4 months ago
"ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከእኔ ጋር ፊት ለፊት ይወያዩ" - ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ
"ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ፑቲንን ማግኘት ከፈለጉ ወደ ሞስኮ ሊመጡ ይችላሉ" - ክሬምሊን
******************
በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ሊያስቆም ይችላል የተባለ አዲስ የዲፕሎማሲ ሐሳብ ከወደ ኪዬቭ ተሰምቷል።
የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ የፊት ለፊት ውይይት ለማድረግ ለሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ቀን እንዲቆርጡ ጠይቀዋል።
ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ለሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በላኩት ደብዳቤ፤ "ቀን አስቀምጥ እና ፊት ለፊት እንገናኝ" ያሉ ሲሆን፣ በገለልተኛ ሀገር ውስጥ ቀጥታ የፊት ለፊት ውይይት ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።
በተጨማሪም በውይይቱ ላይ አሜሪካ እና የአውሮፓ ሀገራት እንዲገኙ እንደሚፈልጉ በደብዳቤያቸው ጠቅሰዋል።
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ድሚትሪ ፔስኮቭ የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት የላኩት ደብዳቤ እንደደረሳቸው ያረጋገጡ ሲሆን፣ "ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ፑቲንን ማግኘት ከፈለጉ ወደ ሞስኮ ሊመጡ ይችላሉ" ብለዋል።
በዚህ ሰዓት የዓለም ትኩረት ያረፈው በአንድ ጥያቄ ላይ ነው፤ ፕሬዚዳንት ፑቲን የዩክሬኑ አቻቸው ያቀረቡላቸውን ጥሪ ይቀበሉ ይሆን? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል።
በቢታኒያ ሲሳይ
#ebc #ukraine #russia #zelensky #putin #peacetalks #diplomacy

5 months ago
ሩሲያ የድል ቀኗን ምክንያት በማድረግ የሁለት ቀናት የተኩስ አቁም አወጀች
*****************
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጠናቀቁ የሚዘከርበትን የድል ቀን ምክንያት በማድረግ ለሁለት ቀናት የሚቆይ የተኩስ አቁም ማወጁን አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ ዩክሬንም ይህንኑ የተኩስ አቁም ውሳኔ እንድትከተል ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፣ በበዓሉ አከባበር ወቅት በሩሲያ ላይ የሚሰነዘር ማንኛውም ጥቃት ካለ የሚሰጠው የአጸፋ መልስ እጅግ ከባድ እንደሚሆን አስጠንቅቋል።
ይህ መግለጫ የወጣው የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በሞስኮ ቀይ አደባባይ የሚካሄደውን የድል ቀን ሰልፍ ኪየቭ ኢላማ ልታደርግ እንደምትችል መጠቆማቸውን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል።
የሩሲያ ማስጠንቀቂያም በበዓሉ ላይ ማንኛውንም ዓይነት ችግር ለመፍጠር የሚደረጉ ሙከራዎችን ለመከላከል ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።
በቢታኒያ ሲሳይ
#russia #ukraine #victoryday #ceasefire #moscow #zelensky #internationalnews #ethiopia

7 months ago
አንድ ሺህ ዜማ ዜሮ ዲግሪ - የካሙዙ ካሳ የሹመት ጥማት እና የአለም መሪዎች ስም ማጥፋት
ፖለቲካ በ 'Auto-tune' አይሰራም የካሙዙ ካሳ የድፍረት ቅንብር እና የተገላቢጦሽ ምሳሌዎቹ
የአቀናባሪ ካሙዙ ካሳ ጽሁፍ በውጪ ሀገራት ስኬታማ የነበሩ ግለሰቦችን እንደ ምሳሌ በማቅረብ የራሱን የፖለቲካ ተሳትፎ ትክክለኛነት ለማስረዳት ቢሞክርም የቀረቡት ማስረጃዎች ግን ካለበት ተጨባጭ ሁኔታ (የትምህርት ዝግጅት ማነስ እና የሙያ አይነት) አንጻር ሲመዘኑ እርስ በርሳቸው የሚጋጩና የሱን ሃሳብ የማይደግፉ ናቸው።
የካሙዙ ካሳን "የአለም ተሞክሮ" ድርሰት ስንመለከተው ሰውየው ቅንብሩ ላይ እንጂ መረጃ ፍለጋው ላይ ጭንቅላቱን እንዳልተጠቀመበት በግልጽ ያስታውቃል።
ሊቅ ያወቀውን ይናገራል ካሙዙ የሰማውን ይዘበዝባል እንደሚባለው የጠቀሳቸው ሰዎች ታሪክ የሱን ድንቁርና እንጂ የሱን ብቃት አያረጋግጥም።
ካሙዙ ሆይ እስቲ የቀረጽከውን የውሸት ሲቪ በትንሹ እንፈትሽው
1. ባለንድራ ሻህ (Balen Shah) - የኔፓሉ መሪ
ካሙዙ የጠቀሰው ባለንድራ ሻህ ራፐር ስለሆነ ብቻ የመሪነት ወንበር ላይ የወጣ ይመስለዋል ነገር ግን እውነታው ይሄ ነው
• የትምህርት ማስረጃው ባለንድራ ሻህ በ Structural Engineering (የህንፃ ስትራክቸር መሐንዲስ) የመጀመሪያ ዲግሪውን የያዘ ሲሆን በማስተርስ ዲግሪው ደግሞ በ Infrastructure Engineering ተመርቋል።
• ለካሙዙ መልእክት፦ ካሙዙ ሆይ የቤት ስራህን ስትሰራ ራፐር መሆኑን ብቻ ሳይሆን መሐንዲስ መሆኑንም ብታነብ ኖሮ አንተ "High School" እንኳን ሳትጨርስ እሱን ለመምሰል ባልዳዳህ ነበር።
ኔፓል ሀገር እንጂ የሙዚቃ ስቱዲዮ አይደለችም!
2. ቮሎዲሚር ዘለንስኪ (Volodymyr Zelenskyy)
"ኮሜዲያን ነበር" ብሎ ካሙዙ ሊያጽናናን ይሞክራል ግን አንድ ነገር ረሳ
• የትምህርት ማስረጃው፦ ዘለንስኪ ከኪዬቭ ብሔራዊ የኢኮኖሚ ዩኒቨርሲቲ በ ህግ (Law Degree) የተመረቀ ባለሙያ ነው።
• ለካሙዙ መልእክት፦ ዘለንስኪ በድራማው ላይ ፕሬዝዳንት ሆኖ ከመጫወቱ በፊት የህግ መጽሐፍትን ገልጦ ያጠና ሰው ነው። አንተ ግን በገሃዱ ዓለም የፓርላማ ወንበር ላይ ተቀምጠህ "ቅንብሩን እንዴት ላሳምረው?" እያልክ ልታቀነቅን ነው ወይስ በ "Autotune" ልታስተዳድረን?
3. ቫችላቭ ሃቬል (Václav Havel)
ካሙዙ የጠቀሰው የቼክ ሪፐብሊክ መሪ ታሪክማ ለካሙዙ ጭራሽ አይሆንም
• የትምህርት ማስረጃው፦ ሃቬል በድራማቲክ አርትስ የተመረቀና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቅ ፈላስፋ (Philosopher) እና ደራሲ ነው።
• ለካሙዙ መልእክት፦ ሃቬል አምባገነንነትን በብዕሩና በፍልስፍናው ያሸነፈ ሰው ነው። አንተ የ 12ኛ ክፍል ማትሪክን እንኳን ሳታልፍ እንዴት ብለህ ነው የሃቬልን ስም ለመጥራት የደፈርከው? ድፍረት ወይስ ድንቁርና?
4. ሮናልድ ሬገን እና አርኖልድ ሽዋርዜኔገር
እነዚህ ሰዎች ወደ ፖለቲካ ከመግባታቸው በፊት ምን እንደነበሩ ካሙዙ ሳያጣራ ተዋናይ ነበሩ ብሎ ዘለለው
• ሮናልድ ሬገን፦ በኢኮኖሚክስ እና ሶስዮሎጂ (Economics and Sociology) ዲግሪ የነበረው ሰው ነው።
• አርኖልድ፦ በቢዝነስ እና ኢንተርናሽናል ኢኮኖሚክስ (Business and International Economics) ዲግሪ አለው።
• ለካሙዙ መልእክት፦ እነዚህ ሰዎች ሆሊዉድ ከመግባታቸው በፊትና ከገቡም በኋላ የተማሩ ሰዎች ናቸው።
"High School" ያላጠናቀቀ ሰው የአሜሪካን ፕሬዝዳንቶች እንደ ምሳሌ ሲጠቅስ "ድንገት ፊልም ውስጥ ያለን" ነው የሚመስለው።
5. ጆርጅ ዌአ እና ኢሱኑ ንዱር
• ጆርጅ ዌአ፦ ፕሬዝዳንት ከመሆኑ በፊት ወደ ትምህርት ቤት ተመልሶ በቢዝነስ ማኔጅመንት እና በፐብሊክ አድሚኒስትሬሽን (Master's in Public Administration) ተመርቋል።
• ለካሙዙ መልእክት፦ ጆርጅ ዌአ ለሀገር መሪነት እግር ኳስ ብቻ አይበቃም ብሎ የተማረ ሰው ነው። አንተ ግን "ከ 10ኛ ክፍል በላይ እውቀት አያስፈልገኝም ብለህ ፓርላማ ለመግባት መመኘትህ ለታዛቢ ግርምት ነው።
ካሙዙ ሆይ የጠቀስካቸው ሰዎች በሙሉ የጋራ መለያቸው "ተምረው ማለፋቸው" ነው።
አንተ ግን ትምህርት ቤት በር ላይ እንኳን ሳታልፍ "እነዚህን ሆነናል" ማለትህ የኢትዮጵያን ህዝብ መወከል እንደ ሙዚቃ ቅንብር መስሎህ ከሆነ ተሳስተሃል።
ፖለቲካ "Key-Note" አይደለም እውቀትና ብቃት ይጠይቃል።
ቢያንስ ቢያንስ ምሳሌ ስትጠቅስ የሰዎቹን የትምህርት ታሪክ ጎግል (Google) ማድረግ እንኳን አለመቻልህ ምክር ቤት ብትገባ ምን አይነት "ጥናት" ልታቀርብ እንደምትችል ከወዲሁ ያሳብቃል።
የፓርቲ አባል መሆን መብት ቢሆንም ሀገር መምራት ግን "ሰባት ድምፅ" መደርደር አይደለም።
Via belayneh Kassa

የካሙዙ ካሳ ላላ መልዕክት
ሠላም ጤና ይስጥልኝ የተከበራችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን
#ethiopia | በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ጉምቱ የተባሉ የኪነጥበብ ባለሞያዎች እና በተለያዩ የሞያ ዘርፎች ላይ አንቱታን ያተረፉ ግለሰቦች ለህዝብ ጥቅም ለሀገር መፅናት ሲሉ በፖለቲካ ተሳትፈዉ ለህዝባቸዉ ይበጃል ያሉትን ታሪክ ሰርተዋል ፣ እየሰሩም ይገኛሉ። በአለም የፖለቲካ ጉዞም ቢሆን የኪነጥበብ ባለሞያዎች እና ስፖርተኞች ከረጅም ጊዜ ጀምሮ በማኅበራዊና ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ብርቱ ተሳትፎ ሲያደርጉ ቆይተዋል።
የነበራቸውን ተሳትፎ በወፍ በረር ለመቃኘት ያክል:-
————
ሴኔጋል – ኢሱኑ ንዱር (Youssou N'Dour)
በዓለም የሙዚቃ መድረክ ተወዳጁ የሴኔጋል ዘፋኝ ኢሱኑ ንዱር፣ ለረጅም ዓመታት በማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ድምጹን ካሰማ በኋላ፣ በ2012 የሴኔጋል የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው ተሾመ። በዚህ ሥልጣን የሀገሪቱን ቅርስ በማስጠበቅ ወጣቶችን በማብቃት ረገድ ትልቅ አሻራ አስቀርቷል።
————-
ላይቤሪያ – ጆርጅ ዊሃ (George Weah)
ከዓለም እግር ኳስ ታላላቅ ኮከቦች አንዱ የሆነው አፍሪካዊ የባሎን ዶር ተሸላሚ ጆርጅ ዌአ፣ ከሜዳ ጡረታ በኋላ ወደ ላይቤሪያ ፖለቲካ በመግባት ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት በ2018 የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆኖ ተመረጠ። የእርሱ ጉዞ ከስፖርት ወደ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር ከሚታወቁት ደማቅ ምሳሌዎች አንዱ ነው።
—————
ናይጄሪያ – ፌላ ኩቲ (Fela Kuti)
የአፍሮቢት ሙዚቃ አባት ተብሎ የሚጠራው ናይጄሪያዊው ፌላ ኩቲ፣ በዘፈኖቹ ብቻ ሳይሆን በጠንካራ የፖለቲካ ንቅናቄውም ይታወቃል። መንግሥትን ጥሩ ሲሰራ ደግፎ በደልና ብልሹ አስተዳደርን በግልጽ ተቃዉሞ የካላኩታ ሪፐብሊክ በመባል በሚታወቀው ማኅበረሰቡ ውስጥ ተደጋጋሚ ቅጣትና እስራት ቢደርስበትም፣ የአፍሪካን የሕዝብ ተነሳሽነት በሙዚቃ አብይ ምሳሌ ሆኖ ቆይቷል።
——————
ዩናይትድ ስቴትስ – ሮናልድ ሬገን (Ronald Reagan)
ከሆሊዉድ ታዋቂ ተዋናዮች አንዱ የነበረው ሮናልድ ሬገን፣ ከስክሪን ወደ ፖለቲካ በመሻገር ከ1967 እስከ 1975 የካሊፎርኒያ ገዥ ሆኖ አገልግሏል፣ በኋላም በ1981 የአሜሪካ 40ኛ ፕሬዚዳንት ሆኖ ተመረጠ። በሁለት የሥልጣን ዘመኑ በቀዝቃዛው ጦርነት ማብቂያ ላይ ትልቅ ሚና በመጫወት፣ የአሜሪካን ኢኮኖሚ በሪጋኖሚክስ ፖሊሲ በማሻሻል ከተዋንያን ወደ ዓለም አለቃነት የተሸጋገሩ ብርቱ ምሳሌ ነዉ።
———————-
ቦብ ማርሊ (Bob Marley)
የሬጌ ሙዚቃ ምልክት ቦብ ማርሊ በዘፈኖቹ የሰላም፣ የአንድነትና የፖለቲካ ነፃነት መልእክት አሰማ። በጃማይካ ከፍተኛ የፖለቲካ ግጭት በነበረበት ወቅት ሁለት ተቀናቃኝ አንጃዎችን በአንድ መድረክ ላይ በማሰባሰብ “One Love” ኮንሰርት በማዘጋጀት ታሪካዊ ስራን ሰርቷል። ምንም እንኳ መደበኛ የፖለቲካ ሹመት ባይይዝም፣ በዓለም ዙሪያ እንደ ታላቅ የሰላም አራማጅና ተጽዕኖ ፈጣሪ ይታወሳል።
——————-//
ካሊፎርኒያ – አርኖልድ ሽዋርዜኔገር (Arnold Schwarzenegger)
በሆሊዉድ ፊልሞች ተወዳጁ የቀድሞ የሰውነት ግንባታ ሻምፒዮንና ተዋናይ አርኖልድ ሽዋርዜኔገር፣ ወደ ፖለቲካ በመግባት ከ2003 እስከ 2011 የካሊፎርኒያ ግዛት 38ኛ ገዥ ሆኖ አገልግሏል። በሁለት ወገን በተካሄደ ልዩ ምርጫ ተመርጦ፣ በአካባቢ ጥበቃና በጀት ማሻሻያ ላይ ትኩረት በማድረግ ከፊልም ስኬት ወደ እውነተኛ አመራር የተሻገረ ምሳሌ ነዉ።
———————-
ዩክሬን – ቮሎዲሚር ዘለንስኪ (Volodymyr Zelenskyy)
ዩክሬናዊው ኮሜዲያንና ተዋናይ ቮሎዲሚር ዘለንስኪ፣ በሰራዉ ተከታታይ ድራማ ውስጥ ፕሬዚዳንትን በመጫወት ታዋቂነትን ካገኘ በኋላ፣ በ2019 በእውነት የዩክሬን ፕሬዚዳንት ሆኖ ተመረጠ። ከሥልጣን ላይ በነበረበት ወቅት ሀገሩ ከባድ ጦርነት የገጠማት ሲሆን፣ ዘለንስኪ በአለም አቀፍ መድረክ የዩክሬንን ድምጽ በማሰማት የኮሜዲ ተዋናይነትን ወደ ጀግንነት የለወጠ አመራር አሳይቷል።
———————-
ቼክ ሪፐብሊክ – ቫችላቭ ሃቬል (Václav Havel)
የቼክ ጸሐፊ፣ ተውኔት ደራሲና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቫችላቭ ሃቬል፣ በኮሚኒስት አገዛዝ ዘመን በፅሑፎቹና በተግባሮቹ የሰላማዊ አብዮት (ቬልቬት አብዮት) መሪ ሆነ። ከአገዛዙ ውድቀት በኋላ በ1989 የቼኮዝሎቫኪያ ፕሬዚዳንት ሆኖተመረጠ፣ በኋላም የቼክ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሆኖ እስከ 2003 አገልግሏል። የጸሐፊነት ብልሃቱን ወደ ዴሞክራሲ ግንባታ በመምራት ከባህል ወደ ፖለቲካ ከፍተኛ ለውጥ ካደረጉ ታላላቅ ሰዎች አንዱ
ነዉ።
ኔፓል ፣ ባለንድራ ሻህ(Balendra Shah) ፣
በሰፊው እሚታወቀዉ መጠሪያዉ Balen ነዉ፣ የቀድሞ ራፐር፣ ሂፕ-ሆፕ አርቲስት እና ስትራክቸራል መሐንዲስ ሲሆን ፣ የኔፓል አዲስ ብሔራዊ መሪ ሆኖ ተነስቷል። ይህም የባለን ፓርቲ የ Rastriya Swatantra Party (RSP) በማርች 5፣ 2026 ምርጫዎች ላይ ታሪካዊ አሸናፊነትን ተጎናፅፏል።
ባለንም በኔፓል ፖለቲካ ከወጣት መሪዎች አንዱ ያደርገዋል ።
———- #እናም የኪነጥበብ ባለሞያዎች በማኅበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ መሳተፍ ለሀገርና ለሕዝብ የጎላ ጥቅም ከማበርከት ባለፈ፣ ለኪነጥበብ ዘርፉ ከፍተኛ መነቃቃትን እንደሚፈጥር በጽኑ አምናለሁ ::ይሄም እድል ለኢትዮጵያ ኪነጥበብ እድገትም ትልቅ ሚና እንዳለው በማመንና አርቱን ሌሎች አገራት በደረሱበት ለማድረስ እንዲሁም ሀገርን በፅኑ ከማገልገል አላማ በመነሳት በተጨባጭ ለሀገር እየሰራ ነዉ ፣ ህዝቤን እና ሀገሬን ወደ ብልፅግና ማማ ያደርሳል ያልኩትን የብልጽግና ፓርቲን ወክዬ ለመወዳደር እጩ መሆኔን ሳበስር ደስታ ይሰማኛል።
—-////—-///—-
በስተመጨረሻም : እነሆ በኢትዮጵያ ታሪክ ወርቃማ ጊዜ ላይ እንገኛለን
የኢትዮጵያ ስብራቶች እየተጠገኑ ነው። በኢትዮጵያ እምቅ ሀብቶች እየወጡ ነው።
የኢትዮጵያ ጂኦ ፓለቲካዊ ቁመና እየተቀየረ ነው፣
ሀገር በምክክር እና በሽግግር ፍትህ ቁርሾዋን እየሻረች፣ ነገዋን እየተለመች ነው፣
ኢትዮጵያ በብዙ ነገሮች እራስዋን የመቻል ዕቅዷን እያሳካች ነው፣
የኢትዮጵያ ህልም እውን ሆኖ፣ ሁለንተናዊ ብልፅግና በኢትዮጵያ እንዲረጋገጥ፣ ጉዞው በውጤት ተጀምሯል።
ይሄን ውጤታማ ጉዞ ይበልጥ ለማሳካት ብልፅግናን መምረጥ ወሳኙ ነገር ነው።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ!!!
ካሙዙ ካሣ

9 months ago
ዘለንስኪ አሜሪካ የቺቺንያውን ሰውዬ አንጠልጥላ ትውሰድልኝ አሉ
#ethiopia | የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ አሜሪካ የቼቼኑን መሪ ራምዛን ካዲሮቭን አፍና እንድትወስድላቸው መጠየቃቸውን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል። ፕሬዝዳንቱ ይህንን ጥሪ ያቀረቡት አሜሪካ በቬንዙዌላው መሪ ኒኮላስ ማዱሮ ላይ የወሰደችውን እርምጃ እንደ አርአያ በመጥቀስ ነው።
📍 የዘለንስኪ ስትራቴጂያዊ ጥሪ
ዘለንስኪ በንግግራቸው ፕሬዝዳንት ትራምፕ በማዱሮ ላይ የወሰዱት እርምጃ "ፈጣን እና ቆራጥ" እንደነበር ገልጸው አድናቆታቸውን ችረዋል። አሁንም አሜሪካ ተመሳሳይ እርምጃ በካዲሮቭ ላይ መውሰድ እንዳለባት ሲያሳስቡ የሚከተለውን ምክንያት ሰጥተዋል፦
"ካዲሮቭ ታፍኖ ከተወሰደ ፑቲን ይመለከታል፤ እናም ቆም ብሎ ሊያስብ ይችላል።"
>
🦁 የካዲሮቭ "ሰው ሁን" ባይ ምላሽ
የሩሲያ ታማኝ የሆኑት የቼቼኑ መሪ ራምዛን ካዲሮቭ ለዘለንስኪ ንግግር የሰጡት ምላሽ ፈጣንና ጠንካራ ነበር። ካዲሮቭ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፦
* "በአሜሪካ ትከሻ አትደበቅ"፦ ዘለንስኪ የሰላም ድርድሩን ከማቀላጠፍ ይልቅ ትንኮሳ ላይ መጠመዳቸውን ገልጸዋል።
* "ፈሪ ነው"፦ "እሱ ራሱ እንደሚያደርገው እንኳ በመግለጽ አላስፈራራኝም፤ ይልቁንም አሜሪካን እየተማጸነ ነው" ሲሉ ዘብተዋል።
* "ሰው ሁን"፦ ዘለንስኪ ከሌላ ኃይል ጀርባ ከመደበቅ ይልቅ ፊት ለፊት መጋፈጥ እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል።
🔍 የፖለቲካ ትንታኔ
ይህ ንግግር በዩክሬን እና በሩሲያ መካከል ያለውን ውጥረት ይበልጥ እንደሚያባብሰው ይታመናል። ዘለንስኪ የአሜሪካን "ጡንቻ" በመጠቀም የሩሲያን የጦር አጋሮች ለማዳከም ያላቸውን ፍላጎት ሲያሳዩ፣ ካዲሮቭ በበኩላቸው ይህንን እንደ ድክመትና እንደ ፕሮፓጋንዳ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ዘለንስኪ #ካዲሮቭ #ዩክሬን #ሩሲያ #አሜሪካ #ትራምፕ #ዓለምአቀፍዜና #የጦርነትዜና #zelensky #kadyrov

1 year ago
የሞስኮ የአፀፋ ምላሽ በመላው ዩክሬን ክልሎች !
ከቀናት በፊት የነዳጅ ማጣርያ ጣቢያዋ ላይ በዩክሬን ጥቃት የደረሰባት ሩሲያ በዛሬው እለት በመላ ዩክሬን በሚገኙ ክልሎች ላይ ያነጣጠረ መጠነ ሰፊ የሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት መፈፀሟ ተነገረ ።
የዩክሬን ባለስልጣናት እንደገለፁት ከሆነ ቅዳሜ ማለዳ ጀምሮ የሩሲያ ተምዘግዛጊ ሚሳኤልና ሰዉ አልባ ድሮኖች በመላው ዩክሬን ሰማይ ላይ እንዳሻቸው ሲፈነጩበት ዉለዋል ጥቃቱ በሰዉና በንብረት ላይም የከፋ ጉዳት አድርሷል ብለዋል ።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ እንዳሉት ጥቃቶቹ የተፈጸሙት በዘጠኝ ክልሎች ማለትም ዲኒፕሮፔትሮቭስክ፣ ሚኮላይቭ፣ ቼርኒሂቭ፣ ዛፖሪዝዝሂያ፣ ፖልታቫ፣ ኪየቭ፣ ኦዴሳ፣ ሱሚ እና ካርኪቭ አካባቢዎች ሲሆንጨበትንሹ 3 ሰዎች መሞታቸውን እና በደርዘን የሚቆጠሩ መቁሰላቸውን ገልፀዋል ።
ዘሌንስኪ በይፋዊ የቴሌግራም አካውንቱ ላይ በሰጠው መግለጫ "የጠላት ኢላማ የእኛ መሠረተ ልማት፣ የመኖሪያ አካባቢዎች እና የሲቪል ኢንተርፕራይዞች ላይ ነበር" በክላስተር ጥይቶች የታጠቀ የሩሲያ ሚሳኤል በዲኒፕሮ ከተማ ባለ ብዙ ፎቅ ሕንፃ ላይ ወድቋል ሲል ገልጿል።
አክሎም “እያንዳንዱ እንዲህ ዓይነቱ ጥቃት ወታደራዊ አስፈላጊነት ሳይሆን ሩሲያውያን ሰላማዊ ሰዎችን ለማስፈራራት እና መሠረተ ልማታችንን ለማውደም የታለመ ስትራቴጂ ነው” ብሏል።
Zelenskyy በሚቀጥለው ሳምንት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከዩኤስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመገናኘት እንደሚጠብቅ ተናግረዋል. በተጨማሪም የዩክሬን እና የዩናይትድ ስቴትስ ቀዳማዊት እመቤቶች ህጻናትን በሚያካትቱ ሰብዓዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የተለየ ውይይት ሊያደርጉ እንደሚችሉም ተናግረዋል።
የአካባቢው ባለስልጣናት በኪየቭ ክልል፣ በቡቻ፣ ቦሪስፒል እና ኦቡኪሂቭ አካባቢዎች ጥቃት መፈፀሙን ገልፀዋል በጥቃቱም ቤት እና መኪኖች ተጎድተዋል።
በዛሬው የሩሲያ ጥቃት 619 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏን የገለፀዉ የዩክሬን አየር ሃይል በበኩሉ 552 ድሮኖች፣ ሁለት ባለስቲክ ሚሳኤሎች እና 29 ክሪዝ ሚሳኤሎች መትቶ መጣሉን አሳዉቋል ።
በተያያዘ ዜና ዩክሬን በሩሲያ የነዳጅ ዘርፍ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈፀሟን የዩክሬን ጄኔራል ስታፍም ተነግረዋል ።
ዩክሬን ቅዳሜ እለት ሰው አልባ አውሮፕላኖቿ በሩሲያ የነዳጅ ኩባንያ ሮስኔፍት የሚተዳደረውን የጄት ነዳጅ አምራች የሆነውን ኖቮኩይቢሼቭስክ ማጣሪያ መምታቷን የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ገልፀዋል ሲሉ የዘገቡት ሞስኮ ታይምስና ሌሎች ተነባቢነት ያላቸው አለምአቀፋዊ የዜና አዉታሮች ናቸዉ።
የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

Sponsored by
Surafel
Comments