20 days ago
ኢትዮጵያ፦ የዓለም ሰላም ተሟጋች እና የፍትህ ፋና ወጊ
******************
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተመሠረተበትን 80ኛ ዓመት ስናስብ ኢትዮጵያ ለዓለም ሰላምና ለፍትህ የከፈለችውን መተኪያ የሌለው መስዋዕትነት ማስታወስ ግድ ይላል።
ኢትዮጵያ ዓለም በጋራ ጉዳዮች ላይ ተሰባስቦ እንዲመክር ካላት ጽኑ አቋም የተነሳ እ.አ.አ በ1923 የመንግሥታቱ ማኅበር አባል ብትሆንም፣ ማኅበሩ ግን ከፋሺስት የመርዝ ጋዝ ጥቃት ሊጠብቃት አልቻለም።
ሀገራችን እ.አ.አ በ1936 በመንግሥታቱ ማኅበር ፊት ቀርባ "ዛሬ በእኛ ላይ የደረሰው ነገ በእናንተ ላይ ይደርሳል" በማለት ያሰማችው ትንቢታዊ ማስጠንቀቂያ በዓለም የዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ የፍትህ ተሟጋችነታችን ቀዳሚ ማሳያ ነው።
ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሲያበቃም ኢትዮጵያ ከ51 የተመድ መሥራች ሀገራት አንዷ በመሆን የሀገራትን ሉዓላዊ እኩልነት የሚያረጋግጡ ድንጋጌዎች በቻርተሩ እንዲካተቱ ታሪካዊ ሚና ተጫውታለች።
ከቃላት ባለፈም በአፍሪካና በተለያዩ ሀገራት ለሚገኙ የነጻነት ታጋዮች መጠጊያና ደጋፊ በመሆን ለጥቁር ሕዝብ ኩራት ሆና ቆይታለች።
በሰላም ጥበቃ ረገድም ከኮሪያ ጦርነት ጀምሮ እስካሁን ከ100 ሺህ በላይ ወታደራዊና የፖሊስ አባላትን በማሰማራት የዓለምን ሰላም በመስዋዕትነት ስታስጠብቅ ኖራለች።
ዛሬም ኢትዮጵያ በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ አፍሪካ ቋሚ መቀመጫና ፍትሃዊ ውክልና ሊኖራት ይገባል የሚለውን ጥያቄ በግንባር ቀደምነት በማንሳት ላይ ትገኛለች።
ይህ የዘመናት የፍትህ ተሟጋችነቷ ጉዞ የሰው ልጆች ሁሉ ድምጽ በእኩልነት እንዲሰማ ካላት ጽኑ ራዕይ የሚመነጭ ነው።
በለሚ ታደሰ
ዝርዝር ትንታኔውን በአስተያየት መስጫው ካጋራነው ሊንክ ያገኙታል 🔗
#ethiopian #diplomacy #un80 #globaljustice #peacekeeping #unitedafrica