21 days ago
🚨 የሸገር ከተማ የፍትሕ በሮች ተዘጉ! ካርታ የሌላቸው ተፈናቃዮች ለፍርድ ቤት ክስ እንዳያቀርቡ በሕገ-ወጥ ትዕዛዝ ተከለከሉ! #ethiopia #shegercity #justicesystem #humanrights #geopolitics
2 months ago
በሸገር ከተማ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የቴክኖሎጂ ፈጠራ ኤግዚቢሽን እና ውድድር ተካሄደ
#ethiopia | በሸገር ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤት እና በሲያትል አካዳሚ መካከል በተደረገው ስምምነት መሠረት ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ለአራት ወራት የተሰጠው የቴክኖሎጂ ስልጠና መጠናቀቁን ተክተሎ በኤቨረስት አካዳሚ የፈጠራ ስራዎች ኤግዚቢሽን እና ውድድር ተካሂዷል።
ተማሪዎቹ በስልጠናው ወቅት በኮዲንግ፣ በሮቦቲክስ፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በኮምፒዩቲንግ፣ በኤሌክትሮኒክስ ዲዛይን እና በፕሮግራሚንግ ዘርፎች የቀሰሙትን የላቀ እውቀት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ችሎታቸውን ለዕይታ አቅርበዋል።
ይህም ስራቸው ለሀገራችን የቴክኖሎጂ እድገት ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ እና ወደፊት በዘርፉ አዎንታዊ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችሉበትን አቅም ያሳየ እንደሆነ ተገልጿል።
በመድረኩ የሸገር ከተማ አስተዳደር፣ የኦሮሚያ ክልል አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ለተማሪዎቹ የፈጠራ ስራዎች ልዩ አድናቆት የተሰጠ ሲሆን በቀጣይም ተስፋ ሰጪ ለሆኑት እነዚህ ወጣቶች ያልተቋረጠ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ተረጋግጧል።
በተጨማሪም ስልጠናውን በማዘጋጀትና በመደገፍ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከተው የሲያትል አካዳሚ፣ የስልጠናውና የፕሮጀክቱ ሀሳብ አመንጪ እንዲሁም የትምህርት ቤቱ ባለቤትና ማናጀር ለሆኑት ለአቶ መንግስቱ ወዳጄ ልዩ ምስጋና እና እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በዚሁ ዝግጅት ላይ የከተማው አስተዳደር እና የትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች የአድናቆት መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን የዘርፉ ባለሙያዎችም ተገኝተው ልምዳቸውን አክፍለዋል።
የዲጂታል ቴክኖሎጂ ለሀገር እድገት ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ መሰል ድጋፎች ለኢትዮጵያ ወጣቶች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አፅንኦት ተሰጥቶበታል።
በመጨረሻም በውድድሩ የላቀ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራቸውን ላቀረቡ ተማሪዎች የሽልማት እና የእውቅና መስጠት ሥነ ሥርዓት የተከናወነ ሲሆን ታናናሽ ህፃናትም የወደፊት ራዕያቸውን እንዲቀርጹና ፍላጎት እንዲያዳብሩ የመድረኩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተደርጓል።
#shegercity #seattleacademy #coding #robotics #artificialintelligence #ethiopianews #technologyinethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ዳለቲ ማረሚያ ቤት በጨርቃ ጨርቅና ዲዛይኒንግ ያሰለጠናቸውን ታራሚዎች አስመረቀ
#ethiopia | በሸገር ሲቲ የሚገኘው የዳለቲ ማረሚያ ቤት ከባውዘር ትሬዲንግ ጋር በመተባበር ለወራት በጨርቃ ጨርቅና ዲዛይኒንግ ሙያ ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን የህግ ታራሚዎች በልዩ ስነ-ስርዓት አስመርቋል።
ሙሉ ወጪው በባውዘር ትሬዲንግ የተሸፈነው ይህ ስልጠና በኦሮሚያ ክልል ደረጃ ለ3ኛ ጊዜ፣ በሸገር ሲቲ ደግሞ ለ2ኛ ጊዜ የተካሄደ ሲሆን፣ ተመራቂዎቹ በሙሉ የሲኦሲ ምዘና ፈተናን በስኬት ማለፋቸው ለትምህርቱ የሰጡትን ከፍተኛ ትኩረት አሳይቷል።
በዕለቱ የታራሚዎች የፈጠራ ስራ የሆኑ አልባሳትና የፋሽን ትርኢት ለታዳሚዎች ቀርቦ የተደነቀ ሲሆን፣ የታራሚ ቤተሰቦች፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም በምረቃው ላይ ተገኝተዋል።
በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ሻፊ ሁሴን፣ ተመራቂዎቹ የቀሰሙትን እውቀት ከማረሚያ ቤት ሲወጡ በኃላፊነት ስሜት ሊጠቀሙበት እንደሚገባ አሳስበዋል።
በሸገር ሲቲ የሚገኘው የዳለቲ ማረሚያ ቤት እያሳየ ያለው የስራ እንቅስቃሴ የሚያኮራ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ ብዙዎች ለማረሚያ ቤት ያላቸውን አመለካከት ባልቀየሩበት በዚህ ወቅት ባውዘር ትሬዲንግ ያደረገው በጎ ተግባር እጅግ የሚያስመሰግን መሆኑን ጠቁመዋል።
ይህ በሸገር ሲቲ እና በጅማ ለወንዶችና ሴት ታራሚዎች የተሰጠው ስልጠና ቀጣይነት ያለው ከመሆኑም በላይ፣ ሀገሪቱ የምትከተለውን "ኢትዮጵያ ታምርት" የተሰኘውን ፖሊሲ ለማስፈጸም ትልቅ አጋዥ አካል መሆኑንም አብራርተዋል።
የዳለቲ ማረሚያ ቤት ረዳት ኮሚሽነር ዋጋሪ ጫላ በበኩላቸው እድሉን ላመቻቹ አካላት ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ የባውዘር ትሬዲንግ መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሀመድ ሰኢድ ይህ ስልጠና ድርጅታቸው ከሚያከናውናቸው የማህበረሰብ አገልግሎቶች አንዱ መሆኑን አስረድተዋል።
ድርጅታቸው ለታራሚዎቹ 64 የሚደርሱ የዲዛይን ልብስ ስፌት ማሽኖችን ያበረከተ ሲሆን፣ በስራው ላይ በየደረጃው አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም የዋንጫ ሽልማት በመስጠት አበረታቷል።
#dalatiprison #shegercity #ethiopia #inmaterehabilitation #skilltraining #fashionanddesign #textiletraining #bowsertrading #ethiopiatamirt

7 months ago
መብራት ይጠፋል!
#ethiopia | ነገ በአዲስ አበባና በሸገር ከተማ የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች
ነገ ሰኞ መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ.ም. የጥገና ሥራ ለማከናወን ሲባል በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተማ በተወሰኑ አካባቢዎች የኃይል አቅርቦት ለተወሰኑ ሰዓታት የሚቋረጥ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።
የጊዜ ሰሌዳና አካባቢዎች፦
1. ከጠዋቱ 3:00 እስከ 10:00 ድረስ፦
የኮዬ ኮንዶሚኒየም (ከብሎክ 600 እስከ 636 በከፊል)፣ የፍሳሽ ማጣሪያ፣ ፋንታ፣ የፈጬ ማርያም መንደር፣ የቱሉ ዲምቱ ክፍያ ጣቢያ፣ የደራርቱ ትምህርት ቤት፣ የአየር ኃይል ካምፕ፣ የወርቁ ሰፈር፣ የመንገድ ትራንስፖርት፣ ገላን ጉራ፣ የባቡሩ ጀርባ፣ ሲዳሞ አዋሽ፣ ገላን መኖሪያ ቤቶች እና የገመዳ ማህበር።
2. ከጠዋቱ 2:00 እስከ 9:30 ድረስ፦
ብርጭቆ፣ የአስኮ 40 በ 60 ኮንዶሚኒየም፣ የጀሞ 2 ኮንዶሚኒየም፣ የስ ውሃ፣ የዓለምገና ማርስ ብስኩት፣ የዋልያ ብረታ ብረት፣ የጂፕሰም ፋብሪካ፣ ጣፎ፣ ኤም.ኤን.ኤስ (MNS) ሚሽን፣ 44 ማዞሪያ፣ ለገጣፎ፣ ሲዲሲ እና ኮሰሮ።
3. ከጠዋቱ 4:00 እስከ 9:00 ድረስ፦
የ700 ማህበራት፣ የቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚኒየም፣ የሸጎሌ አንበሳ ጋራዥ፣ የሸጎሌ መንደር 7፣ ፊናንስ፣ አበበ ቢቂላ፣ ኳስ ሜዳ፣ መሳለሚያ፣ ድዋ አደባባይ፣ የባልደራስ ኮንዶሚኒየም፣ አቧሬ፣ ቤለር እና የሳንፎርድ ትምህርት ቤት አካባቢዎች።
የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ ጥሪ ቀርቧል።
#getu #ethiopia #addisababa #shegercity #electricpower #maintenance #notice #utilitynews #የኤሌክትሪክአገልግሎት #የኃይልመቋረጥ #አዲስአበባ #ሸገር #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments