2 months ago
በወረቀት ላይ የቀረው የ78 አመቱ ድንጋጌ!
*የዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች የመጀመሪያው ረቂቅ ድንጋጌ ይህንን ይመስል ነበር።
#ethiopia | በፈረንጆቹ 1948 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በፈረንሳይ ፓሪስ ተሰብስቦ ይህንን ታሪካዊ ሰነድ አጸደቀ።
ሰነዱ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ያስከተለውን ዘግናኝ እልቂትና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተከትሎ የተዘጋጀ ነበር።
ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ያስከተለውን ዘግናኝ እልቂት ተከትሎ ከእንግዲህ በሰው ልጅ ላይ ግፍ አይፈጸምም በሚል መርህ የተረቀቀው ይህ ታሪካዊ ሰነድ ዛሬ 78 አመት ሞልቶታል።
በጦርነትና በመብት ጥሰት በታመሰችው ዓለማችን ውስጥ
በወረቀት ላይ የቀረ ሰነድ
ሆኗል በሚል ከባድ ትችት እየቀረበበትም ይገኛል።
ይህ ሰነድ የሰው ልጅ መሠረታዊ መብቶችና ነጻነቶች በመላው ዓለም ያለ ምንም ልዩነት እንዲከበሩና እንዲጠበቁ ጠንካራ መሠረት ጥሏል።
ድንጋጌው የሰው ልጅ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ሊኖሩት የሚገቡ መሠረታዊ የሲቪል፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ የማህበራዊ እና የባህል መብቶችን በዝርዝር ያካተተ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ ስምምነት ነው።
የሰነዱ መጸደቅ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ጭቁን ህዝቦች፣ ለነጻነት ታጋዮች እና ለሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች የትግል መነሻና የፍትህ መጠየቂያ መሳሪያ በመሆን ሰፊ ሚና ተጫውቷል።
ዘር፣ ቀለም፣ ጾታ፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት ወይም የፖለቲካ አቋም ሳይለይ እያንዳንዱ የሰው ልጅ በእኩልነትና በነጻነት የመኖር መብት እንዳለው አሳውቋል።
ይህ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ የሰው ልጅ በታሪኩ ካስመዘገባቸው ታላላቅ ሁነቶች አንዱ ተደርጎ ይወሰዳል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #universal #declaration #humanrights #democracy #france #paris #inherited

Harar Jugol – The Living Museum
ሐረር ጁጎል – ሕያው ሙዚየም
#ethiopia | ሐረር በየዕለቱ ሰላም፣ መቻቻል እና አብሮነት የሚኖሩባት ከተማ ናት።
ሐረር በዓለም ላይ ሦስት የዓለም ቅርስ እውቅናዎችን ያጎናጸፈች ልዩ ታሪካዊ ከተማ ናት።
መዲናቱል አውሊያ – የቅዱሳን ከተማ
የምሥራቅ አፍሪካ ቲምቡክቱ
የታሪካዊው የአዳል ሱልጣኔት ዋና ከተማ
የምሥራቅ አፍሪካ ታሪካዊ የንግድ ማዕከል
በእስልምና ዓለም አራተኛዋ ቅድስት ከተማ በመሆን የምትከበር
የድሮውና የዘመናዊው ዓለም የሚገናኙባት ልዩ ከተማ
የሐረርን የበለጸገ ታሪክ፣ ባህል፣ ልዩ የስነ-ሕንፃ ቅርስ እና እንግዳ ተቀባይነት ለመመስከር ይጎብኙ። በየአደባባዩ ታሪክ ይነገራል፤ እያንዳንዱ ጉብኝትም የማይረሳ ተሞክሮ ይሆናል።
Harar is the City of Peace, Tolerance, and Solidarity, where these values are lived every day.
A rare city embraced by three UNESCO World Heritage recognitions, Harar is a treasure unlike any other.
Harar Medinat al-Awliya – The City of Saints
The Timbuktu of East Africa
Former capital of the Adal Sultanate
A historic center of East African trade
Revered as the fourth holiest city in Islam
Where the old meets the new in perfect harmony
Visit Harar to discover its rich history, vibrant culture, remarkable architecture, and warm hospitality. Every corner tells a story, and every visit becomes an unforgettable experience.
ሐረር በዩኔስኮ (UNESCO) በአንድ የዓለም ቅርስነት ዕውቅና የተሰጠው ሲሆን ይህም "ሐረር ጁጎል፣ የተመሸገች ታሪካዊ ከተማ" በመባል ይታወቃል። እ.ኤ.አ. በ2006 "ሐረር ጁጎል፣ የተመሸገች ታሪካዊ ከተማ" በሚል ኦፊሴላዊ ስም በዓለም ቅርስነት መዝገብ ውስጥ ሰፍሯል።
ይህ ስፍራ አንድ የዓለም ቅርስ ቢሆንም፣ ዩኔስኮ ለዚህ ቦታ "የላቀ ሁለንተናዊ እሴት" (Outstanding Universal Value) የሰጠው በሦስት ዋና ዋና የባህል መስፈርቶች (iv እና v) ላይ በመመስረት ነው።
1. ልዩ የሕንፃ ጥበብ ውህደት
ሐረር የአፍሪካ እና የእስልምና ወጎች ያልተለመደ ውህደትን ትወክላለች። የከተማዋ አቀማመጥ እና የ"ሐረሪ" ቤቶች ዲዛይን—በመሃል ላይ በሚገኙ ግቢዎች እና ውስጣዊ ግድግዳዎቻቸው ላይ በሚታዩ ውስብስብ እና ያሸበረቁ የእንጨት ቅርጻ ቅርጾች የሚታወቁ—በክልሉ ከሚገኙ ሌሎች የእስልምና ከተሞች የተለዩ ያደርጓታል። ይህም የኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች እና የሰፊው የእስልምና ዓለም ለዘመናት የነበራቸው መስተጋብር ውጤት የሆነ ልዩ ማንነትን ፈጥሯል።
2. ልዩ የሆነ የሃይማኖት ፋይዳ
ብዙውን ጊዜ በእስልምና አራተኛዋ የተቀደሰች ከተማ ተብላ የምትጠራው (ከመካ፣ ከመዲና እና ከኢየሩሳሌም በመቀጠል)፣ ሐረር ትልቅ መንፈሳዊ ማዕከል ናት። በከተማዋ ግንብ ውስጥ እጅግ በጣም ብዙ የሃይማኖት ስፍራዎች ይገኛሉ፦
ሦስቱ ከ10ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የቆዩትን ጨምሮ 82 መስጊዶች።
ለአካባቢው ቅዱሳን እና እስላማዊ ታላላቅ ሰዎች የተገነቡ 102 መቃብሮች (ሸሪዎች)።
3. "ሕያው" የሆነ ታሪካዊ የከተማ ገጽታ
እንደ ብዙዎቹ የቅርስ ስፍራዎች ሳይሆን፣ ሐረር የመካከለኛው ዘመን የከተማ አወቃቀሯን በመጠበቅ እንደ ዘመናዊ የባህል ማዕከል የምታገለግል "ሕያው" የቅርስ ከተማ ናት። በ13ኛው እና በ16ኛው ክፍለ ዘመን መካከል የተገነባው "ጁጎል" (የመከላከያ ግንብ)፣ አሁንም የድሮዋን ታሪካዊ ከተማ ይከብባል። ይህም የባህላዊ ማህበራዊ አደረጃጀትን፣ የመንገድ አቀማመጥን እና ቀደም ሲል ኢትዮጵያን ከአረብ ባሕረ ገብ መሬት እና ከዓለም ገበያዎች ጋር ያገናኙ የነበሩ ጥንታዊ የንግድ መስመሮችን ጠብቆ እንዲቆይ አድርጓል።
ሐረር በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ዘጠኝ የዓለም ቅርስ ቦታዎች አንዷ ነች። ሌሎችም የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የስምየን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ የአክሱም ሥልጣኔ፣ የፋሲል ግቢ (ጎንደር)፣ የአዋሽ ሸለቆ፣ የታችኛው ኦሞ ሸለቆ፣ የቲያ ሐውልቶች እና የኮንሶ የባህል መልክዓ ምድር ይገኙበታል።
Harar is officially recognized by UNESCO as a single World Heritage site: Harar Jugol, the Fortified Historic Town. It was inscribed on the World Heritage List in 2006 under the official name Harar Jugol, the Fortified Historic Town.
While it is a single site, UNESCO’s recognition is based on three primary cultural criteria (iv and v) that define why it holds "Outstanding Universal Value":
1. Unique Architectural Synthesis
Harar represents an exceptional fusion of African and Islamic traditions. Its urban layout and "Harari" house designs—characterized by central courtyards and intricate, colorful interior woodwork—are distinct from other Islamic cities in the region. This creates a unique architectural identity resulting from centuries of interaction between the Ethiopian highlands and the wider Muslim world.
2. Exceptional Religious Significance
Often described as the fourth holiest city in Islam (after Mecca, Medina, and Jerusalem), Harar serves as a major spiritual center. Within its walls, the city contains an extraordinary concentration of religious sites:
82 mosques, three of which date back to the 10th century.
102 shrines dedicated to local saints and Islamic figures.
3. A "Living" Historic Urban Landscape
Unlike many archeological sites, Harar is a "living" heritage city that has preserved its medieval urban fabric while functioning as a modern cultural hub. Its "Jugol" (defensive wall), built between the 13th and 16th centuries, still encloses the historic old town, maintaining the traditional social organization, street patterns, and ancient trade routes that once connected Ethiopia to the Arabian Peninsula and global markets.
Harar is one of nine total recognitions in the country. The others include the Rock-Hewn Churches of Lalibela, the Simien Mountains National Park, the Kingdom of Aksum, Fasil Ghebbi (Gondar), the Lower Valley of the Awash, the Lower Omo Valley, the Tiya Stelae, and the Konso Cultural Landscape.
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#visitharar #hararjugol #ethiopia #unesco #heritage #culture #tourism #landoforigins #ሐረር #የዓለም_ቅርስ #ቱሪዝም

5 months ago
79ኛዉ የዓለም ጤና ጉባኤ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ እየተካሄደ ይገኛል #wha79
_____________
በጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የተመራዉ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በጄኔቫ እየተካሄደ በለዉ 79ኛዉ የዓለም ጤና ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
በጉባኤዉ ላይ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በቅርቡ ይፋ የሆነዉ የህብረተሰብ ጤና ዳሰሳ ጥናት ግኝት መሰረት ኢትዮጵያ የእናቶችና ህጻናት ሞትን በመቀነስ ረገድ አመርቂ ዉጤት ማስመዝገቧን በመግለጽ በቀጣይም አለም አቀፍ የጤና ተደራሽነትን በማረጋገጥ ለመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ ጠንካራ የጤና ስርዓት እንዲፈጠር በትጋት እንደሚሰራ አጽንኦት በመስጠት ተናግረዋል።
በመላዉ ህብረተሰብ ተሳትፎና የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ቅንጅት እንዲሁም የጤና ባለሙያዉን ተነሳሽነትና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የእናቶችና ህጸናት ጤናን በቀጣይነት ማሻሻል፣ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መከላከልና መቆጣጠር፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ጥራት ያለዉ የጤና አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆን በትኩረት እንደሚሰራ የገለጹት ሚኒስትሯ ኢትዮጵያ ቀጣይነት ያለዉ የጤና ልማት ግቦችን ለማሳካት ከዓለም ጤና ድርጅት፣ ከአፍርካ ህብረት፣ ከሀገራት፣ ከሀገር በቀልና አለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች እንዲሁም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።
The 79th World Health Assembly is being held in Geneva, Switzerland
______________
The Ethiopian delegation led by Health Minister Dr. Mekdes Daba is participating in the 79th World Health Assembly being held in Geneva.
Health Minister Dr. Mekdes Daba, who made a speech at the assembly, stated that according to the recently released public health survey findings, Ethiopia has recorded encouraging results in reducing maternal and child mortality, and emphasized that in the future, by ensuring universal health coverage, high attention will be given to primary health care to diligently work towards creating a strong health system.
The Minister stated that focus will be given to continuously improving maternal and child health through the participation of the entire community and the coordination of relevant stakeholders, as well as by ensuring the motivation and benefit of health professionals, and preventing and controlling communicable and non-communicable diseases, and making quality health services accessible with the help of modern technology: also expressed that Ethiopia is committed to working in coordination with the World Health Organization, the African Union, countries, local and international partner organizations, as well as all stakeholders to achieve the sustainable health development goals.

Abebe Tilahun culture & Sport:
ለፈረንጅ ሚስቶች የቆመች ሐውልት‼️
የመጽሐፉ ርዕስ፦ የፈረንጅ ሚስት
ደራሲት፦ እስከዳር ግርማይ
የገጽ ብዛት ፦ 119
የመጽሐፉ ዋጋ ፦ 150 ብር
እትም፦ 3ኛ /2017 ዓ.ም
ዘውግ፦ ግለ ማስታወሻ (Memoir)+
አርታኢያን፦ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል እና አርቲስት አዜብ ወርቁ
👉መንደርደሪያ
ካርል ሮጀርስ (Carl Rogers) የተባለው ታዋቂው አሜሪካዊ የሥነ-ልቦና ባለሙያ "On Becoming a Person" በተሰኘ መጽሐፉ ላይ በሰዎች መካከል ያለውን ጥልቅ ግንኙነት በማጥናት እንዲህ ይላል። “What is most personal is most universal.” ፦ “እጅግ ሲበዛ ግላዊ የሆነው ነገር፣ እጅግ ሲበዛ ዓለማቀፋዊ ነው።”
ግለ-ማስታወሻ (Memoir)፤ ከሕይወት ውስጥ አንድን ወሳኝ ክስተት፣ ስሜት ወይም ጭብጥ (Theme) መርጦ ይተነትናል። ትኩረቱ "ከገጠመኝ ነገር ምን ተማርኩ? ምን ተሰማኝ?" የሚል ነው። በሌላ አነጋገር ግለ-ማስታወሻ ከታሪክ ይልቅ ትርጓሜና ስሜት ላይ ያተኩራል።
አንድ ሰው ለብቻው የሚሰማው፣ ለሌላ ሰው ለመናገር የሚፈራው ወይም "እኔ ብቻ ነኝ እንዲህ የሚሰማኝ" ብሎ የሚያስበው የግል ስሜት (ለምሳሌ፦ የፍርሃት፣ የብቸኝነት ስሜት፣ ወይም የናፍቆት፣ የመበሳጨትና የመብከንከን ስሜት) በሚገርም ሁኔታ ሌሎች ሰዎችም በውስጣቸው የሚሰማቸው ነው።
ስለሆነም ጸሐፊዋ እስከዳር ስለ ራሷና በዙሪያዋ ስላሉ ተመሳሳይ ሰዎች እጅግ ጥብቅና ግላዊ የሆኑ ጉዳዮችን በሐቀኝነት ስትናገር፣ በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች በታሪኳ ውስጥ የራሳቸውን ስሜት አግኝተውታል። የሥነ-ልቦና ጠበብት አንድ ሰው ወደ ራሱ ማንነት (Inner self) በጥልቀት በወረደ ቁጥር፣ ከግል ማንነቱ ባለፈ የሰው ልጅን የጋራ ማንነት (Collective Human Experience) ያገኛል ብለው ያምናሉና በፈረንጅ ሚስት የሆነውም ይሄው ነው።
ሌላኛው ጄምስ ጆይስ (James Joyce)የተባለ ምሁር "በተለየው (in the particular) ውስጥ ሁልጊዜም ዓለማቀፋዊውን (the universal) ነገር እናገኛለን።" በማለት በሥነ-ጽሑፍ ሥራዎቹ የግል ተሞክሮን ማዕከል ማድረጉን ገልጿል። እንዲሁም ራልፍ ዋልዶ ኤመርሰን (Ralph Waldo Emerson) "በገዛ ልብህ ውስጥ የምታምነው እውነት ለሁሉም ሰዎች እውነት ነው።" በሚል ሀሳብ ተመሳሳይ ፍልስፍናን አራምዷል።
በአጠቃላይ አባባሉ "የሰው ልጅ ስሜትና ተፈጥሮ በየትኛውም ቦታ አንድ ነው" የሚለውን መሠረታዊ እውነት የሚያሳይ ነው። የፈረንጅ ሚስት የሚለው ግለ-ማስታወሻ በራስ ሕይወት መስኮትነት ዓለምን የማሳያ ጥበብ ሆኖ ብቅ ብሏል። ጸሐፊዋ በራሷ ሕይወት ውስጥ ያለውን ትርጉም ስትፈልግ፣ አንባቢው ደግሞ በጸሐፊው ታሪክ ውስጥ የራሱንና የማኅበረሰቡን ሕይወት ያያል፣ ይታዘባል።
የፈረንጅ ሚስት
👉ግላዊና ዓለማቀፋዊ ሀሳብ፤ ጸሐፊዋ ስለ ራሷ ብቻ ስታወራ ለአንባቢው አሰልቺ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በግል ሕይወቷ በፈረንጅ ሚስትነቷ፣ በኢትዮጵያዊነቷ፣ የደረሰባትን ሐዘን፣ ፍቅር፣ ክህደት ወይም መገለል በሐቀኝነት ስለገለጠችው፣ አንባቢያን በራሳቸው ሕይወት ውስጥ ተመሳሳይ ስሜት አጋጥሟቸው ስለሚያውቅ ከጸሐፊዋ ጋር፣ እንደግል በሀሳብ፣ እንደማኅበረሰብ በአባልነት ይቆራኛሉ።
ሰው ወደ ራሱ ውስጠት በጥልቀት በቆፈረ ቁጥር፣ የሁሉንም ሰው የጋራ ምንጭ ያገኛል። የራስን እውነተኛ ስሜት፣ ስቃይ እና ደስታ መፈለግ እና እዚያ ጥልቀት ላይ ሲደርሱ የምናገኘው ራስን ብቻ ሳይሆን መላውን የሰው ልጅ የሚያገናኘውን የጋራ ክር ነው። ለዚህ ነው ግላዊ ማስታወሻዎች (Memoirs) በሚገባ ተቆፍረው ሲጻፉ ዓለምን ሁሉ የመንካት አቅም የሚኖራቸው።
በሥነ-ጽሑፍ እና በፈጠራ ድርሰት ዓለም ውስጥ በስፋት የምትታወቀው አሜሪካዊት ጸሐፊ ማያ አንጄሉ (Maya Angelou) “In the particular is contained the universal.” ፦ በተለየው/በግል ታሪክ ውስጥ፣ ዓለማቀፋዊው እውነት ይገኛል። ብላለች ።
ይህች የፈረንጅ ሚስት መጽሐፍ ከኢትዮጵያዊ ወንድ ውጭ ላገባችሁ ቀወል ስም የፈረንጅ ሚስት ለምትባሉ ሁሉ ሴቶች የቆመች ቅልብጭ ያለች ሐውልት ናት።
👉በፈረንጅ ሚስት መጽሐፍ ውስጥ ፤
ሐቀኝነት (Honesty)አለ፦ ግለ-ማስታወሻ ጸሐፊዋ ራሷን ብቻ ያሞግሰችበት ሳይሆን፣ ድክመትና ስህተቶችንም ጭምር የገለጥችበት መጽሐፍ ነው። ሐቀኝነት ከሌለ አንባቢው በታሪኩ አይመሰጥም።
የራስ መተማመኗን ፈረንጅ የማግባት ውጤት ሲያደርጉት፤ ሐበሻ ብታገባ ኖሮ በዚህ የራስ መተማመኗ ድሮ እንደሚፈታት ሲያሙላት በስላቅ ሐቋን ትጠይቃለች።
"እውነት የሀገሬ ሴቶች ታዋቂ፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ እና በራሳችሁ
የምትተማመኑ ከሆናችሁ ትዳራችሁ አይጸናም?
ደመወዛችሁ ከባለቤታችሁ ደመወዝ ሲበልጥ፣ ሥልጣናችሁ ከትዳራችሁ በላይ ሲገዝፍ ትፋታላችሁ?
ወይስ ትዳራችሁን መርጣችሁ፣ የመጣላችሁን ዕድል አሳልፋችሁ ለወንድ እና ላላገቡ ሴቶች ትሰጣላችሁ?
የሀገሬ ወንዶችስ? በሥራ፣ በደመወዝ ወይም በሥልጣን የምትበልጣችሁን ሴት ማግባት ትፈራላችሁ እንዴ?"
መልስ አትፈልግም።
ይልቁንስ ደራሲዋ ጥያቄዎቹን የምታቀርበው ምላሽ ፈልጋ ሳይሆን፣ ማኅበረሰቡን በመስታወት ፊት አቁማ ራሱን እንዲታዘብ ለማድረግ ነው።
ጭብጥ (Theme)አለ፦ ታሪኳ የሚሽከረከርበት አንድ ማዕከላዊ እውነት አለው ። ማዕከላዊ እውነቷ በማኅበረሰባችን ዘንድ ለፈረንጅ ሚስት ያለውን ስሁት አመለካከት ማረም፣ እውነቷንና ጽናቷን በመግለጽ ማንነቷን ማሳየት ነው። ለእያንዳንዱ ገጠመኟ በተግባር የተፈጸመ ምሳሌ ያልደበዘዘ ትውስታ ተቀምጧል ።
በማኅበረሰባችን ዘንድ የፈረንጅ ሚስትን ከሚያራክስበት ዝቅጠታዊ ልማድ የባሰ የሀብታም ቅምጥን የሚያሞግስበትና የሚያከብርበት የስብእና ንጥፈት እንዴት እንዳብከነከናት በሚቆጠቁጥ መልኩ የማዕከላዊ ጭብጡ ማጠንጠኛ ሆኗል ።
ደሞ ለምን ፈረንጅ አገባሽ ? እያሉ የጅል ጥያቄ ለሚጠይቁ አድርቅ ጋዜጠኞች ጥያቄን በጥያቄ በመመለስ በጥያቄያቸው እንዲያፍሩ የምታደርግበት ጥበብ የፈረንጁ ባሏ ምክርና የጭብጧ ማጠናከሪያ ነበር።
"ባለቤቴ ሁል ጊዜ የማይደረስ ጥያቄ ለሚጠይቅሽ ሰው፤ የጠየቀሽን ጥያቄ መልሰሽ ራሱን ጠይቂው። መልሱ ካላጠገበሽ ምን ማለትህ ነው? ብለሽ ይበልጥ እንዲያብራራልሽ እንደገና ጠይቂው። ስህተቱን
እስኪረዳው ተፋተኚው። እንደዚህ ዐይነት ሰዎች ከአምስት
ጥያቄዎች በላይ መመለስ አይችሉም፤ የሚለኝን ሳስበው ተግባራዊ እያደረግኩ።" ትለናለች። (ገጽ34)
ጥበባዊ አቀራረብ አለ፦ ምንም እንኳን እውነተኛ ታሪክ ቢሆንም፣ እንደ ልብ-ወለድ (Fiction) የታሪክ አወቃቀር፣ ገጸ-ባህሪያት አሳሳል እና የቃላት ምርጫ (Imagery) ተጠቀማለች። እንደ ገጸ ባሕርይ ራሷን እና በዙሪያዋ ያሉ ተመሳሳይ ሕይወት የሚጋሩ ወዳጆቿን፣ ቤተሰቦቿን እና በመንገዷ የገጠሟትን አካታለች። የታሪክ አወቃቀሩ ከአንዱ የሕይወት ገጠመኝ ወደ ሌላኛው የሕይወት ገጠመኝ እየተሻገረች፣ በትውስታ እያጀበች በምሳሌ አዋቅራ የልቧን እውነት የሕይወቷን ትርክት ቀንጭባ አቅርባዋለች።
የቃላት አመራረጧ ትኩሳቷን በመግለጥ እንደ እሳት የሚጋረፉ ፣ ስታዝን የሚለዝቡ፣ ስትቆጣ የሚንጣጡ ቃላት ናቸው።
ለምሳሌ የሀብታም ቅምጥን የገለጠችበትን ቃላት ተመልከቱ፦ "የሀብታም ቅምጥ የከተማው ሁሉ ወንድ የሚመኛት፣ ያሳደጓት የሰፈር ጎረምሶች ዓይናቸው እያየ ለባለጸጋ አሳልፈው በመስጠታቸው የሚቆጩባት፣ ዘመድ አዝማዶቿ የእሷ ስኬት የልጆቻቸው ባለመሆኑ የሚቀኑባት፣ የሰፈሩ ሰዎች ለአቅመ ሔዋን ላልደረሱ ልጆቻቸው "አርአያነቷን" እንዲከተሉ ጀብዳቸውን የሚነግሩላት፤ በየቦታው ትንሽዬ "ፈጣሪ" ሆና ብዙ "ደቀ መዛሙርት" ያፈራች ሴት ናት።" (ገጽ 27)
ውስጣዊ ሙግት (Internal Dialogue/ አለ፦ በሆነባት በተደረገባት ነገር ብቻ ሳይሆን፤ የወጣችበት ማኅበረሰብ ግንዛቤ ባለበት ቆሞ መቅረት ጭምር ሲያብሰከስካት ፤ እንደግል መብቷን፣ እንደማኅበረሰብ ውበቷን ስትገፈፍ የምትናገራቸው ቃላት የውስጧን መብከንከን ይገልጻሉ።
"የማዝነው፤ ማኅበረሰባችን በየመንገዱ መሰደቧን እንዳላየ እንዳልሰማ ሆኖ ስለሚያልፋት ብቻ አይደለም ። ከሐበሻ ወንድ ወጭ ሲሆን በፍቅር የማትወድቅ፣ ከሀገሯ ቋንቋ በቀር የፍቅር ቃላት የማትሰማ፣ ጠረን ለምዳ የማትሸነፍ ናት፤ ብለው በመወሰናቸውና የስሜት ሕዋሳቷ ለሌላ ሀገር ዜጋም ቢሆን እንደሚሠሩ ባለማወቃቸውም እንጂ!" (ገጽ16)
"ውጭ ሀገር ስንኖር አለመከበራችን በምንም መልኩ ልክ አይደለም፤ በሰው ሀገር ስንከፋ የሚሰማን ስሜት ፣ ከራሳችን ሀገር ከሚደርስብን የጥቃት ስሜት ጋር ካነጻጸርነው ግን፣ የሕመሙ ክብደት በሰው ሀገር
ሲሆን ይቀንሳል።
ሀገር ያስከፋን ጊዜ ግን ወዴት አቤት ይባላል? የራስ ሕዝብስ ለማን ይከሰሳል?" እያለች ምሯን ትናገራለች።
እናቴ አሳዛኝና አንጀት ቆራጭ ነገሮች ሲገጥሟት፦ "ከቀላድም ባይረዝም ከመጫኛም ባይበልጥ፤
አንጀት ያልቅ የለም ወይ ሲቆረጥ ሲቆረጥ።" ትላለች ።
የማኅበረሰባዊ መገፋት አንጀት ይቆርጣል ፤ አይመልሰኝ አሰኝቶ ድንጋይ ያስወረውራል። በጊዜ ሊታረም ከዘመኑ ጋርም ሊዘምን የሚገባ እንጅ የምናጌጥበት ነውር መሆን የለበትም ።
👉በፈረንጅ ሚስት መጽሐፍ
ደራሲዋ እስከዳር ግርማይና መሰል የፈረንጅ ሚስቶች ያለፈና ያለን ቁስል በቃላት አስጊጣ በመግለጧ ግላዊ እፎይታ ፣ ሕሊናዊ ፈውስ አግኝተውበታል፤ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ።
በመሰል ፈተና ውስጥ ያሉ ሰዎች የግለ ማስታወሻዎቹን ሂደትና መፍትሔ አይተው ተስፋ የሚሰጥ ትምህርት ያገኛሉ። በማኅበረሰባዊ ሂሷም ብዙዎች ራሳቸውን እንዲታዘቡ ራሳቸውን እንዲመረምሩና እንዲታረሙ ኮርኩራለች።
እስከዳር በራሷ የተወሰነ ዘመንና ማኅበረሰብ ውስጥ ለፈረንጅ ሚስት የነበረን አመለካከት ለትውልድ በማስተላለፍ የታሪክ ምስክር በመሆን፤ ለፈረንጅ ሚስቶች ሐውልት አቁማለች።
ማጠቃለያ
ደራሲ እስከዳር ግርማይ በመጽሐፏ ውስጥ 'የፈረንጅ ሚስት' የሚለውን ስም ከስድብነት ወደ ማንነት (Identity)፣ ከማንነትም ወደ ተጋድሎ (Resistance) ቀይራዋለች። ይህ መጽሐፍ የአንድን ግለሰብ ሕይወት ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያዊነትን እና የዘመናዊነትን (Modernity) ግጭት፣ እንዲሁም የሴትነትን ነፃነት የሚፈትን፣ ማኅበረሰባዊ ሕጸፅን ነቅሶ የሚያሳይ መስታወት ነው።
👉እስከዬ አሁንም ያላወጣሽው ብዙ ግላዊ "የመሬማውያን ጉዳይ" አለና በጥልቀት ቆፍረሽ ታወጭው ዘንድ አደራ እላለሁ 🙏
👉የፈረንጅ ሚስት በዶክመንተሪ ቢዘጋጅ ደግሞ ከንባብ የራቀውና የስድብ መጋዘን ከሆነው የማኅበረሰብ ክፍል ውስጥ በእጁ ላይ ገብተሽ ትነግሪዋለሽ። የፈረንጅ ሚስት ማለት በምን የሕይወት ሸለቆ ውስጥ አልፋ ምርጫዋን የምታስከብር እንደሆነች ታሳያቸዋለሽ።
የሀብከ ብርሃኔ ጥላሁን

8 months ago
የደም ትስስርና የነፍስ ጩኸት፡ ከዐድዋ ተራሮች እስከ ጋርቬይ
ዐድዋ አንድ ሺ ጊዜ ቢነገር አንድ ሺ መልዕክት ያለው ድል ነው።ዓለም በአሥራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ ለጥቁር ሕዝቦች አስከፊ ነበረች። አፍሪካ በበርሊን የካርታ ጠረጴዛ ላይ እንደ ታረደ በሬ በቅርጫ ተከፋፍላ፣ ልጆቿ በገዛ ምድራቸው ባዕድ ሆነው ነበር።
በባሕር ማዶ፣ በአሜሪካና በካሪቢያን ደሴቶች፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጥቁሮች ከማንነታቸው ተላቀው፣ ስማቸው ተፍቆ፣ እንደ ቁስ ተቆጥረው በነጮች እርሻ ውስጥ በባርነት አለንጋ ይገረፉ ነበር። ጥቁር መሆን የውርደት፣ የዝቅተኝነትና የሽንፈት ምልክት ተደርጎ የታተመበት ያ ዘመን፣ ለብዙዎች ተስፋ የሞተበት ድቅድቅ ጨለማ ነበር።
ነገር ግን፣ በዚህ ሁሉ ስቃይና እንባ መካከል፣ ከአፍሪካ ቀንድ አንዲት ብርሃን ብልጭ አለች። ያቺ ብርሃን ከኢትዮጵያ ምድር የተገኘች "አድዋ" ትባላለች።
በዛ ዘመን የኢትዮጵያ ተራሮች በጭስና በደም ተሸፍነዋል። ንጉሠ ነገሥቱ ዳግማዊ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ፣ ገበሬውን፣ ቄሱን፣ ሸማኔውንና አርሶ አደሩን አስተባብረው ዘመናዊ መሣሪያ የታጠቀውን የጣሊያን ጦር ፊት ለፊት ተጋጠሙት። ያ ዛረም ድረስ ምናከብረው የድል ቀን ለነጭ ገዢዎች የውርደት፣ ለጥቁር ሕዝቦች ግን የትንሳኤ ቀን ነበር።
ድሉ ሲበሰር "ጥቁር ሰው ነጭን ማሸነፍ ይችላል!" የሚለው ዜና በባርነት ቀንበር ስር ላሉት ወንድሞቻችን የነፃነት ወንጌል ሆነ። ይህ ዜና ጃማይካ ደሴት ላይ ወደሚገኘውና ገና በልጅነቱ የዘሩን መገፋት እያየ ወደሚያለቅሰው ወጣቱ ማርከስ ጋርቬይ ደረሰ።
ማርከስ ጋርቬይ በጃማይካ ሲያድግ፣ በዙሪያው የሚያየው ድህነትን፣ ንቀትንና የጥቁርነትን ስብራት ነበር። ነገር ግን ስለ አድዋ ሲሰማ፣ በውስጡ አንድ ታላቅ እሳት ነደደ። ጋርቬይ ኢትዮጵያን በአካል አይቷት አያውቅም፤ ነገር ግን በልቡ ውስጥ ኢትዮጵያ "የእናት ምድር" ምልክት፣ የክብር ተራራ፣ የነፃነት መቅደስ ሆና ተቀረጸች።
ጋርቬይ "Universal Negro Improvement Association" (UNIA) የተባለውን ማኅበር ሲመሠርት፣ በቢሊዮን ለሚቆጠሩ ጥቁር ሕዝቦች የነገራቸው አንድ ትልቅ እውነት ነበር፦ "እናንተ አገር የሌላችሁ ተቅበዝባዦች አይደላችሁም፤ እናንተ አድዋ ላይ ታሪክ የሠሩ የጀግኖች ወንድሞች ናችሁ!" እያለ ይጮኽ ነበር። ጋርቬይ ለጥቁር ሕዝቦች የሰጠው ሰንደቅ ዓላማ መነሻው የአድዋው የኢትዮጵያ ባንዲራ ነበር። ቀዩ—ስለ ነፃነት የፈሰሰውን ደም፣ ጥቁሩ—የሕዝቡን ክብር፣ አረንጓዴው ደግሞ የአፍሪካን ተስፋ ይወክሉ ነበር።
የጋርቬይ ሕይወት በመከራ የተሞላ ነበር። በዘረኞች እየታደነ፣ በገዛ ወንድሞቹ እየተከዳ፣ በእስር ቤት እየማቀቀ እንኳን፣ ከአንደበቱ የማይጠፋው ቃል "ኢትዮጵያ" የሚል ነበር። ጋርቬይ በሃርለም ጎዳናዎች ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጥቁሮችን ሰብስቦ ሲያሰልፍ "ወደ አፍሪካ ተመልከቱ" እያለ ሲቀሰቅስ፣ በዓይነ ሕሊናው የሚታየው የምኒልክ ጎራዴና የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ነበር።
ጋርቬይ እንዲህ ይል ነበር፦ "እግዚአብሔር ሆይ! ጥቁር ሕዝቦች በራሳቸው መርከብ ወደ እናት ምድራቸው ተመልሰው፣ እንደ አድዋ ጀግኖች በነፃነት የሚኖሩበትን ቀን አሳየኝ!" እርሱ ለዚህ ራዕይ ሲል ክብሩን፣ ገንዘቡንና ጤናውን መሥዋዕት አደረገ።
በወቅቱ የነበሩት ኃያላን መንግሥታት "ይህ ሰው ጥቁሮችን እያነቃ ነው" ብለው ፈሩት። በሐሰት ወንጀል ከሰሱት፣ አሰሩት፣ መጨረሻም ከአሜሪካ አባረሩት።
በ1930 ዓ.ም ንጉሥ ተፈሪ መኮንን "ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ" ተብለው ሲነግሡ፣ በካሪቢያን የሚገኙ የጋርቬይ ተከታዮች በደስታ አበዱ ። ጋርቬይ ቀድሞ "ጥቁር ንጉሥ በአፍሪካ ይነግሣል" ብሎ ተንብዮ ስለነበር፣ የንጉሡ መክሊት ለጋርቬይ ተከታዮች መሲሐዊ ትርጉም ነበረው።
ነገር ግን ታሪኩ እዚህ ላይ አሳዛኝ መልክ ይይዛል። በ1935 ዓ.ም ፋሺስት ጣሊያን በአድዋ የተሸነፈችውን ሽንፈት ለመበቀል በድጋሚ ኢትዮጵያን ስትወርር፣ ጋርቬይ በለንደን ስደት ላይ ነበር። ኢትዮጵያ ስትወረርና ንጉሡ ወደ ስደት ሲመጡ፣ ጋርቬይ ልቡ በሐዘን ተሰበረ። "እንዴት አባቶቻችን አድዋ ላይ ያስከበሩትን ክብር እናጣለን?" ብሎ ምርር ብሎ አለቀሰ። በወቅቱ ከንጉሡ ጋር የነበረው መጠነኛ የሐሳብ ልዩነትና የኢትዮጵያ በጣሊያን እጅ መውደቅ፣ ጋርቬይን ለከፍተኛ ሕመም ዳረገው።
ማርከስ ጋርቬይ በ1940 ዓ.ም በለንደን በብቸኝነት ሲያልፍ፣ የመጨረሻ ቃላቱ ስለ ጥቁር ሕዝብ አንድነትና ስለ አፍሪካ ነፃነት ነበሩ። የሚገርመውና ልብን የሚሰብረው፣ ጋርቬይ ሕይወቱን ሙሉ የዘመረላት፣ ስለ ክብሯ የታገለላትና መላ ሕይወቱን የሰጠላትን ኢትዮጵያን አንድም ቀን በአካል ሳይረግጣት መሞቱ ነው።
እርሱ ለጥቁር ሕዝቦች "ሥር" የሰጠ፣ ከአድዋ ተራሮች የተነሳውን የነፃነት እሳት ወደ ዓለም ያሰራጨ ታላቅ ነፍስ ነበር። እርሱ ሲሞት የነበረው ብቸኝነትና ድህነት፣ ለጥቁር ሕዝብ የከፈለው መሥዋዕትነት ትልቅነት ማረጋገጫ ነው።
ዛሬ የአፍሪካ ህብረት አዲስ አበባ ላይ ሲቆም፣ አድዋ የፓን አፍሪካኒዝም ማዕከል ስትሆን፣ የማርከስ ጋርቬይ መንፈስ በዚያ ደጃፍ ላይ ቆሞ ይታያል።
ጋርቬይ በአካል ባይመጣም፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የጃማይካና የዲያስፖራ ጥቁሮች ዛሬም "ኢትዮጵያ" እያሉ ይዘምራሉ።
አድዋ ላይ የፈሰሰው የኢትዮጵያውያን ደም፣ በካሪቢያንና በአሜሪካ ለነበሩት ባሮች የነፍስ ምግብ ሆኗቸዋል። ጋርቬይ ደግሞ ያንን ደም ወደ ርዕዮተ ዓለም ቀይሮ፣ ጥቁር ሕዝብ በራሱ እንዲተማመን አድርጓል።
አድዋ እና ጋርቬይ የአንድ ታሪክ ሁለት አካላት ናቸው። አድዋ—ሥጋዊና ሞራላዊ ነፃነትን ሲሰጠን፣ ጋርቬይ—መንፈሳዊና አእምሯዊ ነፃነትን ሰጥቶናል። ዛሬም ድረስ በጃማይካ የሚገኙ ራስተፋሪያውያን ወደ ኢትዮጵያ (ሻሸመኔ) ሲመጡ፣ "ወደ አገራችን ተመለስን" የሚሉት ለዚህ ነው።
የአድዋ ድል ባይኖር ጋርቬይ የሚሰብከው ክብር አይኖርም ነበር። ጋርቬይ ባይኖር ደግሞ የአድዋ ድል በኢትዮጵያ ተራሮች መካከል ብቻ ተቀብሮ በቀረ ነበር።
ዛሬ ላይ ሆነን ስናስበው፣ ጋርቬይ ማለት በአድዋ የተነሳው የነፃነት ብርሃን በዓለም ዙሪያ እንዲበራ ያደረገ ታላቅ የመብራት ማማ ነው።
ይህ ታሪክ የሚያስተምረን አንድ ትልቅ እውነት አለ፦ የአፍሪካውያንና የጥቁር ሕዝቦች ትስስር በውቅያኖስ የማይገደብ፣ በባርነት የማይበጠስና በጊዜ የማይደበዝዝ የደም ትስስር መሆኑን ነው። ጋርቬይ በለንደን ስደት ላይ ሆኖ የፈሰሰው እንባ፣ ዛሬ በአፍሪካ አንድነት ውስጥ ፍሬ አፍርቷል።
እኛ የአድዋ ልጆች፣ የማርከስ ጋርቬይ ራዕይ አደራዎች ነን። እርሱ ያላያትን ኢትዮጵያ እኛ ይዘናታል፤ እርሱ የናፈቃትን ነፃነት እኛ እየኖርንባት ነው። ይህን ታላቅ ክብር መጠበቅና ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ የታሪክ ግዴታችን ነው።
ክብር ለአድዋ ጀግኖች! ዝንተዓለም መታሰቢያነት ለአፍሪካ ኩራት ለማርከስ ጋርቬይ!

ፓን አፍሪካ ላይ ያተኮረ ዶክመንተሪ ተመረቀ
#ethiopia | በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን "ICC: Universal Justice Without Universality" ( ዓለም አቀፋዊነት የጎደለው ዓለም አቀፋዊ ፍትህ) የተሰኘ አዲስ ዘጋቢ ፊልም ዛሬ የካቲት 6 2018 በቱሊፕ ኦሎምፒያ ሆቴል ተመርቋል።
በዜግነት የጊኒ ተወላጅ የሆነው ታዋቂው ፓን አፍሪካኒስት ፊልም ሰሪ ባካሪ ካንቴ ዶክመንተሪውን ያዘጋጀ ሲሆን ነዋሪነቱም በፈረንሣይ ነው።
በጄኔሲስ ኢንተርቴይመንት የቀረበው ይህ ዘጋቢ ፊልም፣ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) አሰራር፣ ተአማኒነትና የፍትሐዊነት ጥያቄዎች ዙሪያ የሚያጠነጥን ነው።
የፊልም ባለሙያው ባካሪ ካንቴ በሲኒማቶግራፊ ሙያ ከ 20 አመት በላይ የቆየ ሲሆን ፊልሙንም ለማዘጋጀት 2 አመት ወስዶበታል።
ከአለምአቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አሠራር ጋር በተያያዘ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት የሚገኙ ባለሙያዎችን ቃለ መጠይቅ በማድረግ የቀረበው ይህ ዘጋቢ ፊልም በጉዳዩ ላይ መረጃ ለሚሹ ሁሉ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ነው።
ዶክመንተሪው ለዕይታ በቀረበበት ጊዜ የአፍሪካ ህብረት ባልደረቦችና ሌሎችም የፓን አፍሪካ ጉዳይ ይመለከተናል የሚሉ እንግዶች መታደማቸው ታውቋል።
ይህ ለ30 ደቂቃዎች የቆየው ዘጋቢ ፊልም በተለይም ፍርድ ቤቶች ከአፍሪካ አገራት ጋር ያለውን ግንኙነትና "ሁለንተናዊ ፍትህ" በሚለው መርህና በተግባር ባለው ልዩነት ላይ ያተኮሩ ጥልቅ ትንታኔዎችን አካቷል።
የዚህን ዶክመንተሪ ፊልም የምረቃ መርሀ ግብር ከአፍሪካውያን ወንድሞች ጋር በመሆን ያስተባበረው ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን (ዕዝራ እጅጉ) ሲሆን ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ለመርሀ ግብሩ መሳካት ትልቁን ድርሻ ወስዷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#ethiopia #africanunion #panafricanism #icc #justiceforafrica #bakarykante #documentary #addisababa #tewodajmedia #africaunited

Sponsored by
Surafel
9 months ago
የነገው ማህበረሰብ ዕጣ-ፈንታ፡ የጥንታዊ እሴቶች እና የዲጂታል ዘመናዊነት ፍልሚያ
የ21ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ቆመን ወደ ፊት ስንመለከት፣ የሰው ልጅ ማህበራዊ መዋቅር በታሪኩ አይቶት በማያውቀው የለውጥ ማዕበል ውስጥ ይገኛል። ዛሬ የምንኖርበት ዓለም በሃይማኖት፣ በባህል እና በዘመናዊነት ሶስትዮሽ ፍልሚያ የታጠረ ቢሆንም፣ ይህ ውጥረት ለወደፊቱ አዲስ ዓይነት የሰው ልጅ ማንነት መፈልፈያ እየሆነ ነው።
ሶሺዮሎጂስቶች እንደሚያስረዱት፣ ማንኛውም ማህበረሰብ ወደ "ሃይ-ቴክ" (High-tech) ስልጣኔ በሚሸጋገርበት ወቅት፣ በነባር እሴቶቹ እና በአዲሱ የዓለም ስርአት መካከል የሚፈጠረው ግጭት "የሽግግር ወቅት ቀውስ" (Transition Crisis) መባሉ አይቀርም። ይሁን እንጂ ይህ ቀውስ ውድቀትን ሳይሆን፣ የወደፊቱን የተራቀቀ ማህበረሰብ ለመፍጠር የሚያስችል "የህመም ወሊድ" ነው።
ዛሬ የምናየው የባህል እና የቴክኖሎጂ ግጭት፣ ነገ ለሚመጣው አዲስ ስልጣኔ መሰረት የሚጥል እንጂ ማንነታችንን የሚያጠፋ ብቻ ተደርጎ መወሰድ የለበትም።
የዊሊያም ኦግበርን "የባህል መዘግየት" (Cultural Lag) ፅንሰ-ሃሳብ በወደፊቱ ዓለም ውስጥ ይበልጥ እየጎላ ይመጣል። ቁሳዊ ቴክኖሎጂው በብርሃን ፍጥነት ሲገሰግስ—ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)፣ ባዮ-ቴክኖሎጂ እና የጠፈር ምርምር የዕለት ተዕለት ህይወታችን አካል ሲሆኑ—የሰው ልጅ አስተሳሰብና ስነ-ምግባር ግን አሁንም ወደ ኋላ እየቀረ ነው።
ዛሬ በእጃችን ያለው ስማርት ስልክ ነገ ወደ አእምሯችን የሚተከል ቺፕ ሊቀየር ይችላል፤ ነገር ግን ጥያቄው "ያንን ቴክኖሎጂ የምንመራበት የሞራል ልክ አለን ወይ?" የሚለው ነው። የነገው ማህበረሰብ ትልቁ ፈተና የቴክኖሎጂ እጥረት ሳይሆን፣ የሰለጠነ አእምሮ እጥረት ሊሆን ይችላል። ኦግበርን እንዳሳሰበው፣ በቴክኖሎጂያዊ ብቃት እና በመንፈሳዊ ብስለት መካከል ያለው ክፍተት ካልጠበበ፣ ማህበረሰቡ ወደ ትርምስ ማምራቱ አይቀርም።
ስለሆነም የወደፊቱ ትውልድ ስራ ዲጂታል መሆን ብቻ ሳይሆን፣ ያንን ዲጂታል ዓለም የሚመራበትን አዲስ "ሰብአዊ ስነ-ምግባር" (Digital Ethics) መቅረጽ መሆን አለበት።
ማክስ ዌበር "የዓለም አስማታዊነት ማጣት" (Disenchantment) ሲል የሰጋው ለምክንያታዊነት (Rationality) መስፋፋት ነበር። ሆኖም ግን ወደ ፊት በሄድን ቁጥር የምናየው እውነታ ሃይማኖት ከዘመናዊነት ጋር ተዋህዶ አዲስ መልክ ሲይዝ ነው።
የወደፊቱ ሃይማኖታዊ ማንነት ከመጻሕፍት ገጾች ወጥቶ ወደ ዲጂታል ህልውና (Virtual Reality) ይሸጋገራል። ሰዎች በአካል ሳይገናኙ በመንፈሳዊ ዓለም የሚተሳሰሩበት፣ ሃይማኖትና ቴክኖሎጂ የማይነጣጠሉበት ዘመን ላይ እንገኛለን። እዚህ ጋር ትልቁ ስጋት ሃይማኖት ለፖለቲካዊ መጠቀሚያነት መዋሉ ቢሆንም፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለሰው ልጅ የሞራል ኮምፓስ (Moral Compass) ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። ዘመናዊነት ሰውን ማሽን ለማድረግ ሲሞክር፣ እምነትና ባህል ደግሞ "ሰው" መሆናችንን የሚያስታውሱን ስሮች ሆነው ይቀጥላሉ።
የወደፊቱ ማህበረሰብ በእነዚህ ሁለት ዋልታዎች መካከል የሚኖር ሳይሆን፣ ሁለቱንም አጣጥሞ የሚጓዝ "ሁለንተናዊ ሰው" (Universal Human) ሊሆን ይገባዋል።
ኤሚል ዱርካይም የተነተነው "ማህበራዊ ትስስር" (Social Solidarity) በወደፊቱ ዓለም አዲስ ፈተና ይገጥመዋል። ግሎባላይዜሽን "እኔ" የሚል ግለኝነትን (Individualism) እያገነነ ባለበት በዚህ ወቅት፣ የጋራ ማንነት (Collectivism) እየደበዘዘ መጥቷል። ይህ ሁኔታ ሰውን ከማህበረሰቡ ነጥሎ የብቸኝነት ሰለባ ያደርገዋል። ነገር ግን የወደፊቱ ቴክኖሎጂ ሰዎችን በአዲስ መልክ የማስተሳሰር አቅም አለው። ቤተሰብ በአካል ባይገናኝም በዲጂታል ዓለም ተቀራርቦ የሚኖርበት፣ ባህል ከድንበር አልፎ ዓለም አቀፋዊ የሚሆንበት እድል ሰፊ ነው። ይሁን እንጂ ይህ የዲጂታል ትስስር እውነተኛውን ሰብአዊ መተሳሰብ እንዳይተካ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። የወደፊቱ ማህበረሰብ የሚገነባው በብረትና በኤሌክትሪክ ብቻ ሳይሆን፣ በሰዎች መካከል በሚኖር እውነተኛ ፍቅርና መግባባት ነው። ለዚህም ነው ከግለኝነት ይልቅ ወደ "እኛነት" የሚመልሰን የባህልና የሃይማኖት እሴት ለነገው ዓለም እጅግ አስፈላጊ የሚሆነው።
ጆርጅ ሪትዘር "ማክዶናልድዜሽን (McDonaldization) ሲል የገለጸው የባህል መመሳሰል አደጋ፣ የወደፊቱን ልዩ ልዩ ማንነቶች ስጋት ላይ ጥሏቸዋል። ዓለም ወደ አንድ ወጥ የፍጆታ ባህል ስትቀየር፣ የሀገር በቀል ጥበቦችና እሴቶች የመጥፋት እድላቸው ሰፊ ነው። ነገር ግን የወደፊቱ ንቁ ትውልድ ይህንን አደጋ ተረድቶ "ባህላዊ ህዳሴ" (Cultural Renaissance) ሊፈጥር ይችላል። ቴክኖሎጂን በመጠቀም የራስን ቋንቋ፣ ሙዚቃ እና ታሪክ ለዓለም ማስተዋወቅ ይቻላል። ባህል የሚፈስ ወንዝ እንደመሆኑ መጠን፣ ከዘመኑ ጋር እየተዋሃደ ካልሄደ ይደርቃል። የወደፊቱ ብልህ ማህበረሰብ የጥንቱን ጥበብ ከዘመኑ ሳይንስ ጋር አዋህዶ አዲስ "የማንነት ቀመር" ይፈጥራል።
ራሳችንን ከዓለም ሳንነጥል ነገር ግን ማንነታችንን ሳንለቅ የምንኖርበት "ግሎካል" (Glocal - Global + Local) አስተሳሰብ የነገው ዓለም መመሪያ ይሆናል።
የኧርቪንግ ጎፍማን "ድራማቱርጅ" ቲዎሪ በወደፊቱ ሜታቨርስ (Metaverse) ዓለም ውስጥ ይበልጥ ይገዝፋል።
ሰዎች የተለያዩ ማንነቶችን (Avatars) ይዘው የሚኖሩበት ዘመን ሲመጣ፣ "እውነተኛው ማንነታችን የትኛው ነው?" የሚለው ጥያቄ የነገው ትልቁ ስነ-ልቦናዊ ቀውስ ይሆናል። በማህበራዊ ሚዲያ የሚታየው ድራማ እና በውስጥ የሚሰማው ባዶነት ሰውን ወደ መካኒካዊ ህይወት እንዳይገፋው ስጋት አለ።
ይህንን ክፍተት የሚሞላው ደግሞ ወደ ውስጥ የሚመለከት መንፈሳዊነት እና እውነተኛ ባህላዊ እሴት ብቻ ነው። ቴክኖሎጂው ቢገዝፍም፣ የሰው ልጅ ፍቅርን፣ ርህራሄንና ቅንነትን መፈለጉ አይቀርም። ስለሆነም የወደፊቱ ስልጣኔ በውጫዊ ውበትና በቴክኖሎጂ ብልጭልጭነት ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በውስጣዊ ስብዕና ግንባታ ላይ ማተኮር ይኖርበታል።
በስተመጨረሻም፣ የወደፊቱ ማህበረሰብ እጣ ፈንታ የሚወሰነው ዛሬ በምናስቀምጠው መሰረት ላይ ነው። ቴክኖሎጂ ክንፋችን፣ ባህልና ሃይማኖት ደግሞ ስሮቻችን ናቸው። ክንፍ ብቻ ያለው ወፍ አርፎ የሚቆምበት ቅርንጫፍ የለውም፤ ስር ብቻ ያለው ዛፍ ደግሞ ሰማይን መድረስ አይችልም። የነገው ስኬታማ ትውልድ በአንድ እጁ አይፎን ይዞ በሌላ እጁ የጥንት መጻሕፍቱን የሚያነብ፣ በሳይንስ እያመነ በሃይማኖቱ የሚጸና፣ በዓለም አቀፍ መድረክ እየተወዳደረ ባህሉን የሚወድ "ባለ ሁለት ዓለም" ዜጋ ነው። ይህ ሚዛን ሲጠበቅ ብቻ ነው ከማንነት ቀውስ ወጥተን ወደ ታላቅነት የምንሸጋገረው። የወደፊቱ ታሪክ የሚጽፈው በቴክኖሎጂ መራቀቃችንን ብቻ ሳይሆን፣ በሰብአዊነታችን መላቃችንን ጭምር መሆን አለበት። ይህንን ሚዛናዊ ጉዞ ስንጀምር፣ የሽግግር ቀውሱ አብቅቶ የማንነት ብርሃን ይበራል።

11 months ago
የአለምአቀፍ የሴቶች መብት ስምምነት በሀገራችን የህግ ማእቀፍ እይታና አፈጻጸም አንጻር ያለው ክፍተት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ ወ/ሮ ቃልኪዳን አወቀ በማናቸውም ፌደራል ፍርድ ቤት ጠበቃና የህግ አማካሪ 0910683246
መግቢያ #ethiopia | ኢትዮጵያ የሴቶችን መብት ከማስከበር አንጻር የአለምአቀፍ ስምምነቶችን በማድረግ ቀዳሚ ተግባራት ፈጽማለች። በኢ.ፊ.ድ.ሪ ህገመንግስት አንቀጽ 13/2/ መሠረት የህጋችን አካል በማድረግ የራሷንም ህግ በማውጣት የሴቶችን መብት ለማስጠበቅ አስፈላጊውን ጥረት እያደረገች ነው። ይሁን እንጂ ህጉን በማስፈጸምም ሆነ መብቶቻቸውን ሙሉ ለሙሉ ከማስጠበቅ አንጻር ክፍተቶች የሚታዩ ሲሆን ይህን በዚህ አጭር ጽሁፍ የሚታይ ግንዛቤም ለማህበረሰቡ ለማሳደግ ቀርቧል።
. ፆታዊ ጥቃት ምንድን ነው?
ፆታዊ ጥቃት በሰዎች ላይ አካላዊ፣ ወሲባዊ ወይም ስነ ልቦናዊ ተብለው ሊከፈሉ ይችላሉ።
1.1 የሥነ-ልቦናዊ ጥቃት፡-
በቃላት ወይም ሞራል በሚነኩ አባባሎች ማሸማቀቅ እና ማስፈራት፣ በአካላዊ ጥቃት ወቅት በሚደርስባቸው የአካል ጉዳት ወይም ያልተፈለገ እርግዝና እና የጤና ጉድለት ምክንያት የሚከሰት የሥነ ልቦና አለመረጋጋት፣
1.2 ባህላዊ ጥቃት፡-
በባህል የሚፈፀም የውርስ ጋብቻ፣ ያለመውለድ ችግር ሴትን ብቻ ተጠያቂ አድርጎ በመውሰድ ከትዳር መፈናቀል፣ ልጆችን በማሳደግ ረገድ ሴቶች ከፍተኛውን ድርሻ መሸከም፣ በልጅነት ተገዶ መዳር፣
1.3ኢኮኖሚያዊ ጥቃት፡-
ሴቶችን በኢኮኖሚ ለመቆጣጠር የፋይናንስና የሃብት አማራጮችን መገደብ፣
1.4 ወሲባዊ ጥቃት፡-
ሃይልን በመጠቀም ያለፍላጓቷ የሚፈፀም ማንኛውም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ድርጊትና የግብረ ሥጋ ግንኙነት ድርጊትን የመሰሉ ለመልካም ፀባይ ተቃራኒ የሆኑ ድርጊቶችና ትንኮሳዎችን ፣ አስነዋሪ ለሆኑ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ድርጊቶች ማስገደድ
2. የፆታዊ ጥቃት የሚያስከትላቸው ችግሮች
2.1 የጤና የአካል ጉዳት፣ ሞት፣ ፌስቱላ፣ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ጨምሮ በተለያዩ በሽታዎች መያዝ፣ ላልተፈለገ እርግዝና፣ በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ ህመም እና በወሊድ ወቅት ለአደጋ መጋለጥ፡፡
2.1 የሥነ-ልቦናዊ ሀፍረት፣ ፀፀት፣ ድብርት፣ ፍርሃት፣ ራስን መጥላት፣ በራስ ያለመተማመን፣ አለመረጋጋት፣ ብቸኝነት፣ መገለልና መድሎ፣ የአእምሮ ህመም፣ ተስፋ መቁረጥና ሱሰኛነት፡፡
2.3 ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፆታዊ ጥቃት የተፈፀመባቸው ሴቶች ከትምህርት ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳታፊነት ራሳቸውን ማገለል፣ በኢኮኖሚ አምራችነት መቀነስና ኑሮቸውን በኢኮኖሚ ጥገኝነት መቀጠል፣ የቤተሰብ መበተንና መቃወስ፣ ለስደት፣ ለሌሎች በርካታ ሴቶችና ህፃናት ስጋት፣ አለመረጋጋት የበዛበት ማህበረሰብ እንዲፈጠር፡፡
2.4 በፍትህ ስርዓቱ ላይ ፆታዊ ጥቃት የተፈፀመባቸው ሴቶች ተገቢውን የሕግ ምላሽ እና ከለላ በማያገኙበት ጊዜ በሀገሪቱ ሕግና ሥርዓት ላይ ህብረተሰብ መፈጠር እና ፆታዊ ጥቃት የተፈፀመባቸው ሴቶች ለህግ አካላት ሪፖርት ከማድረግ መቆጠብ፡፡
2.5 የፆታዊ ጥቃት መንሰኤዎች ማህበረሰቡ በሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃት መቀበሉ፣ ኃላ ቀር የሆነ አስተሳሰቦች፣ ጎጂ ልማዳዊ ልምዶች፣ ማህበረሰቡ ስለ ሥርዓተ-ፆታ ያለው ግንዛቤ አነሳ መሆን፣ የሴቶችን መብቶች የሚያስከበሩ ህጎች አፈፃፀም አናሳ መሆን፣ የመጠጥ፣ የእጽና የተለያዩ ሱሶች ተጠቃሚነት፣ ልቅ የሆኑ የወሲብ ፊልሞች መስፋፋት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
2.6 ፆታዊ ጥቃት በማንና የት ይፈፀማል?
በቤተሰብ አባል፣ በጎረቤት፣ ጓደኛ፣ በትዳር አጋር፣ በሀይማኖት አባቶች፣ በመንግስት ባለስልጣናት እና ሌሎች በቅርብ በሚታወቁና በማይታወቁ ሰዎች፣
ጥቃቱ በማንኛዉም ቦታ የሚፈጸም ነዉ፡፡ በቤት ውስጥ፣ በትምህርት ቤት፣ በመንገድ፣ በሥራ ቦታ፣ ገበያ እና በሌሎች፡፡
2.7 ፆታዊ ጥቃትን ለማስቆም የተወሰዱ እርምጃዎች
አለም አቀፋዊ እርምጃዎች፡-
3. የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በሴቶች ላይ የሚፈፀም ጥቃትን 3. ለመከላከልና ለሴቶችና ህፃናት በቂ ጥበቃ ለመስጠት ሰነዶችን፣ መግለጫዎችን እና ስምምነቶችን አፅድቋል፡፡
3.1 ሁሉ ዓቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ/ Universal declaration on human right, 1948/
ይህ ሰነድ የሰዎች እኩል የሆነ ሰብዓዊ ክብርና መብትን እና ሁሉም ሰው ከአካላዊ ስቃይ ኢሰብአዊና ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ የመጠበቅ መብት እንዳለው አካቶ የያዘ አለምአቀፍ ስምምነት ነው፡፡
3.2 አለምአቀፍ የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች ስምምነት / International covenant on civil and political rights, 1966/
በዚህ ስምምነት ላይ በህይወት የመኖር መብትን፣ ከምንም አይነት አድልዎ የመጠበቅ መብትን፣ የአካል ደህንነትንና ነጻነት መብትን እውቅና የሰጠ ሰነድ ነው፡፡
3.4 አለምአቀፍ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ባህላዊ መብቶች ስምምነት/ International covenant on economic, social and cultural rights, 1966/
ይህ ስምምነት ከምንም አይነት አድልዎ የመጠበቅ መብትንና ሚዛናዊና አመቺ የስራ ቦታ የማግኘት መብትን ያካተተ ነው፡፡ ይህ በተዘዋዋሪ ሴቶች በስራ ቦታ ሊፈጸምባቸው ከሚችለው ወሲባዊ ትንኮሳ ጥበቃ ያደርጋል፡፡
3.5 በሴቶች ላይ የሚደረጉ ማናቸውም ዓይነት ልዩነት ወይም አድሎ ለማስወገድ የወጣ ስምምነት (CEDAW, 1979)
ይህም ስምምነት በፆታ ላይ የተመሰረተን አድሎኣዊ ልዩነት፣ ገደብ ወይም ማግለልን በመከልከል አባል መንግስታት በማናቸውም መልኩ የሚፈፀም ልዩነት ለማስወገድ የሚያስችል እርምጃዎችን እንዲወስዱ ያስገድዳል፡፡
3.6 የአፍሪካ ህብረት የመመስረቻ ሰነድ አንቀፅ 4/1 ላይ ማንኛውም የህብረቱ አባል ሀገራት
የሴቶችን እኩልነት የማህበር ግዴታ እንዳለባቸው በመርህ ደረጃ ያስቀምጣል፡፡
3.7 አፍሪካ የሰብዓዊና የህዝቦች መብቶች ቻርተርና የአፍሪካ ሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል/ Protocol to the African charter on human and people’s rights on the right of women, 2003/
ይህ ፕሮቶኮል በሴቶች ላይ የሚደረጉ አድሏዊ ልዩነቶችን ለማስወገድ የወጣው አለም አቀፍ ስምምነት ከያዛቸው ድንጋጌዎች ጋር ተመሳሳይ ድንጋጌዎችን የያዘ ሲሆን የአፍሪካን ሴቶች ነባራዊ ሁኔታ ማለትም በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የሚደርስባቸውን በደልና የስርዓተ-ጾታ ችግሮች ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
3.8 የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት
በአንቀጽ 35/4 በሴቶች ላይ አካላዊ አእምሮዊ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ጎጂ ልማዳዊ ድረጊቶች፣ ህጎችና ልምዶች አንዲወገዱ መንግስት ኃላፊነት እንዳለበት ይገልፃል፡፡
3.9 የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ወንጀል ህግ
የወንጀል ህጉ ፆታዊ ጥቃት የወንጀል ድርጊቶች መሆናቸውን በመደንገግ ሊያስቀጡ የሚችሉትን ቅጣት በማካተት ደንግጓል፡፡ ለመጥቀስ ያህል በግብረ-ሥጋ ነፃነትና ንፅህና ላይ የሚፈጸሙ ወጀሎችን (አንቀጽ 620-628)፣ ለተፈጥሮ በተቃራኒ ባህሪይ የሆኑ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ድረጊቶችን በተመለከተ (አንቀጽ 629-632)፣ የተለያዩ ጎጂ ልማዳዊ ድረጊቶችን (አንቀጽ 561-562) ፣ ጠለፋ (አንቀጽ 587-590)፣ ያለእድሜ ጋብቻ አንቀጽ (647-648)፣ አካል ላይ ጉዳት ማድረስ (አንቀጽ 555-560)፣ ግንኙነት ባላቸዉ ሰዎች መካከል የሚፈጸም ጥቃት (አንቀጽ 564)፣ በሴቶችና ህጻናት መነገድ (አንቀጽ 597-599፣ የዝሙት ተግባር (አንቀጽ 635-638) በህጉ ለሴቶች መብትና ደህንነት ጥበቃ የሰጡ
ድነጋጌዎችን ናቸው፡፡
3.10 የተሻሻለው የፌዴራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992
በጋብቻ፣ በልጅ አስተዳደግ፣ በሃብትና ንብረት አስተዳደር፣ በፍቺ ጉዳዩች ላይ ለሴቶች እኩልነት ትኩረት ተሰጥቷል፡፡
4. ከፍትህ ሚኒስትር እና ከፖሊስ ኮሚሽን ምን ይጠበቃል?
4.1 ወንጀልን መከላከል
ህብረተሰቡ “ፆታዊ ጥቃት መከላከል የእኔ ጉዳይ ነው፤ ይመለከታኛል” ይል ዘንድ በህዝብ አደረጃጀቶችን በመጠቀም እና በተለያዩ የመገናኛ ዜዴዎች የህብረተሰቡን ግንዛቤ በመቀየር ፆታዊ ጥቃት እንዳይፈፀም የመከላከል ስራ መስራት፡፡
እንዲሁም ወንጀልን ለመከላከል ከሚረዱ ዘዴዎች መካከል ወንጀል ፈፅመዉ ሲገኙ ቅጣት ከሚተላለፍባቸዉ ሰዎች ህብረተሰቡ ትምህርት በመዉሰድ ከወንጀሉ እንዲቆጠቡ በማድረግ ነዉ፡፡
የወንጀል ህግ ግቡም ወንጀል አድራጊዎቹ ተቀጥተዉ ሌላ ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡና ለሌሎች ማስተማርያ እንዲሆን ወይም እንዲታረሙ በማድረግ ወይም ተጨማሪ ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ እርምጃዎች እንዲወሰዱባቸዉ ለማድረግ ነዉ፡፡
ከዚህ አንፃር የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተቋም በአዋጅ የተሰጠዉን ስልጣን በመጠቀም በሴቶች የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ከፖሊስ ጋር በመሆን ምርመራ በማድረግ ክስ በመመመስረት እና የድርጊቱን ፈፃሚዎች ለፍርድ ቤት በማቅረብ ተመጣጣኝ የሆነ ቅጣት እንዲወሰን በማድረግ ህብረተሰቡ የፍርድ ቤቱን ቅጣት ውሳኔ እንዲያውቅ እና ራሱን ከድርጊቱ እንዲቆጥብ ማድረግ፡፡
4.2 ምላሽ ከመስጠት አንፃር
በአዲስ አበባ በአስሩም ክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኙ ምድብ ጽ/ቤቶች እና በድሬደዋ ምድብ ጽ/ቤት የተፈፀሙ ፆታዊ ጥቃት ወንጀሎችን ተገቢውን ምርመራን ከፖሊስ ጋር በመሆን ያካሄዳል ምርመራዉንም ከተጠናቀቀ በኃላ ፍርድ ቤት ክስ መስርቶ በማቅረብ እና ክርክር በማድረግ ወንጀል ፈፃሚው እንዲቀጣ የማድረግ ስራን ይሰራል፡፡
4.3 ከፍርድ ቤቶች ምን ይጠበቃል?
ፍርድ ቤቶች በእርግጥ ኃላፊነታቸው በህግ በፍሬ ነገርና በማስረጃ ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገ ቢሆንም ይህን ከማድረግ አንጻር አስፈላጊና ተገቢነት ያላቸውን የህገመንግስት፣ ስለሴቶች የተደረጉ አለምአቀፍ ስምምነቶች እንዲሁም የወንጀል ህጉንና አግባብነት ያለቸውን ህጎች መመሪያዎች መሠረት ባደረገ መልኩ ለሴቶች የተሰጠውን መብቶችን ከማስጠበቅ አንጻር አስፈላጊውን ማጣራት በማድርግ አስተማሪና ለሌላውም አስተማሪ የሆነ የቅጣት ውሳኔ ሊተላለፍ ያስፈልጋል።
5. የሴቶች ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች ለመከላከል የእኩልነት መብት ከማረጋገጥ አንጻር የአፈጻጸም ችግሮች
ሴቶች በህግ የተሰጣቸውን መብት ከማስጠበቅ አንጻር በተለይም በክልል በገጠር ውስጥ ከሚደርሱ ጥቃቶች አንጻር ህጎችን ተግባራዊ ለማድረግ ገና ሰፊ ስራዎች የሚጠበቅ ሲሆን ህጻናት ሴቶች እንኳን ከሚደርስባቸው ጥቃት ህይወታቸውን ቢያጡም እንኳን ይህን አድራጊው አካል ላይ በወንጀል የተቀመጠው ቅጣት የእድሜ ልክ ወይም እስከ 25 አመት ጽኑ እስራት ብቻ መሆኑ በሀገራችን ያሉ ህጎች ኢትዮጵያ በአለምአቀፍ ደረጃ የፈረመቻቸውን የሴቶችን መብቶቾ በህጎቿ አቅፋ የመተግበር ላይ ልልነት የሚታይ መሆኑን ማስተዋል የሚቻል ሲሆን ከዚህ ረገድ ህግ አውጪዎች ሊያስቡበት የሚገባ ነው።
6. ማጠቃለያ
ኢትዮጵያ የፈረመቻቸውን የአለምአቀፍ የሴቶች መብት ስምምነትን በተመለከተ በህጎቿ አንድ አካል አድርጋ ከመተግባር አንጻር የህጉ ልልነት እንዲሁም በህጉ የወጣውን የሴቶች መብትን ለሴቶች በመቶርገም እውን ከማድረግ አንጻር ሰፊ ስራ የሚጠበቅ በመሆኑ ህግ አውጪው፣ህግ አስፈጻሚው እንዲሁም ተርጓሚው ትኩረት ሰጥት ሊሰራ የሚያስፈልገው ነው።

1 year ago
ቢል ጌትስ ሮቦቶች ላይ ግብር እንዲጣል ሀሳብ አቀረቡ
#ethiopia | የማይክሮሶፍት ተባባሪ መስራች የሆኑት ቢል ጌትስ፣ ሮቦቶች የሰዎችን ሥራ ሲረከቡ የገቢ ምንጭ የሆኑ ሮቦቶች ላይ ግብር የመጣል ሀሳባቸው አሁን ባለው የቴክኖሎጂ ለውጥ ዘመን ዳግም ትኩረት አግኝቷል።
ይህን ያልተለመደ አስተያየት ለመጀመሪያ ጊዜ ያቀረቡት እ.ኤ.አ. በ2017 ዓ.ም ሲሆን፣ ሀሳቡም ሠራተኞች ላይ ከሚከፈለው የደመወዝ ታክስ ጋር በሚመሳሰል መልኩ፣ ሥራቸውን በሮቦት ለተኩ የንግድ ተቋማት የሮቦት ግብር እንዲጣል የሚያስችል ነው።
በወቅቱ እንደ ረቂቅ አስተያየት የታየው ሀሳብ፣ አሁን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በምርትና በአገልግሎት ዘርፎች የሰውን ጉልበት በከፍተኛ ፍጥነት እየተካ በመጣበት በዚህ ጊዜ፣ የረዥም ጊዜ አስተዋይነት የታየበት መፍትሔ ሆኖ ቀርቧል።
ምንም እንኳን ጌትስ የሮቦት ግብርን በቀጥታ ከዩኒቨርሳል መሰረታዊ ገቢ (Universal Basic Income – UBI) ጋር ባያያይዙትም፣ እነዚህ ሁለት ጽንሰ-ሐሳቦች የሥራ መጥፋት የሚያስከትለውን ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ለመቋቋም በሚደረጉ ዓለም አቀፍ ውይይቶች ላይ ተደጋግመው ይነሳሉ።
ጌትስ በ2017 ባደረጉት አንድ ቃለ ምልልስ ላይ ዩናይትድ ስቴትስ UBIን ለመቀበል ገና የሚበቃ ሀብት እንደሌላት ገልጸው ነበር። ሆኖም፣ በቅርቡ በ2024 በኔትፍሊክስ ባቀረቡት ተከታታይ ፊልም (What's Next? The Future With Bill Gates) ላይ ያካፈሉት አስተያየት ለውጥ አሳይቷል።
እንደ መናኸሪያ ኤፍ ኤም ዘገባ ከሆነ በድህነት ቅነሳ ላይ ያተኮሩ የUBI ዓይነት ፕሮግራሞች በመጨረሻ የረዥም ጊዜ ወጪ ቁጠባ እንደሚያስገኙ ይከራከራሉ።
ይህንንም ሲያብራሩ፣ በዩናይትድ ስቴትስ የአዋቂዎች ድህነት በዓመት ከ1 ትሪሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስወጣ የሚያመላክተውን መረጃ በመጥቀስ፣ የድህነት ቅነሳ ከጊዜ በኋላ ከሚደረገው ወጪ የበለጠ ጥቅም እንደሚያስገኝ አሳስበዋል።

Comments