1 day ago
A group called Thesis Writer CA ****** ists master's and doctoral students who are stuck between a rough thesis declaration and a completed document. Most arrive with a chapter that simply won't stay together, a disorganized first outline, or remarks from a supervisor they don't understand. The writers and editors are well-versed in graduate research and pay close attention to the requirements of each program. PhD thesis writing, dissertation ****** istance, thesis editing, and thorough proofreading prior to submission are among the services offered. The end product still sounds like the students since they are actively participating from the beginning. It provides them with consistent, sincere ****** istance.
https://www.thesiswriter.c...
https://www.thesiswriter.c...
PhD Thesis Writing Service in Canada | Top Canadian PhD Experts
Our PhD thesis writing service includes everything like topic selection, and research proposal till final chapter. Take support from PhD-certified Tutors.
https://www.thesiswriter.ca/phd-writing-service
24 days ago
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (GERD) እና የአባይ ወንዝ አጠቃቀም፡ ህጋዊ እና ታሪካዊ ትንተና
አጭር ጥናታዊ የህግ ጹሁፍ
አዘጋጅ፦ ፋንታሁን ደለለው
1. መነሻ (Introduction)
የአባይ (ናይል) ወንዝ ለዘመናት በበላይኛው እና በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት መካከል የታሪካዊ፣ ህጋዊ እና ፖለቲካዊ ውዝግቦች መነሻ ሆኖ ቆይቷል። ኢትዮጵያ ከ85% በላይ የሚሆነውን የአባይ ውሃ የምታበረክት ቢሆንም፣ በታሪክ አጋጣሚዎች እና በቅኝ ግዛት ስምምነቶች ምክንያት ሀብቷን እንዳትጠቀም ተፅዕኖ ሲደረግባት ቆይቷል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (GERD) መገንባት መጀመር የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት የመጠቀም ሉዓላዊ መብት በተግባር ያረጋገጠ ትልቅ የታሪክ ምዕራፍ ነው። ይህ አጭር ጥናታዊ ጽሁፍ የኢትዮጵያን እና የግብፅን የህግ ክርክሮች፣ አለምአቀፍ ድንጋጌዎችን እና የኢፌድሪ ህገ-መንግስትን መሰረት በማድረግ የተዘጋጀ የህግ ትንተና ነው።
2. የግብፅ እና የሱዳን ስምምነቶች እና የህግ ክርክሮች
ግብፅ እና ሱዳን በአባይ ወንዝ ላይ ያላቸውን የውሃ ድርሻ እና የይገባኛል ጥያቄ የሚመሰርቱት በቅኝ ግዛት ዘመን እና ከዛ በኋላ በተደረጉ የሁለትዮሽ ስምምነቶች ላይ ነው።
ሀ) የ1929 ስምምነት፦ በእንግሊዝ (የምስራቅ አፍሪካ ቅኝ ግዛቶቿን ወክላ) እና በግብፅ መካከል የተደረገ ሲሆን፣ ግብፅ በወንዙ ላይ የቪቶ (የመከልከል) መብት እንዲኖራት እና በላይኛው ተፋሰስ ሀገራት የሚገነቡ ማናቸውም የልማት ስራዎች የግብፅን ፍላጎት እንዳይነኩ የሚደነግግ ነው።
ለ) የ1959 ስምምነት፦ በግብፅ እና በሱዳን መካከል ብቻ የተደረገ የሁለትዮሽ ውል ሲሆን፣ ጠቅላላ የወንዙን የውሃ ፍሰት ሙሉ በሙሉ በመከፋፈል 55.5 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ለግብፅ፣ 18.5 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ደግሞ ለሱዳን የሰጠ ስምምነት ነው። ኢትዮጵያ ከዚህ ውል ሙሉ በሙሉ ተገልላለች።
የህግ ተቀባይነት ድክመት (Res inter alios acta)፦ በአለምአቀፍ የውል ህግ መርህ መሰረት፣ በሁለት ወገኖች መካከል የተደረገ ስምምነት ሶስተኛ ወገንን ሊያስገድድ አይችልም። ኢትዮጵያ በእነዚህ ስምምነቶች ላይ ያልተፈራረመች በመሆኑ እና መብቷን በግልፅ የነፈጉ በመሆናቸው፣ እነዚህ ስምምነቶች በኢትዮጵያ ላይ ምንም አይነት ህጋዊ ተፈጻሚነት የላቸውም።
3. አለምአቀፍ የውሃ ስምምነቶች እና መርሆች
ዘመናዊው አለምአቀፍ የውሃ ህግ በቅኝ ግዛት ዘመን የነበሩ የይገባኛል ጥያቄዎችን ውድቅ በማድረግ ፍትሃዊ አጠቃቀምን ያበረታታል። እ.ኤ.አ የ1997 የተባበሩት መንግስታት የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ኮንቬንሽን (UN Watercourses Convention) ሁለት ዋና ዋና መርሆችን ያስቀምጣል፦
ሀ) ፍትሃዊ እና ሚዛናዊ አጠቃቀም (Equitable and Reasonable Utilization)፦ እያንዳንዱ ተፋሰስ ሀገር ሌሎችን ሳይጎዳ ከሀብቱ ተጠቃሚ የመሆን መብት አለው። ኢትዮጵያ የህዝቦቿን የኤሌክትሪክ ፍላጎት ለማሟላት ወንዙን የመጠቀም መብቷ በዚህ መርህ የተደገፈ ነው።
ለ) ጉልህ ጉዳት አለማድረስ (No Significant Harm)፦ የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ሀብታቸውን ሲጠቀሙ በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ የለባቸውም። የታላቁ ህዳሴ ግድብ የውሃ ፍሰትን የማይቀንስ (Non-consumptive) የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በመሆኑ በታችኞቹ ሀገራት ላይ ጉልህ ጉዳት አያደርስም።
4. የኢፌድሪ ህገ-መንግስት እና የኢትዮጵያ መብት
የኢፌድሪ ህገ-መንግስት የመንግስትን እና የህዝብን መብትና ግዴታዎች በግልፅ ያስቀምጣል፦
ሀ) አንቀፅ 40(3)፦ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት እና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግስት እና የህዝብ ብቻ መሆኑን ይደነግጋል። ይህም መንግስት የአባይን ወንዝ ለሀገር ልማት የማዋል ሙሉ ሉዓላዊ ስልጣን እንዳለው ያረጋግጣል።
ለ) አንቀፅ 89(1) እና 92(1)፦ መንግስት የሀገሪቱን የተፈጥሮ ሀብቶች በሙሉ በማቀናጀት ዜጎች ህይወታቸው እንዲሻሻል እና ከድህነት እንዲወጡ የማድረግ ህገ-መንግስታዊ ግዴታ አለበት። ታላቁ የህዳሴ ግድብ ይህንን ህገ-መንግስታዊ ግብ ለማሳካት የተገነባ ዋነኛ ብሄራዊ ፕሮጀክት ነው።
5. የናイル ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት (CFA)
የቅኝ ግዛት ስምምነቶችን ሙሉ በሙሉ በመሻር በናይል ተፋሰስ ሀገራት መካከል አዲስ የህግ ማዕቀፍ ለመፍጠር የተዘጋጀው የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት (CFA) በቅርቡ (እ.ኤ.አ 2024) አስፈላጊው የሀገራት ቁጥር ፈርመውት ስላፀደቁት በይፋ ስራ ላይ ውሏል። ይህ ስምምነት የኢትዮጵያን እና የሌሎችን የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ፍትሃዊ የመጠቀም መብት በህግ ያረጋገጠ ትልቅ ድል ነው።
6. ታሪካዊ እና አለምአቀፋዊ ሀገርአቀፍ ድጋፍ
ኢትዮጵያ በግድቡ ዙሪያ ጠንካራ የውስጥ እና የውጭ ድጋፎችን አግኝታለች፦
• የሀገር ውስጥ አንድነት፦ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በገንዘቡ፣ በእውቀቱና በጉልበቱ ግድቡን በባለቤትነት ደግፏል።
• የአፍሪካ ህብረት አቋም፦ 'ለአፍሪካ ችግሮች የአፍሪካዊ መፍትሄ' በሚለው መርህ መሰረት የአፍሪካ ህብረት የድርድር መድረኩን በመምራት የውጭ ጣልቃገብነትን ተከላክሏል።
• የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት አጋርነት፦ እንደ ኡጋንዳ፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ እና ሩዋንዳ ያሉ ሀገራት የኢትዮጵያን ፍትሃዊ የመጠቀም መብት ይደግፋሉ።
7. ማጠቃለያ (Conclusion)
በማጠቃለያው፣ የኢትዮጵያ የአባይን ወንዝ የመጠቀም መብት በተፈጥሮ ህግ፣ በአለምአቀፍ የውሃ ህግጋት (ፍትሃዊ አጠቃቀም) እና በሀገር ውስጥ ህገ-መንግስት የተደገፈ ፅኑ መብት ነው። የቅኝ ግዛት ዘመን የሁለትዮሽ ስምምነቶች ኢትዮጵያን አይገድዱም። የህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ እና የCFA ስምምነት ስራ ላይ መዋል የኢትዮጵያን የታሪክ የበላይነት ወደ ህግ የበላይነት ቀይሮታል።
8. ማጣቀሻዎች (References)
1. United Nations Convention on the Law of the Non-Navigational Uses of International Watercourses (1997).
2. Agreement on the Nile River Basin Cooperative Framework (CFA), 2010 (Entered into force in 2024).
3. Declaration of Principles (DoP) on the GERD signed by Ethiopia, Egypt, and Sudan (2015).
4. The Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia (1995), Articles 40, 89, and 92.
አዘጋጅ ፋንታሁን ደለለው , Lawyer , 0929101037
በ word እና PDF በቴሌግራም በአማረኛ እና እንግሊዘኛ ያገኙታል። https://t.me/Fantahunlawye...
email :- delelewfantahun20102010.com
https://www.facebook.com/s...
#ethiopia
#governmentpolicy
#ethiopianculture

25 days ago
ከ1.2 ትሪሊዮን ዶላር የንግድ ልውውጥ እስከ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ክፍት ቀጣና፤ የብሪክስ መሪዎች አዳዲስ የትብብር ሥልቶችን ነደፉ
*************************
የአባል ሀገራቱን በማስፋት በሕንድ ኒው ዴልሂ የተካሄደው 18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ በቴክኖሎጂ፣ በፀጥታ እና በኢኮኖሚ ዘርፎች የጋራ ትብብርን ለማጠናከር የሚያስችሉ አዳዲስ ሥልቶች ተነድፈዋል።
የብሪክስ አባል ሀገራት መሪዎቹ የጥምረቱ መፍትሔዎች ለመላው የደቡቡ ክፍለ ዓለም ሀገራት ተደራሽ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ጠንካራ የአፍሪካ ውክልና እንዲኖር፣ የፋይናንስ እና የገበያ ተደራሽነት ይበልጥ እንዲሰፋ፣ እንዲሁም ንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ትሥሥርን ለማሳደግ ተግባራዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጠይቀዋል።
የ‘ኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ’ አድማሱን በመላው አፍሪካ እንዲያስፋፋ በማለም የባንኩን ቢሮ በአዲስ አበባ ለማስተናገድ ኢትዮጵያ በሙሉ አቅም ዝግጁ መሆኗንም አረጋግጠዋል።
በአዲስ አበባ የሚካሄደው 32ኛው የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) በብሪክስ ሙሉ ድጋፍ ለአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎች እና ለዘላቂ ልማት መፋጠን ሁሉንም ድምፆች የሚያሰባስብ ሁሉን አቀፍ መድረክ ሆኖ ማገልገል እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስገንዝበዋል።
የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የሀገራቸውን የሊቀመንበርነት ጊዜ በማጠቃለል ባደረጉት ንግግር፣ የብሪክስ ሀገራት የተላላፊ በሽታዎች ወረርሽኝን በጋራ ለመከላከል የሚያስችል የተቀናጀ ሥርዓት ለመፍጠር መስማማታቸውን አስታውቀዋል።
በተጨማሪም በድንገተኛ አደጋዎች ጊዜ የቅድመ-ማስጠንቀቂያ መረጃዎችን ለመለዋወጥ እና የሎጂስቲክስ አቅርቦት ሰንሰለትን ለማጠናከር የሚያስችሉ የትብብር ማዕቀፎች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
በፈጠራ ዘርፍ፣ የጀማሪ ቢዝነሶችን (Start-ups) እና ኢንኩቤተሮችን የሚያስተሣሥር የብሪክስ ኔትወርክ፣ የብሪክስ ስታርት-አፕ የፈጠራ ፈንድ፣ እንዲሁም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን እና የጂኦ-ስፓሻል ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሮች እውነተኛ ፍላጎት የሚያውለው የብሪክስ የዲጂታል ግብርና ኔትወርክ መጀመሩን አብራርተዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ክህሎትን ለማሳደግ እና ሴቶችን ለማብቃት ያለመው ‘ብሪክስ ኮኔክት’፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን የሚደግፍ ፖርታል እና በትራንስፖርት ጉዳዮች ላይ ልምድ ለመለዋወጥ "የብሪክስ የከተሞች የወደፊት ፎረም" መቋቋማቸውን አስታውቀዋል።
በዘላቂ ልማት ዘርፍም የስማርት ግሪድ የዲጂታል ልህቀት ማዕከል መቋቋሙን ጠቅሰዋል።
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በበኩላቸው፣ ዛሬ ላይ ብሪክስ ባለብዙ ወገንተኝነትን ከሚያጠናክሩ እና ፍትሐዊ የሆነ የባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓትን ከሚቀርጹ መሪ ኃይሎች አንዱ መሆኑን ገልጸዋል። በብሪክስ ሀገራት መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ 1.2 ትሪሊዮን ዶላር መድረሱን እና አባል ሀገራቱ ከዓለም የወጪ ንግድ ሩብ ያህሉን እንደሚሸፍኑ ያነሱት ፑቲን፣ አሁንም ያልተሟጠጠ ሰፊ አቅም መኖሩን አስረድተዋል።
የጋራ የኢኮኖሚ ዕድገት ፕላትፎርም መፈጠር እንዳለበትም አሳስበው፣ አዲሱ የልማት ባንክ (NDB) እስካሁን 40 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጉ 123 ፕሮጀክቶችን ፋይናንስ ማድረጉን እና ተጨማሪ የረጅም ጊዜ ካፒታልን ለመሳብ ዲጂታል ንብረቶችን የሚጠቀም አዲስ የኢንቨስትመንት ፕላትፎርም መፍጠር እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ፣ በተግባራዊ ትብብር ላይ ያተኮሩ አምስት አዳዲስ ፕሮጀክቶችን አቅርበዋል። ከእነዚህም መካከል፣ በብሪክስ ሀገራት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂዎችን ለመለዋወጥ የሚያስችል የመጀመሪያውን ክፍት ዞን (open-access zone) መፍጠር፣ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች መካከል አጋርነት መመሥረት፣ ለዲጂታል ኢንዱስትሪዎች የጋራ የክላውድ (Cloud) ፕላትፎርም ማዘጋጀት እና ከፍተኛ ባለሙያዎችን ለማሠልጠን የብሪክስ የምሕንድስና ተሰጥዖ ልማት ጥምረት እንዲሁም የወጣት ሳይንስ እና ፈጠራ ልውውጥ ፕሮግራም ማቋቋም ይገኙበታል።
የኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን፣ ጽናት፣ ትብብር እና ዘላቂ ልማት የጥምረቱ የቀጣይ ሥራ መሠረት ሊሆኑ እንደሚገባ አሳስበው፣ ያለ ደኅንነት ኢኮኖሚያዊ ጽናት ሊኖር እንደማይችል ጠቁመዋል።
ኢራን በጂኦግራፊያዊ አቀማመጧ እና በኢነርጂ እንዲሁም በትራንስፖርት ዘርፍ ያላት አቅም ለብሪክስ ሀገራት አዳዲስ የትብብር መንገዶችን ለመፍጠር እንደሚያግዝ አረጋግጠዋል።
ብሪክስ በማደግ ላይ ላሉ ኢኮኖሚዎች የትብብር መድረክ ብቻ ሳይሆን ማንም ኃይል የሌሎች ሕዝቦችን ዕጣ ፈንታ የመወሰን መብት የሌለበት፣ ይበልጥ ሚዛናዊ እና አካታች ለሆነ ዓለም የሚደረግ ምኞት ተምሳሌት መሆኑ ተገልጿል።
ለሁለት ቀናት በሕንድ መዲና ኒው ዴልሂ የተካሄደው 18ኛው የብሪክስ ሀገራት መሪዎች ጉባኤ፣ 140 አንቀጾች ያሉት የኒው ዴልሂ የአቋም መግለጫን (New Delhi Declaration) በማጽደቅ ተጠናቅቋል።
በዮናስ በድሉ
#ethiopia #ebc #brics #brics2026 #globalsouth #newdelhideclaration

2 months ago
በወረቀት ላይ የቀረው የ78 አመቱ ድንጋጌ!
*የዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች የመጀመሪያው ረቂቅ ድንጋጌ ይህንን ይመስል ነበር።
#ethiopia | በፈረንጆቹ 1948 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በፈረንሳይ ፓሪስ ተሰብስቦ ይህንን ታሪካዊ ሰነድ አጸደቀ።
ሰነዱ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ያስከተለውን ዘግናኝ እልቂትና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተከትሎ የተዘጋጀ ነበር።
ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ያስከተለውን ዘግናኝ እልቂት ተከትሎ ከእንግዲህ በሰው ልጅ ላይ ግፍ አይፈጸምም በሚል መርህ የተረቀቀው ይህ ታሪካዊ ሰነድ ዛሬ 78 አመት ሞልቶታል።
በጦርነትና በመብት ጥሰት በታመሰችው ዓለማችን ውስጥ
በወረቀት ላይ የቀረ ሰነድ
ሆኗል በሚል ከባድ ትችት እየቀረበበትም ይገኛል።
ይህ ሰነድ የሰው ልጅ መሠረታዊ መብቶችና ነጻነቶች በመላው ዓለም ያለ ምንም ልዩነት እንዲከበሩና እንዲጠበቁ ጠንካራ መሠረት ጥሏል።
ድንጋጌው የሰው ልጅ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ሊኖሩት የሚገቡ መሠረታዊ የሲቪል፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ የማህበራዊ እና የባህል መብቶችን በዝርዝር ያካተተ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ ስምምነት ነው።
የሰነዱ መጸደቅ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ጭቁን ህዝቦች፣ ለነጻነት ታጋዮች እና ለሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች የትግል መነሻና የፍትህ መጠየቂያ መሳሪያ በመሆን ሰፊ ሚና ተጫውቷል።
ዘር፣ ቀለም፣ ጾታ፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት ወይም የፖለቲካ አቋም ሳይለይ እያንዳንዱ የሰው ልጅ በእኩልነትና በነጻነት የመኖር መብት እንዳለው አሳውቋል።
ይህ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ የሰው ልጅ በታሪኩ ካስመዘገባቸው ታላላቅ ሁነቶች አንዱ ተደርጎ ይወሰዳል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #universal #declaration #humanrights #democracy #france #paris #inherited

4 months ago
ST. PAUL, Minn. - The Governor of Minnesota has officially proclaimed Friday, July 3, as "Ethiopian Day" across the state, acknowledging the rich cultural heritage and significant contributions of the Ethiopian American community.
The official proclamation recognizes the achievements of Ethiopian residents in various sectors that strengthen the state, including business, education, healthcare, public service, and the arts. It highlights the community's enduring spirit and its vital role in enriching Minnesota's social and economic landscape.
The declaration coincides with the 43rd annual Ethiopian sports tournament, a major community gathering. Organizers and community leaders welcomed the governor's proclamation, expressing their gratitude for the state's recognition of their heritage and resilience.
The Ethiopian Day celebrations are scheduled to take place on Friday, July 3, at TCO Stadium in Eagan, Minnesota, where attendees will gather to honor their unity, shared future, and vibrant traditions.

6 months ago
ድንግልና(Virginity)
ድንግልና ባለማችን ላይ ይህ ነው የሚባልና ሁሉንም ሊያስማማ የሚችል ትርጓሜ የሌለው ቃል ሲሆን ይህም የሆነበት ምክንያት በጊዜ ለውጥ ፣ ከቦታ ቦታ፣ ከማህበረሰቡ ባህል እና ሀይማኖት አንፃር የተመሰረተ እይታ ስላለው ነው።
በደፈናው ሲተረጎም ግን ከዚህ በፊት ግንኙነት አድርጋ የማታውቅ እንስት “ድንግል” የሚለው ስያሜ ይሰጣታል።
ድንግልና በማህበረሰቡ የተሰጠው የባህል እና የሀይማኖት ትርጓሜ እንጂ ምንም አይነት በሳይንስ ወይም በህክምና ጥበብ ትርጓሜ ሊሰጠው የሚችል ወይም በምርመራ ታይቶ ሊረጋገጥ የሚችል ነገር አይደለም።
ድንግልና Vs ሀይመን (Hymen)
ሀይመን (Hymen) የሴት የመራቢያ አካል ወደ ሆነው ማህፀን መግቢያ /vagina/ ኮሪደር ላይ ያለ ስስ እና መለጠጥ የሚችል አካል ሲሆን
ከሰው ሰው የተለያየ አይነት ቅርፅ ሊኖረው ይችላል፤ አንዳንዶች ላይ በተፈጥሮ የሌለ ሲሆን አንዳንዶች ላይ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ የማህፀን መግቢያውን (Vagina) ደፍኖ ሊገኝ ይችላል።
ሀይመን (Hymen) በሰው ልጅ ላይ ብቻ የሚፈጠር አካል ሳይሆን በተለያዩ እንስሶች ላይም ይገኛል ለምሳሌ እንደ ፈረስ፣ ዝሆን፣ አሳ ነባሪ ፣ ቺምፓንዚ እና የመሳሰሉት
ሀይመን (Hymen) የሰው ልጅ ፅንስ 5 ወር ላይ እያለ የሚፈጠር አካል ሲሆን ፥ ከወሊድ በፊት ወይም ከወሊድ በውሀላ ቀዳዳው ይከፈታል። በጊዜ ሂደት የተለያየ የቀዳዳ መጠኖችንም ይይዛል።
ሀይመን (Hymen) ሊወጠርና ሊቀደድ የሚችል አካል ሲሆን፤ ይህም በተለያዩ ድርጊቶች ሊሆን ይችላል። እነኚህም :- የግብረ ስጋ ግንኙነት፣ የወር አበባ መፀዳጃ(Tampons) መጠቀም፣ የጣት የማህፀን ምርመራ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ( የፈረስ ግልቢያ፣ ሳይክል፣ ስፕሊት… ) ፣ በመራቢያ አካል አካባቢ የሚደርሱ አደጋዎች እና የመሳሰሉት ሊሆኑ ይችላሉ።
ድንግልና Vs የድንግልና ምርመራ(Virginity Test)??
በአለም ጤና ድርጅት (WHO, 2018) በወጣ መረጃ መሰረት ከዚህ በፊት በጤና ተቋማት ውስጥ ድንግልናን ያመለክታል ተብሎ የሚታሰበውን የሴት ልጅ አካል (Hymen) አለ ወይም የለም ፣ ተገርስሷል ወይስ አልተገረሰሰም የሚለውን ለማወቅ የሚደረገው ምርመራ(Virginity Test) ከአካሏ(Hymen) የአፈጣጠር ሁኔታ እና በእንቅስቃሴዎች ምክንያት በመራቢያ አካል ላይ በሚደርሱ ጫናዎች በሚፈጠር የቅርፅ ለውጥ ምክንያት አለ ወይም የለም ብሎ በእርግጠኝነት መናገር የማያስችል መሆኑ ተረጋግጧል
በተጨማሪም ወሲባዊ ጥቃት በደረሰባቸው ሴቶች ላይ ምርመራውን ማድረግ ከፍተኛ የሆነ የህመም ስሜት እንዲሁም የመጀመሪያውን የጥቃቱን ጊዜ አይነት ስሜት ቀስቃሽ ሁኔታ መፍጠር የሚያመጣ ሲሆን ሴቲቱ ለህይወቷ የሚያሰጋ ደረጃ ላይ ለምሳሌ እንደ ደም መፍሰስ እና የመሳሰሉት አደጋዎች መኖራቸው ለማረጋገጥ እና ህክምና ለመስጠት ካልሆነ በስተቀር በምርመራው ሀይመን(Hymen) በድርጊቱ ተገርስሷል( ድንግል አይደለችም) ወይም አለ( ድንግል ነች) ማለት በፍፁም አይቻልም ወይም አያስደፍርም።
እንደ WHO መረጃ የድንግልና ምርመራ የሴትን ልጅ የፆታዊ እኩልነት የጣሰ የምርመራ አይነት የሚል ሲሆን ይህም ሴቶች ላይ ብቻ ያነጣጠረ እና የወንዱን ድንግልና ከጥያቄ ውስጥ የማያስገባ ነው፤ ይህ ደሞ ኋላ ቀር ያረጀ ያፈጀ አስተሳሰብ ይለዋል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ የ1964ቱን World Medical Association’s Declaration of Helsinkiን በማጣቀስ ጤና ባለሙያዎች ይህንን የድንግልና ምርመራ(Virginity test) ማድረግ “መጀመሪያ ሰው ላይ ጉዳት አታድርስ - first, do no harm” የሚለውን ህግ ስለሚጥስ ለተጠያቂነት ይዳርጋል ይላል።
👉 አስተውል!!
በመጀመሪያ ግንኙነት ደም አላየህም ማለት ሚስትህ/ጓደኛህ ድንግል ነች አይደለችም የሚለውን አይነግርህም
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሴቶች (~63%)ቱ በመጀመሪያ ግንኙነት ምንም አይነት ደም አይኖራቸውም
seledadotio

10 months ago
ራስን በራስ ማስተዳደር እስከ መገንጠል
የሕገመንግስት አንቀጽ 39 እና ዓለም አቀፍ ህጎች
በህግ ባለሙያ ፋንታሁን ደለለው
መግቢያ #ethiopia | በአለምአቀፍ ደረጃ ራስን በራስ ማስተዳደር /self determination/ ጽነስ ሀሳቡ እስከ የት ድረስ እንደሆነ የተለያየ ትርጉም ሲሰጥበት ይስተዋላል። አንዳንዶች የመገንጠልን ጽንሰ ሀሳብን የሚያካትቱ ሲሆን አንዳንዳቹ ደግሞ የመገንጠልን ጽንሰሀሳብ በፍጹም በህገመንግስታቸው ውስጥ ሳያካትቱ እንደውም መገንጠል ላይ በዝምታም ሆነ በግልጽ የሚከለክሉ ሀገራት አሉ።
ራስን በራስ እስከ ማስተዳደር መገንጠል ስረአት በህገመንግስታቸው የሚያካትቱ ሀገራት ደግሞ በግልጽ እንዴት ሊሆን እንደሚችል በግልጽ አስቀምጠዋል። ከዚህ ውጭ ባለፈም በህጋዊ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ተገንጥለው ሀገር ነን የሚሉ እያስተዋልናቸው ያለ ሲሆን እነዚህ ሀገራት "እጣፋንታቸው ምንድነው?" የሚለውን በዚህ አጭር ጽሁፍ የምንመለከተው ይሆናል
1. ራስን በራስ ማስተዳደር ምንድነው?
(self determination)
ራስን በራስ ማስተዳደር አንድ ሀገር ወይም የአንድ ሀገር ክልል የሀገሩን የህገመንግስት እና የህግ የበላይነት በማክበር ያለማንም ጣልቃ ገብነት ራሳቸውን በራሳቸው እድል የሚያስተዳድረበት ነው። በዚህ ረገድ የተለያየ አይነት ዙርያ ጥምጥም አይነት ትርጉም ቢመላለስም ራስን በራስ ማስተዳደር ማለት ከማንም ከጣልቃገብነት ነጻ በመሆን በህግ የበላይነትና በህዝቦች መፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አስተዳደር ነው።
2. ራስን በራስ ማስተዳደር እስከመገንጠል እንዴት ይፈጸማል? self determination to succesion
ራስን በራስ ማስዳደር እስከ መገንጠልን ተግባራዊ ለማድረግ የሚፈልግ ሀገር ከነበረበት ሀገር ጋር ለመቀጠል የሚያስችለው ዲሞክሪያሳዊ ፣ ህገመንግስታዊ መብትን ፣ አለምአቀፍ የዲሞክሪያሳዊ እና የሰብአዊ መብቶችን ለመጎናጻፍ ከእናት ሀገሩ ያጣ እንደሆና በህዝቡ ላይ ተደጋጋሚ የመብት ጭቆና እና የመብት ጥሰት እየደረሰበት ከሆነ ነው።
በዚህ ጊዜ ራስን በራስ የማስተዳደር እስከ መገንጠል መብት ጥያቄው ለሀገረ መንግስቱ ለሀገረ መንግስቱ መብት የተሰጠው ሲሆን ይህን በማቅረብ ህጉን ተከትሎ የሚወሰን ይሆናል።
ከዚያም በሀገሩ ህዝብና ህገመንግስት መሠረት በማድረግ አጠቃላይ ውሳኔ መገንጠል የሚፈልገው ህዝብ ጭምር ተጠይቆ የመጨረሻ መልሱ ያለ ልዩነት የመገንጠል መብትን የሚፈቅድ ከሆነ መገንጠል ተግባራዊ ይሆናል።
ይህ የሚሆነውም የመገንጠል መብት በህጉ በግልጽ የተቀመጠ እንደሆነ ነው። አለበለዚያ ግን መገንጠል አይታሰብም ተገነጠልኩ ቢልም የቅዥት ተግባር ይሆናል እንጂ ህጉን የጠበቀ ተግባር አይሆንም።
3. ራስን በራስ ማስተዳደር እስከ መገንጠል ተግባር እንዴት ይፈጸማል?
በመጀመሪያ ደረጃ የመጀመሪያዋ ሀገር የመገንጠል ጥያቄ የሚቀርብባት ህጋዊ ሀገር ልትሆን ያስፈልጋል። ይህም ማለት በአለም አቀፍ ልምድ ህጎች ውሳኔዎች መሠረት ሀገር ለማለት የምትበቃ ልትሆን ያስፈልጋል።
ሀገር ስትሆን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ህግ አውጪ፣ ህግ አስፈጻሚ ፣ህገመንግስት፣ህዝብ፣ግዛት፣የውጭ ግንኙነት አቅም ፣ ሉአላዊነት ሊኖራት ያስፈልጋል።
ይህቺ ሀገር በዚህ ልክ ህጋዊ ከሆነች በኋላ ነው የመገንጠል ጥያቄን የተወሰነው ሀገረ ግዛት ወይም ክልል ራስን በራስ ማስተዳደር ወይም እስከ መገንጠል የሚለውን በመጠየቅ በጠያቂው ህዝብ፣ ግዛትና እና በተጠያቂው ሀገር ህዝብ ሙሉ ፍቃድ ተፈጻሚ የሚሆነው።
ለምሳሌ ከኢትዮጵያ መገንጠል የሚፈልግ ክልል የሁሉም ክልሎች ፣ የፌደራል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤ፥ የፌድሬሽን ምክር ቤት እንዲሁም የጠያቂው ክልል ምክር ቤት በሙሉ ያለ ምንም ልዩነት የመገንጠል ይሁንታን ሊገኝ ያስፈልጋል።
አንዱ እንኳን የልዩነት ሀሳብ ካመጣ የመገንጠል ሀሳብ ተግባራዊ ሊሆን አይችልም። ይህ በኢፊድሪ ከመንግሥት አንቀጽ 39 ላይ የተቀመጠ ነው።
ለምሳሌ በኢትዮጵያ ይህ ህገመንግስት ሳይወጣ መንግስት ሳይመረጥ የመገንጠል ስረአት የሚከናወንበት ህግና ህገመንግስት ሳይኖር ሀገርንና ህዝብን ወክሎ የውጭ ግንኙነቶች ጋር የድርድርና የማስፈጸም አቅም ያለው የፖለቲካ ፓርቲ ወደ መንግስት የተቀየረ ሳይኖር ሀገርን በበላይነት የሚገዛ ህመንግስት ሳይመሰረት በተረባበሸ የሀገር ስሜት ውስጥ በመሆን ተገንጥያለው ብሎ በተወሰኑ ቡድኖች ብቻ በተደረገ የማይጸና ውል የመገንጠል ጥያቄ አቅራቢውም ሆነ ተቀባይውም ህጋዊ ቅቡልነት የሌላቸው ናቸው።
3. ቅቡልነት ያለው ህግን ሳይከተሉ መገንጠልን በራሳቸው ህጋዊ ያደረጉ ሀገራት እጣ ፈንታቸው ምን ይሆናል?
እነዚህ ሀገራት by defacfo(ያለ ህግ ቅቡልነት) ያላቸው ቢሆንም ከሌሎች ሀገሮች ጋር በሚያደርጉት ግንኙነቶች የሌላን ሀገርን ብሔራዊ ጥቅም መብት የሚነካ ከሆነ ጥቅሙ የሚነካበት ሀገር በተለይም ሀገር የሆነበት አካሄድ ህጋዊ ጥያቄን የሚያስነሳ ከሆነ ይህንን በመቃወሚያነት በማንሳት ብሔራዊ ጥቅሙ የተነካበት ሀገር መብቱን ማስከበር ይችላል።
4. መደምደሚያ
ይህ እንደ ጸሀፊው የህግ ምርምርና አስተያየት የቀረበ ቢሆንም ዋናው ነገር እንደ ጸሀፊው አስተያየት ሀገራት እንደ ህጋዊ ሀገር ሆነው ህዝባቸውን በማስተዳደር የዜጎችን እና የሀገርን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ በመጀመረያ ደረጃ በህግ ቅቡልነት ሊኖራቸው ያስፈልጋል።
References/ዋቢ መጽሀፍት/
1. Crawford, J. (2006). The Creation of States in International Law (2nd ed.). Oxford University Press.
2. International Court of Justice (ICJ). (2010). Accordance with International Law of the Unilateral Declaration of Independence in Respect of Kosovo, Advisory Opinion.
3. International Court of Justice (ICJ). (1986). Frontier Dispute (Burkina Faso/Republic of Mali), Judgment.
4. Montevideo Convention on the Rights and Duties of States. (1933).
5. United Nations Human Rights Council (UNHRC). (2022). Report of the Special Rapporteur on the situation of human rights in Eritrea. A/HRC/50/20.
6. United Nations Security Council (UNSC). (1999). Resolution 1244. S/RES/1244.
7. United Nations Security Council (UNSC). (1961). Resolution 169. S/RES/169.
8. Vaughan, S. (2011). The Ethio-Eritrean Conflict and the Algiers Agreement: A Legal Analysis. In A. Jacquin-Berdal & M. Plaut (Eds.), Unfinished Business: Ethiopia and Eritrea at War. Red Sea Press.
9. Woods, T. (2019). The Law of Territorial Integrity and the Eritrea-Ethiopia Boundary Commission. Cambridge Journal of International and Comparative Law.

የአለምአቀፍ የሴቶች መብት ስምምነት በሀገራችን የህግ ማእቀፍ እይታና አፈጻጸም አንጻር ያለው ክፍተት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ ወ/ሮ ቃልኪዳን አወቀ በማናቸውም ፌደራል ፍርድ ቤት ጠበቃና የህግ አማካሪ 0910683246
መግቢያ #ethiopia | ኢትዮጵያ የሴቶችን መብት ከማስከበር አንጻር የአለምአቀፍ ስምምነቶችን በማድረግ ቀዳሚ ተግባራት ፈጽማለች። በኢ.ፊ.ድ.ሪ ህገመንግስት አንቀጽ 13/2/ መሠረት የህጋችን አካል በማድረግ የራሷንም ህግ በማውጣት የሴቶችን መብት ለማስጠበቅ አስፈላጊውን ጥረት እያደረገች ነው። ይሁን እንጂ ህጉን በማስፈጸምም ሆነ መብቶቻቸውን ሙሉ ለሙሉ ከማስጠበቅ አንጻር ክፍተቶች የሚታዩ ሲሆን ይህን በዚህ አጭር ጽሁፍ የሚታይ ግንዛቤም ለማህበረሰቡ ለማሳደግ ቀርቧል።
. ፆታዊ ጥቃት ምንድን ነው?
ፆታዊ ጥቃት በሰዎች ላይ አካላዊ፣ ወሲባዊ ወይም ስነ ልቦናዊ ተብለው ሊከፈሉ ይችላሉ።
1.1 የሥነ-ልቦናዊ ጥቃት፡-
በቃላት ወይም ሞራል በሚነኩ አባባሎች ማሸማቀቅ እና ማስፈራት፣ በአካላዊ ጥቃት ወቅት በሚደርስባቸው የአካል ጉዳት ወይም ያልተፈለገ እርግዝና እና የጤና ጉድለት ምክንያት የሚከሰት የሥነ ልቦና አለመረጋጋት፣
1.2 ባህላዊ ጥቃት፡-
በባህል የሚፈፀም የውርስ ጋብቻ፣ ያለመውለድ ችግር ሴትን ብቻ ተጠያቂ አድርጎ በመውሰድ ከትዳር መፈናቀል፣ ልጆችን በማሳደግ ረገድ ሴቶች ከፍተኛውን ድርሻ መሸከም፣ በልጅነት ተገዶ መዳር፣
1.3ኢኮኖሚያዊ ጥቃት፡-
ሴቶችን በኢኮኖሚ ለመቆጣጠር የፋይናንስና የሃብት አማራጮችን መገደብ፣
1.4 ወሲባዊ ጥቃት፡-
ሃይልን በመጠቀም ያለፍላጓቷ የሚፈፀም ማንኛውም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ድርጊትና የግብረ ሥጋ ግንኙነት ድርጊትን የመሰሉ ለመልካም ፀባይ ተቃራኒ የሆኑ ድርጊቶችና ትንኮሳዎችን ፣ አስነዋሪ ለሆኑ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ድርጊቶች ማስገደድ
2. የፆታዊ ጥቃት የሚያስከትላቸው ችግሮች
2.1 የጤና የአካል ጉዳት፣ ሞት፣ ፌስቱላ፣ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ጨምሮ በተለያዩ በሽታዎች መያዝ፣ ላልተፈለገ እርግዝና፣ በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ ህመም እና በወሊድ ወቅት ለአደጋ መጋለጥ፡፡
2.1 የሥነ-ልቦናዊ ሀፍረት፣ ፀፀት፣ ድብርት፣ ፍርሃት፣ ራስን መጥላት፣ በራስ ያለመተማመን፣ አለመረጋጋት፣ ብቸኝነት፣ መገለልና መድሎ፣ የአእምሮ ህመም፣ ተስፋ መቁረጥና ሱሰኛነት፡፡
2.3 ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፆታዊ ጥቃት የተፈፀመባቸው ሴቶች ከትምህርት ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳታፊነት ራሳቸውን ማገለል፣ በኢኮኖሚ አምራችነት መቀነስና ኑሮቸውን በኢኮኖሚ ጥገኝነት መቀጠል፣ የቤተሰብ መበተንና መቃወስ፣ ለስደት፣ ለሌሎች በርካታ ሴቶችና ህፃናት ስጋት፣ አለመረጋጋት የበዛበት ማህበረሰብ እንዲፈጠር፡፡
2.4 በፍትህ ስርዓቱ ላይ ፆታዊ ጥቃት የተፈፀመባቸው ሴቶች ተገቢውን የሕግ ምላሽ እና ከለላ በማያገኙበት ጊዜ በሀገሪቱ ሕግና ሥርዓት ላይ ህብረተሰብ መፈጠር እና ፆታዊ ጥቃት የተፈፀመባቸው ሴቶች ለህግ አካላት ሪፖርት ከማድረግ መቆጠብ፡፡
2.5 የፆታዊ ጥቃት መንሰኤዎች ማህበረሰቡ በሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃት መቀበሉ፣ ኃላ ቀር የሆነ አስተሳሰቦች፣ ጎጂ ልማዳዊ ልምዶች፣ ማህበረሰቡ ስለ ሥርዓተ-ፆታ ያለው ግንዛቤ አነሳ መሆን፣ የሴቶችን መብቶች የሚያስከበሩ ህጎች አፈፃፀም አናሳ መሆን፣ የመጠጥ፣ የእጽና የተለያዩ ሱሶች ተጠቃሚነት፣ ልቅ የሆኑ የወሲብ ፊልሞች መስፋፋት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
2.6 ፆታዊ ጥቃት በማንና የት ይፈፀማል?
በቤተሰብ አባል፣ በጎረቤት፣ ጓደኛ፣ በትዳር አጋር፣ በሀይማኖት አባቶች፣ በመንግስት ባለስልጣናት እና ሌሎች በቅርብ በሚታወቁና በማይታወቁ ሰዎች፣
ጥቃቱ በማንኛዉም ቦታ የሚፈጸም ነዉ፡፡ በቤት ውስጥ፣ በትምህርት ቤት፣ በመንገድ፣ በሥራ ቦታ፣ ገበያ እና በሌሎች፡፡
2.7 ፆታዊ ጥቃትን ለማስቆም የተወሰዱ እርምጃዎች
አለም አቀፋዊ እርምጃዎች፡-
3. የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በሴቶች ላይ የሚፈፀም ጥቃትን 3. ለመከላከልና ለሴቶችና ህፃናት በቂ ጥበቃ ለመስጠት ሰነዶችን፣ መግለጫዎችን እና ስምምነቶችን አፅድቋል፡፡
3.1 ሁሉ ዓቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ/ Universal declaration on human right, 1948/
ይህ ሰነድ የሰዎች እኩል የሆነ ሰብዓዊ ክብርና መብትን እና ሁሉም ሰው ከአካላዊ ስቃይ ኢሰብአዊና ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ የመጠበቅ መብት እንዳለው አካቶ የያዘ አለምአቀፍ ስምምነት ነው፡፡
3.2 አለምአቀፍ የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች ስምምነት / International covenant on civil and political rights, 1966/
በዚህ ስምምነት ላይ በህይወት የመኖር መብትን፣ ከምንም አይነት አድልዎ የመጠበቅ መብትን፣ የአካል ደህንነትንና ነጻነት መብትን እውቅና የሰጠ ሰነድ ነው፡፡
3.4 አለምአቀፍ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ባህላዊ መብቶች ስምምነት/ International covenant on economic, social and cultural rights, 1966/
ይህ ስምምነት ከምንም አይነት አድልዎ የመጠበቅ መብትንና ሚዛናዊና አመቺ የስራ ቦታ የማግኘት መብትን ያካተተ ነው፡፡ ይህ በተዘዋዋሪ ሴቶች በስራ ቦታ ሊፈጸምባቸው ከሚችለው ወሲባዊ ትንኮሳ ጥበቃ ያደርጋል፡፡
3.5 በሴቶች ላይ የሚደረጉ ማናቸውም ዓይነት ልዩነት ወይም አድሎ ለማስወገድ የወጣ ስምምነት (CEDAW, 1979)
ይህም ስምምነት በፆታ ላይ የተመሰረተን አድሎኣዊ ልዩነት፣ ገደብ ወይም ማግለልን በመከልከል አባል መንግስታት በማናቸውም መልኩ የሚፈፀም ልዩነት ለማስወገድ የሚያስችል እርምጃዎችን እንዲወስዱ ያስገድዳል፡፡
3.6 የአፍሪካ ህብረት የመመስረቻ ሰነድ አንቀፅ 4/1 ላይ ማንኛውም የህብረቱ አባል ሀገራት
የሴቶችን እኩልነት የማህበር ግዴታ እንዳለባቸው በመርህ ደረጃ ያስቀምጣል፡፡
3.7 አፍሪካ የሰብዓዊና የህዝቦች መብቶች ቻርተርና የአፍሪካ ሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል/ Protocol to the African charter on human and people’s rights on the right of women, 2003/
ይህ ፕሮቶኮል በሴቶች ላይ የሚደረጉ አድሏዊ ልዩነቶችን ለማስወገድ የወጣው አለም አቀፍ ስምምነት ከያዛቸው ድንጋጌዎች ጋር ተመሳሳይ ድንጋጌዎችን የያዘ ሲሆን የአፍሪካን ሴቶች ነባራዊ ሁኔታ ማለትም በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የሚደርስባቸውን በደልና የስርዓተ-ጾታ ችግሮች ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
3.8 የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት
በአንቀጽ 35/4 በሴቶች ላይ አካላዊ አእምሮዊ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ጎጂ ልማዳዊ ድረጊቶች፣ ህጎችና ልምዶች አንዲወገዱ መንግስት ኃላፊነት እንዳለበት ይገልፃል፡፡
3.9 የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ወንጀል ህግ
የወንጀል ህጉ ፆታዊ ጥቃት የወንጀል ድርጊቶች መሆናቸውን በመደንገግ ሊያስቀጡ የሚችሉትን ቅጣት በማካተት ደንግጓል፡፡ ለመጥቀስ ያህል በግብረ-ሥጋ ነፃነትና ንፅህና ላይ የሚፈጸሙ ወጀሎችን (አንቀጽ 620-628)፣ ለተፈጥሮ በተቃራኒ ባህሪይ የሆኑ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ድረጊቶችን በተመለከተ (አንቀጽ 629-632)፣ የተለያዩ ጎጂ ልማዳዊ ድረጊቶችን (አንቀጽ 561-562) ፣ ጠለፋ (አንቀጽ 587-590)፣ ያለእድሜ ጋብቻ አንቀጽ (647-648)፣ አካል ላይ ጉዳት ማድረስ (አንቀጽ 555-560)፣ ግንኙነት ባላቸዉ ሰዎች መካከል የሚፈጸም ጥቃት (አንቀጽ 564)፣ በሴቶችና ህጻናት መነገድ (አንቀጽ 597-599፣ የዝሙት ተግባር (አንቀጽ 635-638) በህጉ ለሴቶች መብትና ደህንነት ጥበቃ የሰጡ
ድነጋጌዎችን ናቸው፡፡
3.10 የተሻሻለው የፌዴራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992
በጋብቻ፣ በልጅ አስተዳደግ፣ በሃብትና ንብረት አስተዳደር፣ በፍቺ ጉዳዩች ላይ ለሴቶች እኩልነት ትኩረት ተሰጥቷል፡፡
4. ከፍትህ ሚኒስትር እና ከፖሊስ ኮሚሽን ምን ይጠበቃል?
4.1 ወንጀልን መከላከል
ህብረተሰቡ “ፆታዊ ጥቃት መከላከል የእኔ ጉዳይ ነው፤ ይመለከታኛል” ይል ዘንድ በህዝብ አደረጃጀቶችን በመጠቀም እና በተለያዩ የመገናኛ ዜዴዎች የህብረተሰቡን ግንዛቤ በመቀየር ፆታዊ ጥቃት እንዳይፈፀም የመከላከል ስራ መስራት፡፡
እንዲሁም ወንጀልን ለመከላከል ከሚረዱ ዘዴዎች መካከል ወንጀል ፈፅመዉ ሲገኙ ቅጣት ከሚተላለፍባቸዉ ሰዎች ህብረተሰቡ ትምህርት በመዉሰድ ከወንጀሉ እንዲቆጠቡ በማድረግ ነዉ፡፡
የወንጀል ህግ ግቡም ወንጀል አድራጊዎቹ ተቀጥተዉ ሌላ ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡና ለሌሎች ማስተማርያ እንዲሆን ወይም እንዲታረሙ በማድረግ ወይም ተጨማሪ ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ እርምጃዎች እንዲወሰዱባቸዉ ለማድረግ ነዉ፡፡
ከዚህ አንፃር የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተቋም በአዋጅ የተሰጠዉን ስልጣን በመጠቀም በሴቶች የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ከፖሊስ ጋር በመሆን ምርመራ በማድረግ ክስ በመመመስረት እና የድርጊቱን ፈፃሚዎች ለፍርድ ቤት በማቅረብ ተመጣጣኝ የሆነ ቅጣት እንዲወሰን በማድረግ ህብረተሰቡ የፍርድ ቤቱን ቅጣት ውሳኔ እንዲያውቅ እና ራሱን ከድርጊቱ እንዲቆጥብ ማድረግ፡፡
4.2 ምላሽ ከመስጠት አንፃር
በአዲስ አበባ በአስሩም ክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኙ ምድብ ጽ/ቤቶች እና በድሬደዋ ምድብ ጽ/ቤት የተፈፀሙ ፆታዊ ጥቃት ወንጀሎችን ተገቢውን ምርመራን ከፖሊስ ጋር በመሆን ያካሄዳል ምርመራዉንም ከተጠናቀቀ በኃላ ፍርድ ቤት ክስ መስርቶ በማቅረብ እና ክርክር በማድረግ ወንጀል ፈፃሚው እንዲቀጣ የማድረግ ስራን ይሰራል፡፡
4.3 ከፍርድ ቤቶች ምን ይጠበቃል?
ፍርድ ቤቶች በእርግጥ ኃላፊነታቸው በህግ በፍሬ ነገርና በማስረጃ ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገ ቢሆንም ይህን ከማድረግ አንጻር አስፈላጊና ተገቢነት ያላቸውን የህገመንግስት፣ ስለሴቶች የተደረጉ አለምአቀፍ ስምምነቶች እንዲሁም የወንጀል ህጉንና አግባብነት ያለቸውን ህጎች መመሪያዎች መሠረት ባደረገ መልኩ ለሴቶች የተሰጠውን መብቶችን ከማስጠበቅ አንጻር አስፈላጊውን ማጣራት በማድርግ አስተማሪና ለሌላውም አስተማሪ የሆነ የቅጣት ውሳኔ ሊተላለፍ ያስፈልጋል።
5. የሴቶች ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች ለመከላከል የእኩልነት መብት ከማረጋገጥ አንጻር የአፈጻጸም ችግሮች
ሴቶች በህግ የተሰጣቸውን መብት ከማስጠበቅ አንጻር በተለይም በክልል በገጠር ውስጥ ከሚደርሱ ጥቃቶች አንጻር ህጎችን ተግባራዊ ለማድረግ ገና ሰፊ ስራዎች የሚጠበቅ ሲሆን ህጻናት ሴቶች እንኳን ከሚደርስባቸው ጥቃት ህይወታቸውን ቢያጡም እንኳን ይህን አድራጊው አካል ላይ በወንጀል የተቀመጠው ቅጣት የእድሜ ልክ ወይም እስከ 25 አመት ጽኑ እስራት ብቻ መሆኑ በሀገራችን ያሉ ህጎች ኢትዮጵያ በአለምአቀፍ ደረጃ የፈረመቻቸውን የሴቶችን መብቶቾ በህጎቿ አቅፋ የመተግበር ላይ ልልነት የሚታይ መሆኑን ማስተዋል የሚቻል ሲሆን ከዚህ ረገድ ህግ አውጪዎች ሊያስቡበት የሚገባ ነው።
6. ማጠቃለያ
ኢትዮጵያ የፈረመቻቸውን የአለምአቀፍ የሴቶች መብት ስምምነትን በተመለከተ በህጎቿ አንድ አካል አድርጋ ከመተግባር አንጻር የህጉ ልልነት እንዲሁም በህጉ የወጣውን የሴቶች መብትን ለሴቶች በመቶርገም እውን ከማድረግ አንጻር ሰፊ ስራ የሚጠበቅ በመሆኑ ህግ አውጪው፣ህግ አስፈጻሚው እንዲሁም ተርጓሚው ትኩረት ሰጥት ሊሰራ የሚያስፈልገው ነው።

Sponsored by
Surafel
11 months ago
አዋሽ ኢንሹራንስ አ.ማ. በተጠናቀቀው ሂሳብ ዓመት 1 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ አስመዘገበ።
#fastmereja I አዋሽ ኢንሹራንስ አ.ማ በተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት ለ31ኛ ጊዜ አመርቂ ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን፣ በዓመቱ ከታክስ በፊት ብር 1 ቢሊዮን በላይ አተረፈ። በበጀት ዓመቱ የተገኘው ያልተጣራ ትርፍ ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 27 በመቶ በላይ እድገት ያሳየ መሆኑ በኩባንያው የባለአክሲዮኖች 31ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተገልጿል። የአዋሽ ኢንሹራንስ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 31ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ተካሂዷል፡፡ ኩባንያው በተጠናቀቀው ሂሳብ ዓመት የተቀዳጀው ትርፍ በኢትዮጵያ የግል ኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ታሪክ ከዚህ ቀደም ያልተመዘገበና ለመጀመሪያ ጊዜ የሆነ፣ ከቢሊየን ብር የተሽገረ ትርፍ ሆኖ ተመዝግቧል።
በተጠናቀቀዉ በጀት አመት የኩባንያው የተከፈለ ካፒታል በ38 በመቶ አድጐ ብር 2.65 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ የተፈረመ ካፒታሉም ደግሞ 4 ቢሊዮን ሆኗል፡፡
ኩባንያዉ በዋነኛ የሥራ ዘርፎች እያስመዘገበ የዕድገት ምጣኔን በተመለከተ፣ በጀነራል ኢንሹራንስ (Non-Life) የ43 በመቶ፣ በሕይወት ዘርፍ ኢንሹራንስ ደግሞ የ48 በመቶ ዕድገት በማሳካት፣ እንደዚሁም በተካፉል የ124 በመቶ ዕድገት በማስመስግብ እጅግ አኩሪ ዉጤት አስመዝግቧል። ኩባንያዉ በአሥሩ ዓመት መሪ ዕቅድ እየተመራ ይሄን እጅግ ፈጣን የሆነ የዕድገት ምጣኔ በማሣካት ተካፉልን ጨምሮ በሁሉም የሥራ ዘርፎች በድምሩ ከ4.53 ቢሊዮን ብር በላይ አጠቃላይ ገቢ መሰብሰብ ችሏል፡፡ በጄነራል ኢንሹራንስ ከ3.73 ቢሊዮን ብር በላይ፣ በሕይወት ኢንሹራንስ ደግሞ ከ656.27 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሁም በተካፉል ከ156 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ ችሏል። የኩባንያዉ ፈጣን እድገት እና የላቀ ስራ አፈጻጸም ሁሉን አቀፍ ዉጤት ያመጣ ሲሆን በጀነራል ኢንሹራን ከ17ቱ የግል ኢንሹራንስ ኩባንያዎች የገበያ መሪነቱን በሰፊ ልዩነትና የገበያ ድርሻ ለ13ኛ ዓመት ያረጋገጠ ሲሆን፣ በሕይወትና ጤና መድን (Life Assurance) ዘርፍ ደግሞ ከአጠቃላይ የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ መሪነቱን ዳግም አረጋግጧል። በተጨማሪም በሸሪዓ መርህዎች በሚገዛው የተካፉል ዘርፍም ከሀገሪቱ አጠቃላይ ኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ በአጭር ጊዜ ዉስጥ በሰፊ ልዩነት በአንደኝነት ለመምራት ያስቻለዉን አስደናቂ ዉጤት አስመስግቧል።
ኩባንያው የገበያ አድማሱን ይበልጥ ለማስፋትና ለተገልጋዩ ሕብረተሰብ ተደራሽነቱን ለማረጋገጥ አቅዶ በተንቀሳቀሰዉ መሰረት አጠቃላይ የኩባንያዉ የቅርንጫፍና የአገናኝ ቢሮዎቻች ብዛት በዓመቱ መጨረሻ 71 የደረሰ ሲሆን፣ የሽያጭ ወኪሎችን ብዛት ከ300 በላይ በማድረስ ከ100 ሺ በላይ ለሚሆኑ ደንበኞች ቀልጣፋና አስተማማኝ የመድን አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። አዋሽ የደንበኞችን እና ሰፊዉን የሀገራችን ማህበረሰብ ያማከለ የመድን ሽፋን አገልግሎት በመስጠት ቀዳሚዉን ስፍራ የሚይዝ ኩባንያ ሲሆን አብዛኞቹ የሀገራችን ህዝቦች የተሰማሩበትን የግብርና ዘርፍ ከተፈጥሮ አደጋና ከአየር ንብረት መዛባት የሚታደገዉን የሰብል መድን አገልግሎት በዘንድሮው አመት መስጠት ጀምሯል።
በሌላ በኩል ቀደም ሲል ያበለጸጋቸውን ዘመናዊ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሲስተሞች በመታገዝ ለደንበኞቹ አስተማማኝ የመድን ሽፋን አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ እና ለደንበኞቹ ምቹና ቀላል ለማድረግ የሚይስቺል ዘመናዊ ዲጅታል ቻናል አበልጽጎ ወደ ስራ ለማስገባት ከመጨረሻ ምዕራፍ ደርሷል። በተጨማሪም ጊዜዉ የደረሰበትን የቴክኖሎጂ መፍትሄዎች ሁሉ በመጠቀም ወደ ደንበኞቹ ለመቀርብ ቆራጥ አቋም ያልው በመሆኑ ደንበኞች የተለያየ የክፍያ አማራጭ ያገኙ ዘንድ ከሀገራችን የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ አንዱ ከሆነው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ (ኤም ፔሳ) ጋር በመስራት ላይ ይገኛል።
የኢንቨስትመንት ምክረ ሃሳቦችን (Proposals) አዋጭነት በጥንቃቄ በመገምገምና በመፈተሽ በበጀት ዓመቱ በተለያዩ ስድስት ኩባንያዎች ላይ ኢንቨስት ያደረገ ሲሆን፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለመደግፍ የ107.6 ሚሊዮን ብር ቦንድ ግዢ፣ በተጨማሪም በልማት ባንክም በ120.3 ሚሊዮን ብር የቦንድ ግዢ በመፈጸም ለሀገራችን የልማትና እድገት ጥረት የፋይናንስ ምንጭ በመሆን የበኩሉን አስተዋጽዎ አበርክቷል።
በሌላ በኩል ለዋና መ/ቤቱ ባለ 4B+G+35 ወለል ያለው ሕንፃ ግንባታ የዲዛይን ማሻሻያ ሥራ (Design revision)፣ የሾሪንግ እና የመሰረት ቁፋሮ ሥራ ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ፣ የዋናዉ ህንጻ ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
በተጠናቀቀው የሂሳብ አመት ለተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢ ጥበቃ ላይ የራሱን ድርሻ ለመወጣት ለተለያዩ የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የገንዘብ፣ የቁሳቁስ እና ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ ተቋሟዊ ማህበራዊ ሀላፊነቱን ተጥቷል። ለአብነትም አሳሳቢ የሆነዉን የአየር ንብረት ለዉጥ ለመዋጋት የናይሮቢ ድክላሬሽን (Nairobi Declaration) በመፈረም ቀዳሚ በመሆን የተሰጡ ኢኒሼቲቮችን በመተግበር ላይ የሚገኝ ብቸኛው የሀገራችን ኢንሹራንስ ኩባንያ ለመሆን ችሏል። በተጨማሪም ለልዩ ልዩ የድጋፍና የልማት ዕርዳታ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት በበጀት ዓመቱ በድምሩ ከብር 30 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ በማድረግ ለወገንና ለአገራዊ ጥሪዎች ምላሽ መስጠት ችሏል፡፡
በመጨረሻም በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ለተቀዳጀው ውጤት አስተዋፅዖ ላደረጉ ሁሉ ኩባንያዉ ከፍ ያለ ምስጋና እያቀረበ፣ በኩባንያዉ ላይ ፍፁም ዕምነት በመጣል አዋሽ ኢንሹራንስን ምርጫቸው ላደረጉና አብረውን ለሰሩ ውድና እጅግ የተከበሩ ደንበኞቻችን ታላቅ ምስጋና ያቀርባል። በቀጣይም ኩባንያዉ አገልግሎቱን ይበልጥ በማዘመን የደንበኞችን ፍላጎት ማዕከል ባደረገ ጥናት በመታገዝ አዳዲስ የአገልግሎት አይነቶችን ለገበያው በማቅረብ ደንበኞቹን ለማገልገል በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል፡፡
አዋሽ ኢንሹራንስ አ.ማ. መስከረም 20 ቀን 1987 ዓ.ም. ከመንግስት የንግድ ፍቃድ አገኘ፣ ታህሳስ 23 ቀን 1987 ዓ.ም. በይፋ ስራዉን ጀመረ። በሀገራችን የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ታሪክ ለሌሎች ምሳሌ በሆነዉ ጠንካራ መሠረት ላይ የተገነባ የመጀመሪያዉ መሰረተ-ሰፊ የግል ኢንሹራንስ ኩባንያ ነዉ። በምስረታ ወቅት ባለአክሲዮኖቹ 456 የነበሩ ሲሆኑ አሁን ላይ የባለአክሲዮኖች ብዛት 2168 ደርሷል።
#ቢዝነስ

Comments