2 months ago
ዳለቲ ማረሚያ ቤት በጨርቃ ጨርቅና ዲዛይኒንግ ያሰለጠናቸውን ታራሚዎች አስመረቀ
#ethiopia | በሸገር ሲቲ የሚገኘው የዳለቲ ማረሚያ ቤት ከባውዘር ትሬዲንግ ጋር በመተባበር ለወራት በጨርቃ ጨርቅና ዲዛይኒንግ ሙያ ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን የህግ ታራሚዎች በልዩ ስነ-ስርዓት አስመርቋል።
ሙሉ ወጪው በባውዘር ትሬዲንግ የተሸፈነው ይህ ስልጠና በኦሮሚያ ክልል ደረጃ ለ3ኛ ጊዜ፣ በሸገር ሲቲ ደግሞ ለ2ኛ ጊዜ የተካሄደ ሲሆን፣ ተመራቂዎቹ በሙሉ የሲኦሲ ምዘና ፈተናን በስኬት ማለፋቸው ለትምህርቱ የሰጡትን ከፍተኛ ትኩረት አሳይቷል።
በዕለቱ የታራሚዎች የፈጠራ ስራ የሆኑ አልባሳትና የፋሽን ትርኢት ለታዳሚዎች ቀርቦ የተደነቀ ሲሆን፣ የታራሚ ቤተሰቦች፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም በምረቃው ላይ ተገኝተዋል።
በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ሻፊ ሁሴን፣ ተመራቂዎቹ የቀሰሙትን እውቀት ከማረሚያ ቤት ሲወጡ በኃላፊነት ስሜት ሊጠቀሙበት እንደሚገባ አሳስበዋል።
በሸገር ሲቲ የሚገኘው የዳለቲ ማረሚያ ቤት እያሳየ ያለው የስራ እንቅስቃሴ የሚያኮራ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ ብዙዎች ለማረሚያ ቤት ያላቸውን አመለካከት ባልቀየሩበት በዚህ ወቅት ባውዘር ትሬዲንግ ያደረገው በጎ ተግባር እጅግ የሚያስመሰግን መሆኑን ጠቁመዋል።
ይህ በሸገር ሲቲ እና በጅማ ለወንዶችና ሴት ታራሚዎች የተሰጠው ስልጠና ቀጣይነት ያለው ከመሆኑም በላይ፣ ሀገሪቱ የምትከተለውን "ኢትዮጵያ ታምርት" የተሰኘውን ፖሊሲ ለማስፈጸም ትልቅ አጋዥ አካል መሆኑንም አብራርተዋል።
የዳለቲ ማረሚያ ቤት ረዳት ኮሚሽነር ዋጋሪ ጫላ በበኩላቸው እድሉን ላመቻቹ አካላት ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ የባውዘር ትሬዲንግ መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሀመድ ሰኢድ ይህ ስልጠና ድርጅታቸው ከሚያከናውናቸው የማህበረሰብ አገልግሎቶች አንዱ መሆኑን አስረድተዋል።
ድርጅታቸው ለታራሚዎቹ 64 የሚደርሱ የዲዛይን ልብስ ስፌት ማሽኖችን ያበረከተ ሲሆን፣ በስራው ላይ በየደረጃው አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም የዋንጫ ሽልማት በመስጠት አበረታቷል።
#dalatiprison #shegercity #ethiopia #inmaterehabilitation #skilltraining #fashionanddesign #textiletraining #bowsertrading #ethiopiatamirt

Comments