19 days ago
የመጨረሻ አማራጬ ስለሆነ አንድ ነገር ከመሆኔ በፊት ግልፅ አድርጌ ልንገራችሁ። ለእናቴ ስል ነው ይሄን ለመፃፍ ሶሻል ሚዲያ ላይ የወጣሁት። የማያልፍ የለም አውቃለሁ ግን አንዴ ብታነቡት ነው። ይህ የእኔ ያለፉት ጥቂት አመታት አጭር ታሪክ ነው ለታሪክ ይቀመጥልኝ!!
የዛሬ አራት አመት አከባቢ እማዬን፤ እናትዬን ካንሰር አገኘብኝ። ያኔ እኔ 12ተኛ ክፍል ነበርኩ። 2015 ከገባበት ጊዜ ጀምሮ አመቱን ሙሉ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ስትሰቃይ ነው የከረመችው። እኔም ከዛ በኋላ ፍፁም ሌላ ሰው ሆንኩ። በእኩለ ቀን አይኔን ሳልዘጋ ያቃዠኛል፤ መከራዋ ድንገት ድቅን ይልብኛል፤ ከሰዎች ጋር ቆሜ የሚታየኝ የሚሰማኝ ግን ሲቃ ነው ትምህርቱም አስጠላኝ ( btw I was really famous for my IQ and academic performance... እኔ ነበርኩ ማትሪክ ከፍተኛ ይሰራል ተብዬ ምጠበቀው) እናቴ ለኔ ትምህርት ራሷን ጥላ፤ እኔ በትምህርት ትልቅ ደረጃ ደርሼ ለማየት ሁሉ ነገሯን ሰውታ ቀርፃ ነው ያሳደገችኝ። የዘወትር የልጅነት ህልሜም አድጌ በሳይንሱ ዘርፍ ስኬታማ ሆኜ አሳይቻት የደስታና የተድላ ኑሮ ማኖር ነበር። 12ተኛ ክፍል ላይ ግን ሁሉም ነገር ተጠቅልሎ ገሃነም ገባብኝ። ስቃዩዋ እንደ ቁስል እየጠዘጠዘኝ እንኳን ላጠና ሌላ ነገር ማሰብ ራሱ አልቻልኩም (ድንገት ደንግጬ እነሳለሁ በለሊት... ስልክ እንዳልደውል ሰዓቱ በጣም ሄዷል)።
እንዲህ እንዲህ እየተባለ ማትሪክ ደርሶ ግቢ ገባን። ገና ከመግባቴ ከህንፃ ደረጃ ላይ ወድቄ ተሰባበርኩላችሁ። ሰው ፈተና ላይ እያለ እንደ እቃ በሽቦ ይጠግኑኛል😂 ካልተፈተንኩ ብዬ ቀወጥኩት ክሊኒኩ ውስጥ (እናቴ ከሰማች አውቃለሁ ምን እንደሚፈጠር) ግንኮ እግሬ በድን ሆኗል..ተሸክመው አስደግፈው አስተኙኝ። ሞላልቼ ተሸክመውኝ ይወጣሉ.. ሞላልቼ ተሸክመውኝ ይወጣሉ.. እያልን እያልን ፈተናው ልክ ሲያልቅ innovation ላይ እንድትሰሩ የተመረጣቹ ልጆች እዚሁ ቅሩ ሲባል አጋጣሚውን ተጠቅሜ እስክድን ግቢ ለመቆየት ወሰንኩ እሷ still ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ናት (I was in love with robotics btw)
ከሁለት ወር በኋላ እኔም ዳንኩ እሷም 'አሁን ደህና ስለሆነችና regular check up ህክምናዋን ከቤት እየመጣች በትክክል እስከተከታተለች ድረስ እስከ full life expectancy'ዋ መኖር ትችላለች "ድናለች"(it's not a fatal type of cancer if well-treated) ተብላ ቤት መጣች። በደስታ አበድን። "back to normal life somehow".. ከዛ ውጤትም መጣ (519)። I knew I had a bad year ግን still ተበሳጭቼ ነበር (የ highschool ego'ዬ ሙሉ በሙሉ አልጠፋም ነበር 😁)። ግቢ ገባሁ። ፍሬሽ year እግዚአብሔር ይመስገን በሰላም ጨረስኩ። 2nd year'ም ምንም አይልም ነበር። 3ተኛ አመት ላይ ግን ድጋሚ አመማት። traumaዬ እንዳለ መመለስ ጀመረ. እንቅልፍ እምቢ አለኝ... በዚያ ላይ the way the medical expenses hit us last time, ቃል የለኝም ታቁታላቹ የበሽታውን ባህሪይ (የደሟ ናሙና በየሁለት ወሩ ነው ውጪ ሚላከው).. እሱን እሱንም ሳስብ I knew we ain't gonna afford a single tablet this time!!!
በመጨረሻም አሁን ላይ እንደገና ደከማት። ደምም አንሷታል ብለው ደም ሰጥተው ቤት ላኳት። ከመጣች በኋላ ግን በጣም አመማት። ከአልጋ ላይ ራሱ ተነስታ መቆም አትችልም ከቀን ወደ ቀን ስቃይ ነው ምግብም ብዙ አይበላላትም ዶክተሩ ግን በቀጣይ ቀጠሮ ሰውነቷ ተመልሶ ማየት ፈልጋለሁ ብሏት ነበር። እንዲ ብሎ ከላካት በኋላ አሁን እንደዚ እንደደከማት አላየም። መድሃኒቱም አለቀ እስከ ቀጠሮው ቀን የምትውጠው። አሁኑኑ ዶክተር ካላያት እየተባለ ነው ግን we can't afford it right now! ቁጭ ብዬ ስቃዩዋን ማየት ከበደኝ 😭😭😭 የምሰራው video editing'ም በቂ ገንዘብ ሊያመጣልኝ አልቻለም። I can't lose her man I CAN'T!!!!! እማዬን አድኑልኝ!! ከማበዴ በፊት እናቴን አትርፉልኝ ዝም ብላቹ አትዩኝ PLEASE🙏🙏😭😭😭
በገንዘብ ካልቻላችሁ በፀሎታቹ አግዙኝ... It must mean something, right?? ለምታውቁት ሰው ሼር ብታረጉልኝ ባለውለታዎቼ ናችሁ!! እወዳችኋለሁ።
CBE: 1000558030759

4 months ago
Yederaw Support:
አምስቱ ድምፅ አልባ ገዳዮች
#ethiopia | ምንም አይነት የህመም ስሜት ወይም ምልክት ሳያሳዩ በውስጣችን ለዓመታት በመደበቅ ድንገተኛ እና አደገኛ የጤና እክል ስለሚያደርሱ አምስት አደገኛ በሽታዎች (ድምፅ አልባ ገዳዮች)ን እንሆ
1. የደም ግፊት (Hypertension)
ይህ የጤና እክል በህክምናው ዓለም ቀዳሚው ድምፅ አልባ ገዳይ በመባል ይታወቃል። የደም ግፊት ምንም አይነት ምልክት ሳያሳይ የደም ቧንቧዎችን እያጠበበ እና እየጎዳ ለአስርት ዓመታት በሰውነታችን ውስጥ ሊቆይ ይችላል። በሽታው ስር እየሰደደ ሲሄድም ለድንገተኛ የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ (ስትሮክ) እና ለልብ ድካም ይዳርጋል።
ይህንን ለመከላከል ጨው የበዛባቸውን ምግቦች ከአመጋገብ ውስጥ ማስወገድ፣ መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እንዲሁም ውጥረትና ጭንቀትን መቀነስ ይመከራል።
2. ከፍተኛ ኮሌስትሮል እና የደም ስር መጥበብ (Atherosclerosis) በደማችን ውስጥ ያለው ከመጠን ያለፈ ስብ (ኮሌስትሮል) የደም ስሮችን ቀስ በቀስ በመዝጋት የደም ቧንቧዎች ለዓመታት እንዲጠቡ ያደርጋል። እነዚህ የደም ቧንቧዎች ሙሉ በሙሉ ተዘግተው ድንገተኛ የልብ ድካም ወይም የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ አደጋ እስከሚያደርሱ ድረስ ምንም አይነት ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ።
ስብ የበዛባቸው እና የተቀነባበሩ ምግቦች፣ ከመጠን በላይ ውፍረት፣ ማጨስ፣ አልኮል ማብዛት እንዲሁም የዘር ውርስ ተጠቃሽ ናቸው።
3. ስር የሰደደ የኩላሊት በሽታ (Chronic Kidney Disease)
የዚህ በሽታ አስከፊነቱ ኩላሊት ከ90 በመቶ በላይ ሥራዋን እስክታቆም ድረስ ምንም ምልክት አለማሳየቱ ነው። አንድ ሰው በሽታው ገብቶበት ሰውነቱ ማበጥ ከጀመረ በኋላ ወደ ህክምና ተቋም ቢሄድ ለህክምና ጊዜው እንደረፈደ ሊቆጠር ይችላል።
አይነት 2 የስኳር በሽታ፣ የደም ግፊት፣ ውፍረት፣ ማጨስ፣ የኩላሊት ኢንፌክሽን ወይም ጠጠር፣ የሽንት ፊኛ መዘጋት፣ የህመም ማስታገሻዎችን አብዝቶ መውሰድ እና በቂ ውሃ አለመጠጣት ችግሩን ያፋጥኑታል።
4. አይነት 2 የስኳር በሽታ (Type 2 Diabetes)
ይህ በሽታ ጸጥ ብሎ በመቆየት አብዛኛውን ጊዜ ምልክቱ የሚታወቀው እይታችንን ስናጣ ወይም ከባድ የነርቭ ጉዳት ሲደርስብን ነው።
* እንዴት ይከሰታል? ከፍተኛ ስኳር እና የተቀነባበረ ካርቦሀይድሬት ያለው ምግብ አብዝቶ መጠቀም ጣፊያችን ኢንሱሊን ቶሎ ቶሎ እንድታመነጭ ያስገድዳታል፤ በዚህም ሴሎች ኢንሱሊኑን በመላመድ በሽታው ይከሰታል። በተጨማሪም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ ጡንቻዎቻችን ግሉኮስን እንዳያቃጥሉ በማድረግ ስኳር በደማችን ውስጥ ለረጅም ሰዓት ቆይቶ የደም ቧንቧዎችን እንዲጎዳ ያደርጋል።
5. የጉበት ስብ (Fatty Liver)
በመጨረሻም የምንመለከተው የጉበት ላይ ስብ ክምችትን ነው። ጉበት ህመም ተቀባይ ነርቮች (Pain Receptors) ስለሌሉት፣ ከመጠን በላይ ስብ በውስጡ ሲጠራቀም ምንም አይነት የህመም ስሜት አይሰማንም። ሆኖም ግን ጉበታችን በዝምታ ለረጅም ጊዜ እየተጎዳ ቆይቶ በመጨረሻም 'ሲርሆሲስ' (Cirrhosis) ለተባለ የጉበት ሥራ ማቆም ችግር ይዳርጋል።
ከመጠን በላይ ውፍረት፣ አልኮል አብዝቶ መጠጣት እንዲሁም የስኳር እና የከፍተኛ ኮሌስትሮል ህመሞች በበሽታው የመያዝ እድልን በእጅጉ ከፍ ያደርጋሉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #አራዳFM #ዜና_ጤና #ጤና #ድምፅ_አልባ_ገዳዮች #የደም_ግፊት #ስኳር_በሽታ #ኩላሊት #የጉበት_ስብ #ኮሌስትሮል #silentkillers #healthnewsethiopia
"ለሚጥል በሽታ መቆጣጠሪያ የሚያገለግለው ፌንቶይን ታብሌት የጥራት ችግር አለበት" - የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት|
#ethiopia | የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ሜዲካመን ባዮቴክ ሊሚትድ በተባለ ኩባንያ የተመሠረተ ለሚጥል በሽታ (Epilepsy) መቆጣጠሪያ የሚያገለግለውን የፌንቶይን 100 ሚሊ ግራም (Phenytoin 100 mg) ታብሌት መድኃኒት የጥራት ችግር ስላለበት ከጤና ተቋማት በአስቸኳይ እንዲሰበሰብ በደብዳቤ ማዘዙን ታውቋል።
የቅርንጫፍ መሥራያ ቤቱ ለሁሉም የጤና ተቋማት በጻፈው ደብዳቤ ላይ እንደገለጸው በአምራቹ የተመረቱት የዚህ መድኃኒት ባቾች በሙሉ የጥራት ደረጃውን ባለማሟላታቸው ተመላሽ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
ይኹን እንጅ መድኃኒቱን ያልመለሱ ተቋማት ያላቸውን ቀሪ መጠን በደብዳቤ ገልጸው እስከ መጋቢት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንዲመልሱ ጥብቅ ማሳሰቢያ ቢሰጥም አንዳንድ የጤና ተቋማት መድኃኒቱን አለመመለሳቸውን አገልግሎቱ አሳውቋል።
ይህንን ትዕዛዝ ተላልፈው መድኃኒቱን ተመላሽ የማያደርጉ ተቋማት ለሚከሰት የጤና መታወክ ሙሉ ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ አሳስቧል።
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በመረጃው በጠቀሰው ባች የተመረተው ምርት ከ19ኙም የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎቶች እንዲሰበሰቡ ነው ያዘዘው።
ዜጎች ለሚጥል በሽታ መድኃኒት ሲጠቀሙ በጤና ባለሙያ የታዘዘላቸው እና ጥራቱ የተረጋገጠ መኾኑን እንዲያረጋግጡ ይመክራል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #nbc #tablet #addis #warning #new

5 months ago
🚨 አስቸኳይ የጥቆማ ጥሪ 🚨
በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ በሚሊኒየም አዳራሽ አቅራቢያ የሚገኘው አዶርሰም ሕንፃ (Adorsom Building) 2ኛ ፎቅ ላይ የሚገኝ ቢሮ ተዘርፏል። እነዚህ በምስሉ ላይ የምታዩዋቸው የአድዋን ድል ቀን በድፍረት ንብረት ዘርፈው ተሰውረዋል።
⚠️ የተዘረፉ ንብረቶች፦
ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች
ታብሌቶች (Tablets)p
ፕሮፌሽናል የፎቶና የቪዲዮ ካሜራዎች
የተለያዩ የስልክ መሣሪያዎች
🔍 የሌቦቹ ሁኔታ፦
ሌቦቹ የቢሮውን የደህንነት ካሜራ (Footage) ለማጥፋትና መረጃ ለመሰወር ቢሞክሩም፣ በሌሎች የሕንፃው መቆጣጠሪያ ካሜራዎች ላይ ማንነታቸው በግልጽ ሊታወቅ ችሏል።
🙏 የዜግነት ግዴታዎን ይወጡ!
እነዚህን ግለሰቦች የምታውቁ፣ ያያችሁ ወይም በተመሳሳይ ሁኔታ ዝርፊያ የተፈጸመባችሁ ወገኖች ጥቆማ በማድረግ እንድትተባበሩ ጥሪ ቀርቧል።
✅ ለጥቆማው ተገቢው ወሮታ ይከፈላል!
ጥቆማ ለማድረስ፦
📍 ቦሌ አደይ አበባ ፖሊስ ጣቢያ በአካል በመቅረብ ወይም
📞 በስልክ ቁጥሮች፦ 0988188890 ወይም 0907247454 ይደውሉ።
የሌቦቹን ፎቶ በማየትና ይህን መረጃ ሼር (Share) በማድረግ ወንጀለኞቹ ለሕግ እንዲቀርቡ ይተባበሩ! ወንጀልን በጋራ እንከላከል!

Sponsored by
Surafel
Comments