1 month ago
ኩባንያችን የሳይበር ደህንነት ኮንፈረንስ ላይ በስትራቴጂካዊ አጋርነት በመሳተፍ ላይ ይገኛል
ኩባንያችን የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UN-ECA) እና የኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነት ማኅበር (ECySA) በጋራ ባዘጋጁት “የሳይበር ደህንነት በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘመን” (ICCA 2026) አህጉራዊ ኮንፈረንስ ላይ በአጋርነት እየተሳተፈ ይገኛል።
ይህ ኮንፈረንስ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን ተጨባጭ አህጉራዊ ተሞክሮዎችን፣ ጥናቶችን፣ የሳይበር ጥቃት ክስተቶችንና የቴክኖሎጂ ልህቀቶችን በመጋራት አህጉራዊ ትብብርን ለማጠናከር እንዲሁም በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የታገዙ የሳይበር ቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለማስተዋወቅ ያለመ ነው።
በመርሐ ግብሩ የኩባንያችን ኢንፎርሜሽን ሴኩሪቲ ቺፍ ኦፊሰር ፀጋዬ አማኑኤል፤ ያለ ዲጂታል አስተማማኝነት (Digital Trust) የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ሙሉ አቅም ማሳካት አዳጋች መሆኑን እና የሳይበር ደህንነት ለዘላቂ ዕድገት ወሳኝ መሆኑን በዝርዝር አብራርተዋል።
በዚሁ አህጉራዊ ኮንፈረንስ ላይ ኩባንያችን ደህንነቱ የተረጋገጠ የዲጂታል ሥነ-ምህዳር ለመገንባት ቁልፍ ሚና ለመጫወት የሚያስችሉ፤ በተለይ ለዳታ ደህንነት ጥበቃ፣ ለኔትወርክ ኦፕሬሽን ደህንነት እና ለሳይበር ጥቃት መከላከያ የሚሆኑ የኢንተርፕራይዝ ሶሉሽኖችን ለእይታ አቅርቧል።
ኩባንያችን የብሔራዊ የዲጂታል መሠረተ ልማት ባለቤት እንደመሆኑ፤ በዘመናዊ የሳይበር ቴክኖሎጂዎች ልቆ በመገኘት፣ የዳታ ሉዓላዊነትን በማስጠበቅና የዲጂታል ኢኮኖሚውን አስተማማኝነት በማረጋገጥ ለአህጉራዊ የዲጂታል ጉዞው ስኬት የበኩሉን ማድረጉን የሚቀጥል ይሆናል።
#ethiotelecom #cybersecurity #icca2026 #telebirr #digitalafrica #cyberresilience #gsma #itu #ecysa #uneca

Comments