናት የጠበቁት፣ ማንነታቸውንና ባህላቸውን ለዓለም የሚያሳዩበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው። ዓመታት ዓመታትን እየተኩ፤ የአባቶቸው ፈር ሳይለቁ የደረሱት የከረዩ አባቶች፣ ዛሬም በኩራት ወደ አባቶቻችን በታሪካዊ መሬት ይጠሩናል።
ሁላችንም በቦታው በመገኘት ባህላቸውን እና ታሪካቸውን እንካፈል!
#ባህላችን የማንነታችን ነፀብራቅ ነው!,የከረዩ ገዳ በዓል፦ የቡታ ሰርግ እና የጎባ (ሥልጣን) ርክክብ!!
የከረዩ ኦሮሞ ጠንካራ ታሪክ፣ ባህል እና የገዳ ሥርዓት ያለው ማህበረሰብ ነው። ይህ በዓል የአንድነቱ፣ የጀግንነቱ እና የማንነቱ መገለጫ ነው።
የመከበሪያ ቦታ፦ ተሬ ሌዲ (Tarree Leedii) የሚጪሌ ገዳ የሥርዓት አፈፃፀም መርሃ ግብር (ከታህሳስ 16 - 26)
ከታህሳስ 16/2018ዓ.ም ጀምሮ የሚጪሌ ገዳ አባላት ተሬ ሌዲ ላይ ሠፍረዋል።
በአባ ቦኩ አዳራሽ (ጋልማ) ውስጥ እሳት ይለኩሳሉ።
የምርቃት እና የአርዳጋ (የመስዋዕት) ሥነ-ሥርዓት ያከናውናሉ።
ግመሎችን በታላቅነት ቅደም ተከተል ይፈታሉ።
ሁፌና ተራራ ላይ የከተሪ እንጨት ያቃጥላሉ፣ ኮርማም ያርዳሉ።
2. የከራ (የደጅ) ሥነ-ሥርዓት (ታህሳስ 17)፦
በአባ ቦኩ ደጅ ላይ ዱላቻ (ጥቁር ላም) ያርዳሉ።
ለአባ ቦኩ እሳት እና ለአርዳጋው ጠባቂዎችን ይመድባሉ።
3. አዳራሽ መገንባት (ታህሳስ 18 - 20)፦
የአባ ቦኩን አዳራሽ (ጋልማ) ይገነባሉ።
የእንግዳ ማረፊያ (ዳሳ)፣ የላም እና የግመል በረት ይሠራሉ።
4. ፀሎት እና ውይይት (ታህሳስ 20 - 25)፦
ወደ ተራራ እና ወደ ወንዝ በመሄድ አምላክን (ዋቃን) ሰላም እንዲሰጣቸው ይለምናሉ።
ስለ ገዳው እና ስለ እንግዶች አቀባበል ልዩ ልዩ ውይይቶችን (ገሪ) ያደርጋሉ።
የአካባቢውን ሰላም የሚያውጅ አዋጅ ያውጃሉ።
5. የማጠቃለያ ቀን (ታህሳስ 26)፦
ረፋድ፦ ሂዲ (ለሥርዓቱ የሚፈለግ ዕቃ) ያዘጋጃሉ፣ ቢቲማ (የኋላ ደጅ) ይገነባሉ።
ከሰዓት በኋላ፦ የጋልማው አባት (አባ ጋልማ) ገቢ የሚያመጡ ሰዎችን ይቀበላሉ።
ምሽት፦ የቡታ ሰርግ ሥነ-ሥርዓት ሳይመሽ ይጀመራል።
ማጠቃለያ፦
ታህሳስ 27 ቀን የባሊ (የሥልጣን) ርክክብ ወይም የጎባ ሥነ-ሥርዓት በመከናወን በዓሉ ይጠናቀቃል።
በሄሎ መተሐራ
#fentale #metahara #kereyu #gada #oromia #culturalheritage #oromia Culture and Tourism Bureau #oromia Tourism Commission

7 months ago