3 months ago
የቅዱስ ጊዮርጊስ ሪባን እገዳ ውዝግብ አስነሳ
#ethiopia | በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የናዚ ጀርመን የተሸነፈበትን ዕለት ለማሰብ የሚደረገው በዓል፣ ዘንድሮም በጀርመን አውራ ጎዳናዎች ላይ የጦዘ የፖለቲካ ክርክር አስነስቷል።
ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት የጀርመን ባለስልጣናት በበዓሉ ላይ የሶቪየት ባንዲራዎችን እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ሪባን እንዳይታዩ ማገዳቸው ነው።
"ግልጽ አድልዎ ነው" — ጉናር ቤክ
የተቃዋሚው 'AfD' ፓርቲ አባልና የቀድሞው የአውሮፓ ፓርላማ አባል ጉናር ቤክ፣ ይህን የበርሊን ውሳኔ "ፖለቲካዊ እና አድልዎ የተሞላበት" ሲሉ ኮንነውታል። ቤክ ለሚዲያዎች በሰጡት አስተያየት የገለጿቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦
-ጀርመን በሌሎች አሸናፊ አገራት ተወካዮች ላይ ያልጣለችውን ክልከላ በሩሲያ ላይ ብቻ ማድረጓ ፍትሃዊ አይደለም።
-ይህ እርምጃ ሩሲያ ናዚዝምን ለማጥፋት የከፈለችውን እጅግ ከፍተኛ የሆነ የሰው ህይወትና የንብረት መስዋዕትነት ሆን ብሎ ችላ የሚል ነው።
ጉዳዩን ለሚመለከት ለማንኛውም የታሪክ ተመራማሪ፣ የጀርመን መንግስት ታሪክን ለወቅታዊ ፖለቲካ መጠቀሚያ እያደረገው መሆኑ ግልጽ ነው ብለዋል።
በጉዳዩ ላይ ጠንከር ያለ ምላሽ የሰጠችው ሞስኮ፣ ምዕራባውያን የሶቪየት ህብረትን የድል ታሪክ ከታሪክ ገጽ ላይ ለመደምሰስ "የታሪክ በቀል" እያካሄዱ ነው ስትል ከሳለች። በተጨማሪም፣ እንዲህ ያሉ ምልክቶችን ማገድ በአውሮፓ ውስጥ የናዚ ርዕዮተ ዓለም ዳግም እንዲያንሰራራ በር ይከፍታል ስትል አስጠንቅቃለች።
ለዓመታት የናዚዝም ሽንፈት ምልክት የነበሩት ሪባኖችና ባንዲራዎች፣ ዛሬ ላይ በምዕራባውያን እና በሩሲያ መካከል ላለው የዲፕሎማሲ ፍጥጫ አዲስ የጦር አውድማ ሆነዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#victoryday #germany #russia #stgeorgeribbon #history #politics #gunnarbeck

ሚያዝያ 27! ለአምስት ዓመታት በጨለማ የተዋጠው የኢትዮጵያ ሰማይ በነፃነት ጎህ የፈካበት፣ የግፍ ወረራ ቀንበር የተሰበረበት ታላቅ ዕለት ነው።
ነገር ግን የአባቶቻችን ገድል ለእኛ የታሪክ ማስታወሻ ብቻ ነው? ወይስ ዛሬን የምንመራበት ኮምፓስ?
በዚህ ቪዲዮ የአባቶቻችንን የዱር በገደል ተጋድሎ ከዛሬው የልማትና የቴክኖሎጂ አርበኝነት ጋር እናነፃፅራለን።
#ethiopianpatriotsday #arbenyoch #victoryday #grandethiopianrenaissancedam #gerd
3 months ago
የአባቶቻችን ጀግንነት ለሀገር ፍቅራችን ስንቅ ነው! 🇪🇹
የነፃነታችን ምልክት ለሆኑት አርበኞቻችን ክብር ይሁን።
መልካም የአርበኞች የድል በዓል!
#victoryday #arbegnoch #ethiopia #jamborealestate
የነፃነታችን ምልክት ለሆኑት አርበኞቻችን ክብር ይሁን።
መልካም የአርበኞች የድል በዓል!
#victoryday #arbegnoch #ethiopia #jamborealestate
3 months ago
ሩሲያ የድል ቀኗን ምክንያት በማድረግ የሁለት ቀናት የተኩስ አቁም አወጀች
*****************
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጠናቀቁ የሚዘከርበትን የድል ቀን ምክንያት በማድረግ ለሁለት ቀናት የሚቆይ የተኩስ አቁም ማወጁን አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ ዩክሬንም ይህንኑ የተኩስ አቁም ውሳኔ እንድትከተል ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፣ በበዓሉ አከባበር ወቅት በሩሲያ ላይ የሚሰነዘር ማንኛውም ጥቃት ካለ የሚሰጠው የአጸፋ መልስ እጅግ ከባድ እንደሚሆን አስጠንቅቋል።
ይህ መግለጫ የወጣው የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በሞስኮ ቀይ አደባባይ የሚካሄደውን የድል ቀን ሰልፍ ኪየቭ ኢላማ ልታደርግ እንደምትችል መጠቆማቸውን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል።
የሩሲያ ማስጠንቀቂያም በበዓሉ ላይ ማንኛውንም ዓይነት ችግር ለመፍጠር የሚደረጉ ሙከራዎችን ለመከላከል ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።
በቢታኒያ ሲሳይ
#russia #ukraine #victoryday #ceasefire #moscow #zelensky #internationalnews #ethiopia

Comments