2 months ago
የፓሪስ ኦሎምፒክ ኮከብ ጋቢ ቶማስ በአዲስ አበባ ሊትገኝ ነው!
#ethiopia | በአለም አትሌቲክስ አውድ ውስጥ ደማቅ ስም ያላት አሜሪካዊቷ የ200 ሜትር የኦሎምፒክ ሻምፒዮን ጋቢ ቶማስ፣ በኢትዮጵያ በሚካሄደው ታሪካዊ የግራንድ ፕሪክስ ውድድር ላይ እንደምትሳተፍ አረጋገጠች።
ታሪካዊ ውድድር በአዲስ አበባ
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የምታስተናግደው የአንድ ቀን ዓለም አቀፍ የውድድር መድረክ (World Athletics Continental Tour) ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ይህ ውድድር የአለም የጥቁር ህዝቦች ኩራት በሆነችው አዲስ አበባ መካሄዱ ልዩ ትርጉም የሚሰጠው ሲሆን፣ የጋቢ ቶማስ መገኘት ደግሞ ውድድሩን በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል።
የጋቢ ቶማስ ድንቅ ስኬቶች
ጋቢ ቶማስ በዓለም አቀፍ መድረኮች ያስመዘገበቻቸው ውጤቶች በአጭሩ፦
በ200 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት።
በዚሁ ኦሎምፒክ በ4x100 ሜትር እና በ4x400 ሜትር የሪሌ ውድድሮች ከአጋሮቿ ጋር ተጨማሪ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ለአሜሪካ አስገኝታለች።
በቡዳፔስት ዓለም ሻምፒዮና የብር እንዲሁም በቶኪዮ ኦሎምፒክ የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ ናት።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን (ኢአፌ) እንደገለጸው፣ የዚህች አንጋፋ አትሌት መምጣት ለኢትዮጵያ ስፖርት እድገትና ለቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ኢትዮfm #gabbythomas #addisababagrandprix #ethiopianathletics #paris2024champion #continentaltour #addisababa #ethiopia #athleticsnews

3 months ago
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ
ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው ኮንቲኔንታል ቱር እና የዓለም ሻምፒዮናን የማስተናገድ ዕቅድ
#ethiopia | የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ዛሬ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በማግኖሊያ ሆቴል ለሚዲያ አካላት በሰጡት መግለጫ፣ በአገራችን አትሌቲክስ ታሪክ አዲስ ስኬት የሚመዘገብባቸው ታላላቅ ሥራዎች በቀጣይ ሳምንታት እንደሚከናወኑ አስታውቀዋል።
ታሪካዊው ኮንቲኔንታል ቱር፦
በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው የኮንቲኔንታል ቱር ውድድር የአገራችንን የስፖርት ዲፕሎማሲ አቅም የሚያሳድግና ዓለም አቀፍ ውድድሮችን የማዘጋጀት ብቃታችንን ለዓለም የሚያሳይ ይሆናል። ውድድሩን ከነሐስ (Bronze) ወደ ወርቅ (Gold) ደረጃ ለማሳደግ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው።
የዓለም ሻምፒዮናን የማስተናገድ ጥረት፦
ኢትዮጵያ በ2029 እና በ2031 የሚካሄዱትን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎችን ለማስተናገድ በጨረታ ሂደት ውስጥ በንቃት እየተሳተፈች ትገኛለች።
የ2028 ዓለም አቀፍ ውድድር፦
የ2028 የዓለም አትሌቲክስ አልትሜት ሻምፒዮንሺፕን ለማዘጋጀት የሚያስችሉ የጨረታና የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተገልጿል።
መደበኛ ስብሰባዎች፦
55ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እና 29ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በቀጣይ ሳምንታት የሚከናወኑ ሌሎች ዋና ዋና ተግባራት ናቸው።
ይህ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ውጤት ብቻ ሳይሆን፣ ትላልቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን በማዘጋጀትም የዓለም ትኩረት እንድትሆን የሚያስችላት ትልቅ እርምጃ ነው።
#getu #ethiopia #athletics #continentaltour #sileshisihine #worldathletics #sportdiplomacy #addisababa #አትሌቲክስ #ስለሺስህን #ኮንቲኔንታልቱር #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments