23 days ago
የኢትዮጵያ እና የተመድ የ80 ዓመታት ታሪካዊ ቁርኝት
****************
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የስምንት ዐሥርተ ዓመታት ጉዞ ውስጥ፣ ኢትዮጵያ በጋራ ደኅንነት፣ በሰላም እና በልማት ፅኑ አቋም ይዛ በዓለም አቀፍ መድረክ ደማቅ አሻራዋን አኑራለች።
ይህ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተሻገረው የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ጉዞ ተመድ የተመሠረተበትን በዓል ሲያከብር፣ የድርጅቱ ቀዳሚ መሥራች እና ንቁ ተሳታፊ የሆነችው ሀገራችን በዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ፣ በሰላም ማስከበር እና በልማት ትብብር ረገድ ያሳለፈቻቸው ዓመታት በክብር ይወሳሉ።
እ.አ.አ በ1945 ተመድ ሲመሠረት፣ ኢትዮጵያ ቻርተሩን ከፈረሙ 51 ቀዳሚ መሥራች ሀገራት መካከል አንዷ ነበረች።
ይህም በወቅቱ በቀኝ ግዛት ሥር ለነበሩት በርካታ የአፍሪካ እና የእስያ ሀገራት ትልቅ የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀ ታሪካዊ ክስተት ነበር።
ታዲያ ይህ ግንኙነት ለሌሎች ሀገራት ከተስፋነት በዘለለ፣ ላለፉት 80 ዓመታት ጠንካራ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ይዘት ኖሮት ቀጥሏል።
በተባበሩት መንግሥታት የታሪክ ድርሳን ውስጥ የኢትዮጵያ ስም ጎልቶ ከሚነሳባቸው ተግባራት ቀዳሚው የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ነው።
ከ1950ዎቹ የኮሪያ ጦርነት ጀምሮ በኮንጎ፣ በሩዋንዳ፣ በቡሩንዲ፣ በላይቤሪያ፣ በዳርፉር እንዲሁም በቅርብ ጊዜያት በአብዬ እና በደቡብ ሱዳን የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ኢትዮጵያ ለሌሎች ሀገራት ሰላም ዘብ በመቆም ግንባር ቀደም ሚናዋን ተወጥታለች።
ኢትዮጵያ ለተመድ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ በርካታ የሰላም አስከባሪ ወታደሮችን በመላክ ከግንባር ቀደምት ሀገራት ተርታ የምትሰለፍ ሆና ቀጥላለች፡፡ ይህም ለዓለም ሰላም እና መረጋጋት ያላትን ፅኑ አቋም በተግባር ያሳየችበት ነው።
አዲስ አበባ የድርጅቱ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (ECA) እና የሌሎች በርካታ የተመድ ኤጀንሲዎች መቀመጫ መሆኗ የኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት ግንኙነት ሌላው ትልቅ መገለጫ ነው።
እ.አ.አ በ1958 የተመሰረተው ይህ ኮሚሽን አዲስ አበባን ከኒውዮርክ እና ከጄኔቫ በመቀጠል የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ማዕከል እንድትሆን አድርጓታል።
ይህ ትብብር ኢትዮጵያ በአህጉራዊ የልማት አጀንዳዎች እና በኢኮኖሚ ትሥሥር ዙሪያ ያላትን ሚና በከፍተኛ ሁኔታ አሳድጎታል።
ተመድ 80ኛ ዓመቱን ሲያከብር ኢትዮጵያ የድርጅቱ ቻርተር እንዲከበር፣ የአፍሪካ ድምፅ በፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ሰጪነት ውስጥ ጉልህ ስፍራ እንዲኖረው እና በዘላቂ የልማት ግቦች ስኬት ዙሪያ ከተባበሩት መንግሥታት ጋር ያላትን አጋርነት እያጠናከረች ትገኛለች።
የኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የ80 ዓመታት ጉዞ፣ ለቀጣዩ ትውልድም በጠንካራ መሠረት ላይ ተገንብቶ ዘላቂ ተጽዕኖ እየፈጠረ እንደሚቀጥል ይታመናል።
በሀና ምንዳሁን
#ethiopia #ebc #un80 #unitednations #peacekeeping #globaldiplomacy #uneca

2 months ago
ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ማህበረሰቦች እና ሴት ስራ ፈጣሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርገው ታላቁ የማይክሮ ፋይናንስ ኮንፈረንስ ተጀመረ!
#fastmereja :የኢትዮጵያ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ማህበር (AEMFI) ከአውሮፓ ህብረት (Eሀ) እና ከዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ዓለም አቀፍ የነገው ትውልድ ማይክሮ ፋይናንስ ኮንፈረንስ በዛሬዉ እለት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
ከመጋቢት 15 እስከ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የስብሰባ ማዕከል በሚቆየው በዚህ ጉባኤ ላይ፤ የፖሊሲ አውጪዎች፣ የፋይናንስ ዘርፍ መሪዎች፣ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች እና የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
“ዕድሎችን በፈጠራ፣ በአካታችነት እና በማገገም አቅም ባላቸው የፋይናንስ አገልግሎቶች መክፈት'' በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ይህ ኮንፈረንስ፣ በዋናነት ዲጂታል ፈጠራዎች እና የፖሊሲ ማሻሻያዎች የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማስፋት ያላቸውን ሚና ይፈትሻል።
በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ማህበረሰቦች እና ሴት ስራ ፈጣሪዎች የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑና የኢኮኖሚ ጥንካሬ እንዲገነቡ በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ሰፊ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ለሶስት ቀናት በሚቆየዉ ጉባኤ ውስጥም የከፍተኛ የፋይናንስ ባለሙያዎች የፓናል ውይይቶች፣በፈጠራ የታጀቡ የፋይናንስ መፍትሄዎች ገለጻዎች፣እንዲሁም የፊንቴክ (Fintech) እና የማይክሮ ፋይናንስ ውጤቶች የሚቀርቡበት ኤግዚቢሽን እንደሚካሄድም ነዉ የተገለፀዉ።
ይህ ኮንፈረንስ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፉን ለማዘመንና አካታች ለማድረግ በምታደርገው ጥረት ውስጥ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው የተገለጸ ሲሆን፣ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትን ለማምጣት የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ያላቸውን ሚና ለማጎልበት ያለመ ነው፡፡
ይህ ኮንፈረንስ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፉን ለማዘመንና አካታች ለማድረግ በምታደርገው ጥረት ውስጥ እንደ ትልቅ ምዕራፍ የሚቆጠር መሆኑ ተገልጿል፡፡
በተለይም ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ዘመናዊ አሰራሮችን በመከተል የገጠሩን ማህበረሰብ እና አነስተኛ የንግድ ዘርፎችን ወደ ፋይናንስ ስርዓቱ በማስገባት ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ያላቸውን ድርሻ እንዲያሳድጉ ትልቅ መድረክ ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።
ኮንፈረንሱ እስከ መጋቢት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚቀጥል ሲሆን፣ በስተመጨረሻም በዘርፉ ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የጋራ የአቋም መግለጫ በማውጣት ይጠናቀቃል ተብሎ ይገመታል።

4 months ago
አዲስ አበባ አህጉራዊ ኃላፊነቷን በብቃት በመወጣት፣ ለአፍሪካውያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የጋራ መማማሪያ መድረክ መሆኗን ዳግም አረጋግጣለች።
ዛሬ በአህጉራችን መዲና አዲስ አበባ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ ከተሞች ከመጡ ከንቲባዎች እና ከክልል አስተዳዳሪዎች ጋር ፍሬያማ የአቻ ለአቻ የመማማሪያ መድረክ እያካሄድን እንገኛለን።
በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) አማካኝነት በአፍሪካ ከተሞች የፋይናንስ አስተዳደር (Financial Management) አፈፃፀም ላይ በተካሄደው ጥልቅ የዳሰሳ ጥናት መሠረት፤ አዲስ አበባ ከተመዘነችባቸው 6 መስፈርቶች ውስጥ በ5ቱ የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገቧ ልምድ እንድታካፍል ተመርጣለች።
ጥናቱ ከተካሄደባቸው ስድስት የአፍሪካ ከተሞች (ናይሮቢ፣ ዳሬሰላም፣ ሉሳካ፣ ኪጋሊ እና ያውንዴ) መካከል አዲስ አበባ የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ ቀዳሚ መሆን ችላለች። በተለይም የገቢ እና የፋይናንስ ሀብት አስተዳደርን በማዘመን ረገድ ከተማችን የጀመረችው ሪፎርም ውጤታማና ለአፍሪካ ከተሞች አርአያ መሆኑን የጥናቱ ግኝት አመላክቷል።
ይህ ስኬት፤ ከተማችን ከምትሰበስበው አጠቃላይ ገቢ ውስጥ 71 በመቶውን ለልማት ሥራዎች በመመደብ፣ የዜጎችን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ስናደርግ የቆየነው የሪፎርም ጉዞ ውጤማነት ማሳያ ነው።
ዛሬ ከተለያዩ ከተሞች ለልምድ ልውውጥ የመጡት ተሳታፊ ከንቲባዎች እነዚህን የሪፎርም ሥራዎች በአካል በመጎብኘት፣ አዲስ አበባ በፋይናንስ እና በገቢዎች ስራ አቅሟን እንዴት ገንብታ ወደ ተግባራዊ ለውጥ እንደቀየረችው ሰፊ ተሞክሮ የምታካፍል ይሆናል።
ይህ መድረክ የአፍሪካ ከተሞችን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በጋራ የምንቀርጽበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው።
በመጨረሻም፣ ለዚህ ጥናት መሳካትና ለከተማችን እውቅና ለሰጡት ለተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA)፣ እንዲሁም የውጤቱ ባለቤት ለሆኑት ለአዲስ አበባ ነዋሪዎችና ለሥራ ባልደረቦቼ ሁሉ የላቀ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
አዲስ አበባ የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ሆና ትቀጥላለች!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
Addis Ababa has once again reaffirmed its continental leadership by serving as a platform for mutual learning among our African brothers and sisters.
Today, in our continental capital, we are hosting a productive peer-to-peer learning forum with mayors and regional administrators from various African cities.
According to an in-depth survey conducted by the United Nations Economic Commission for Africa (UNECA) on the financial management performance of African cities, Addis Ababa was selected to share its experience after achieving outstanding results in five of the six key metrics evaluated.
Among the six African cities surveyed (Nairobi, Dar Es Salaam, Lusaka, Kigali, and Yaoundé), Addis Ababa emerged as the top performer. The findings specifically highlighted that the reforms our city initiated in modernizing revenue and financial resource management are both effective and serve as a blueprint for other African cities.
This success is a testament to the effectiveness of our reform journey, through which we have allocated 71% of the city’s total revenue to development projects to ensure the sustainable benefit of our citizens.
The visiting mayors and participants will personally tour these reform projects today. Addis Ababa will share its extensive experience in building financial and revenue capacity and translating that capacity into tangible, transformative change.
This forum represents a historic opportunity for us to collectively shape the future of African cities.
Finally, I would like to extend my deepest gratitude to the UNECA for conducting this study and recognizing our city, as well as to the residents of Addis Ababa and my colleagues, who are the true owners of this achievement.
Addis Ababa will continue to be a symbol of African prosperity!
May God bless Ethiopia and its people!