22 hours ago
ኬንያ 109 የተደራጁ ወንጀለኛ ቡድኖችን ዝርዝር ይፋ አደረገች።
የኬንያ መንግሥት በሀገሪቱ 109 የተደራጁ የወንጀል ቡድኖችን ለይቶ ማውጣቱን አስታውቋል። ይህ ቁጥር በ2016 በGazette Notice No. 10427 ህገ-ወጥ ከተባሉ 89 ቡድኖች ጭማሪ ነው።
የተደራጁ የወጣት ቡድኖች ለፖለቲካ ማስፈራራት፣ ጥቃት እና ትንኮሳ ውስጥ መሳተፋቸው በስጋትነት ሲጠቀስ፥ ኬኒያ በ2027 ለምታካሂደው አጠቃላይ ምርጫ ከባድ የደህንነት ፈተና ሊሆን እንደሚችልም ተጠቁሟል።
«ጥቃት፣ ማስፈራራት እና የወንጀል ቡድኖችን ለፖለቲካ ጥቅም መጠቀም በዚህ ሂደት ውስጥ ቦታ የላቸውም» ብለዋል።
መንግሥት ባወጣው መረጃ መሰረት ምዕራብ ኬንያ 38 የሚሆኑ የተደራጁ ወንጀለኛ ቡድኖች የሚገኙባት ግዛት ስትሆን ሪፍት ቫሊ 22፤ እንዲሁም ናይሮቢ 20 የተመዘገቡባቸው ግዛቶች ሆነዋል።
በናይሮቢ የህዝብ ትራንስፖርት እና አነስተኛ ንግድ ላይ የሚደረግ ማስገደድ፣ በባህር ዳርቻ በቢላና በስለት የሚፈጸም ጥቃት፣ በሪፍት ቫሊና በድንበር ደግሞ የመሳሪያ ዝውውርና የከብት ዘረፋ የቆዩ መታወቂያዎች ሲሆኑ፣ እነዚህ ቡድኖች በፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ መጀመራቸው ስጋት ሆኖ ተቀምጧል።
መንግሥት ምርመራውን ከግለሰብ ወንጀለኞች ባሻገር የቡድን መሪዎችን፣ ቅጥረኞችን እና ፋይናንስ አቅራቢዎችን እየተከታተለ መሆኑን ሲገልጽ፣ የተወሰኑ እንቅስቃሴዎች ድንበር ተሻጋሪ በመሆናቸው ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚደረግ ትብብርም እየተጠናከረ ነው ሲል አስታውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም
@TikvahethMagazine

21 days ago
ከ46 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ የማታለል ወንጀል ፈጽሞ ከሀገር የተሰወረው ተጠርጣሪ በኢንተርፖል ትብብር በቁጥጥር ሥር ዋለ
ከ46 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸውን 12 የBYD Seagull ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በውክልና ለመሸጥ ከተረከበ በኋላ ገንዘቡን ለተበዳይ ሳያስረክብ ከባድ የማታለል ወንጀል ፈጽሞ ከሀገር የተሰወረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።
ተጠርጣሪው ከግል ተበዳይ አቶ ዮናስ ገብረመስቀል ጋር በነበረው የውክልና ስምምነት ተሽከርካሪዎቹን ከተረከበ በኋላ፣ የተገኘውን ገንዘብ ይዞ ከሀገር በመውጣት በታይላንድ፣ በሲንጋፖር፣ በፊሊፒንስ እና በኢንዶኔዥያ ሀገራት ሲዘዋወር ቆይቷል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከዓለም አቀፉ የፖሊስ ኅብረት ድርጅት (ኢንተርፖል) ጋር ባደረገው የቅርብ ትብብር በግለሰቡ ላይ ዓለም አቀፍ የቀይ ማስታወቂያ (Red Notice) እንዲወጣበት አድርጓል።
በዚህም መሠረት ተጠርጣሪው መስከረም 3 ቀን 2019 ዓ.ም በኢንዶኔዥያ ኢንተርፖል በቁጥጥር ሥር የዋለ ሲሆን፤ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተላልፎ መሰጠቱ ነው የተገለጸው።
ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ የምርመራ መዝገብ አደራጅቶ ያጠናቀቀ ሲሆን፤ ከዚህ በተጨማሪም በሌሎች ሁለት ከባድ የማታለል ወንጀሎች ተጠርጥሮ ተጨማሪ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ ገልጿል።
Seledadotio

22 days ago
ከ46.4 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን 12 የBYD Seagull ኤሌክትሪክ ተሽከርካረዎችን በመሸጥ ገንዘቡን ለተበዳይ ሳያስረክብ ከባድ የማታለል ወንጀል ፈጽሞ ከሀገር የተሰወረው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ
ከ46.4 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን 12 ቢዋይዲ Seagull የኤሌክትሪክ ተሽከርካረዎችን በውክልና ለመሸጥ ከግል ተበዳይ ዮናስ ገብረመስቀል ከተረከበ በኋላ ገንዘቡን ሳያስረክብ ከባድ የማታለል ወንጀል ፈጽሞ ከሀገር የተሰወረው ሰልማን መሀመድ የተባለው ግለሰብ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና በኢንተርፖል ትብብር በኢንዶኔዥያ ሀገር በቁጥጥር ሥር ውሏል።
ተጠርጣሪው ከኢትዮጵያ ወጥቶ በታይላንድ፣ በሲንጋፖር፣ በፊሊፒንስና በኢንዶኔዥያ ሀገራት ከሕግ ተጠያቂነት ለማምለጥ ሲዘዋወር ከቆየ በኋላ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖል ጋር በመተባበር በግለሰቡ ላይ ዓለም አቀፍ የቀይ ማስታወቂያ (Red Notice) እንዲወጣበት በማድረግ በኢንዶኔዥያ ኢንተርፖል መስከረም 3 ቀን 2019 ዓ.ም በኢንዶኔዥያ ሀገር በቁጥጥር ሥር ውሎ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተላልፎ ተሰጥቷል።
ሰልማን መሀመድ በተጠረጠሪው ወንጀል ፖሊስ የምርመራ መዝገብ አደራጅቶ ያጠናቀቀ ሲሆን ከዚህ ወንጀል በተጨማሪም በሌሎች ሁለት ከባድ የማታለል ወንጀሎች ተጠርጥሮ ተጨማሪ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑንም ገልጿል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተለያዩ የሽብር ወንጀሎችና በሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች የሚፈለጉ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ሕግ ፊት ለማቅረብ ከሀገራት የፖሊስ ተቋማትና ከኢንተርፖል ጋር በትብብር እየሠራ ሲሆን ይህንንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ለዚህ ኦፕሬሽን መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ለአዲስ አበባ ፖሊስ፣ ለኢንዶኔዥያ ፖሊስ እና ለዓለም አቀፉ የፖሊስ ኅብረት ድርጅት (ኢንተርፖል) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርቧል።

26 days ago
Addis Ababa Cooperatives Sell Meat at 1,200 ETB
#ethiopia I Consumer cooperative butcher shops across Addis Ababa are offering beef at a subsidized rate of 1,200 ETB per kilogram in celebration of the 2019 Ethiopian New Year, according to the Addis Ababa Cooperative Commission.
The initiative aims to ease the financial burden on city residents during the high-demand holiday season by offering an affordable alternative to soaring commercial market prices.
Service delivery began early in the morning at 5:00 AM local time across cooperative butcher shops situated in all sub-cities of the capital. Official data from the commission indicates that residents are actively purchasing from these points, citing noticeable price reductions compared to private local vendors.

6 months ago
መ/ቁ 00030
ፍትህ በጲላጦስ
ከሳሽ ፦አይሁድ ጠበቃ💥 ዲያብሎስ ጋር ቀርበዋል
ተከሳሽ ፦ኢየሱስ ክርስቶስ💠 ጠበቃ መንፈስ ቅዱስ ጋር ቀርበዋል
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዪ ፍርድ ተሰጥቷል
🔥 ፍርድ
#ethiopia | ለዚህ ክስ ምክንያት የሆነው ከሳሽ በጠበቃቸው አማካይነት በ30 አ.ም ተከሳሽ ለግርፋት ስቃይ እና መስቀል ሞት የሚያበቃ ወንጀል ፈጽሟል በመባሉ ምክንያት ሲሆን የወንጀሉ ዝርዝር 1/የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ማለቱ በሉቃስ ወንጌል ምእራፍ 22፥71 እንደተጻፈው
2/የአይሁድ ንጉስ ነኝ ማለቱ
3/ለቄሳር ግብር ህዝቡ እንዳይሰጥ ማድረጉ
4/ህዝብን በማሳመጽ በሉቃስ ወንጌል 23፥1-3 እንደተገለጸው የሙሴን ህግጋት በመተላለፉ ነው።
💥ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ የፍርድ ችሎት ከቀረበ በኋላ ከከሳሽ የቀረበለትን ክስ ተመልክቶ በመጀመሪያ ደረጃ ጉዳዩን ተቀብሎ ለማየት የግዛት ስልጣን አለኝ ወይንስ የለኝም የሚለውን መርምሯል🔥
ይህን በተመለከተ ሲያጣራ የተከበሩ ዳኛ ጲላጦስ ኢየሱስ ክርስቶስ ገሊላዊ መሆኑን በመረዳት ገሊላም በሄሮድስ ግዛት መሆኑን በመረዳት ይህን ጉዳይ ለማየት ስልጣን የለኝም በማለት ጉዳዩ በሄሮድስ ግዛት እንዲታይ ብይን ሰጥቶበታል ።
ወደ ሄሮድስ ግዛት እንዲታይ ታጅቦ የተላከው ክርሰቶስ ከሄሮድስ ፊት ቀረበ።ሄሮድስም የኢየሱስን ዜና ስለሚሰማ በፊቱ ስለቀረበ ደስ አለው።ሄሮድስም ኢየሱስን ሲጠይቀው ኢየሱስ ዝም ብሏል። ዝም ማለቱ እንዳላመነ አስቆጥሮለታል።ሄሮድስ የማየት ስልጣኑን በተመለከተ ምክንያቱን ባያስረዳም ጉዳዩን ወደ ጲላጦስ መልሶታል ።
💥ጲላጦስም ጉዳዩን ተቀብሎ ለማየት ስልጣን ያለው መሆኑን ተረድቶ ለኢየሱስ የእምነት ክህደት ቃል አቅርቦለት ኢየሱስ ከተከሰሰበት ሁለቱን ክሶች ያመነ ሲሆን እነዚህም የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ና የአይሁድ ንጉስ ነኝ ማለቱን ነው
በእነዚህ ሁለቱ ክሶች ላይ ብያለሁ ይበል እንጂ ጥፋተኛ ነኝ አላለም ከዚህ ጋር ተያይዞ የተከሰሰበት ህግ ምን ይላል የሚለውን ማየቱ ተገቢ ነው።ባልታመኑት ሁለቱ ክሶች ላይም ጲላጦስ መርምሯል።
💠ኢየሱስ ክርስቶስ ግብርን በተመለከተ በሉቃስ ወንጌል 20፥25 የቄሳርን ግብር ለቄሳር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር በማለት አይሁዳውያን ስለግብር ለጠየቁት ጥያቄ መልስ ሰጥቷል ይህ ለእርሱ ማስረጃ ሲሆን አይሁዳውያን ግን በዚህ ላይ ማስረጃ አላቀረቡም
💠ኢየሱስ ህዝብን አሳምጿል?ሁከት አስነስቷል?"የሚለውን ስንመለከት ኢየሱስን አምስት ገበያ ህዝብ በፍላጐት ተከትለውታል አብልቶ አጠጥቶዋቸዋል ፈውሷል የሞተ አስነስቷል አይነስውር አብርቷል ሽባ ተርትሯል ጎባጣ አንቅቷል በውሀ ላይ ተራምዷል እነርሱ ራሳቸው በመጻህፋቸው የሚጠባበቁትን መንግስተሰማያት ሰብኳል ለብዙ ዘመናት በበሽታ በደዌ የተያዙትን ከህመማቸው ነጻ አድርጓል ይህን ተግባር ራሳቸው የሚያውቁት ሲሆን በአራቱም የወንጌል መጽሀፍ ተቀምጧል።የወንጀል ባህሪም የለውም ።እነርሱ ግን ለዚህ ተጨባጭ ማስረጃ አላቀረቡም ።
💠ከሁከት ጋር ተያይዞ ለተነሳው አይሁዳውያን በሰለሞን ቤተመቅደስ ንግድ ሲገበያዩ ነጋዴዎችን ማባረሩ እንስሳቶችን ከየጎሪያቸው መልቀቁ የንግድ እቃዎችን መበተኑ በተመለከተ ሲመረመር ሁከት የሚያስብል አይደለም ።ምክንያቱም 1/ቤተመቅደሱን ያሰራው ጠቢቡ ሰለሞን ሲሆን አገልግሎቱም ህዝቡ ከአምላኩ እግዚአብሔር ጋር በጸሎት እንዲገናኝ እንዲያመሰግን ነው።ለንግድ አልተፈቀደላቸውም ።እዚህ ላይ የእግዚአብሔር ሰው የሆነ ወይም ለጸሎት የሚመጣ በንጉስ ሰሎሞን መብት አለው ።ገባይተኞች ህገወጥ በሆነ መንገድ የያዙት ነው።ኢየሱስ ለመጸለይ ለማመስገን በሰለሞን መብት ተሰጥቶታል ።
መብቱን ለመጠቀም ደግሞ ገባይተኛው መውጣት አለበት።ኢየሱስ ቤቴ የጸሎት ቤት ነው እያለ ነው ሲያስወጣቸው የነበረው ።ኢየሱስ የሰለሞን ዘር ስለመሆኑ የሚካድ አይደለም በሌላ አነጋገር የቅድመ አያቶቹ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ቀጥታ የመፋለም መብት ስላለው በህገወጥ መንገድ የያዙትን የማስወጣት መብት(inheritance and lawful ) አለው ። ከዚህ አንጻር ሁከት አልተፈጠረም።
💠ሌላው የህግ አከራካሪ ጉዳይ ያለበት የአይሁድ ንጉሥ ነኝ ፣የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ማለቱ ነው።ይህ ሲመረመር በክቡር ዳኛው ጲላጦስ ክርስቶስ🔥 አምላክ መሆኑን ተጨባጭ (tangible ) ማስረጃ አልተገኘም ።ግን ሙታን እያስነሳ ሌሎች ተአምራቶችን ማድረጉ ይታወቃል (judicial notice )።አምስት ገበያ ህዝብም በታምራቱ አስከትሏል ።ይህን ካደረገ ንጉስ የማይሆንበት ምክንያት ሊኖር አይችልም ተአምራቱም ምድራዊ አይመስልም ።ንጉስ ነኝ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ማለቱ የትኛውንም የሙሴ ህግ የተላለፈ ስለመሆኑ አላሳዩም ፣አልተላለፈም
💠የጲላጦስ ችሎት የግራ ቀኙን ማስረጃ ከህግ አግባብ ከመረመረ በኀላ በኢየሱስ ላይ 💦በደል አላገኘሁትም 😴 ሲል ውሳኔውን አሳውቋል ።
በዚህ ጊዜ ካህናቱ እና አይሁዳውያን እድምተኞች እጅግ በጣም ተቆጡ ጮኹ 💥ንጉሱም ፈራ🔥ስቀለው ስቀለው እያሉ እጅግ በጣም ጮኹ?ንጉሡ እጅግ በጣም ፈራ።ከዚህም የተነሳ በስቅላት እንዲሞት ፈቀደላቸው።
የቅጣት ውሳኔ እና አፈጻጸም
ኢየሱስ ክርስቶስ የፈጸመው ጥፋት ስለመኖሩ ማስረጃ ባይገኝበትም የህዝቡ ጬሀት እና ማስፈራራት ለጲላጦስ አገዛዝ ከፍተኛ ስጋት ከመሆኑ የተነሳ ክርስቶስ በከፍተኛ መከራ ስቃይ ውርደት ስቅላት ሞት እንዲቀጣ ሆኖ አፈጻጸሙም ከጎሎጎታ እስከ ቀራንዮ እንዲሆን ተወስኗል ➕
ትእዛዝ
1. በሲኦል ያሉ ነፍሳት ማረፊያቸው ገነት እንዲሆን ታዟል
2. ይግባኝ የለውም
3.በክርስቶስ ያመነ የሲኦሉ መዝገቡ ተዘግቷል ።
ጠበቃና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው 2012 ዓ.ም

7 months ago
መብራት ይጠፋል!
#ethiopia | ነገ በአዲስ አበባና በሸገር ከተማ የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች
ነገ ሰኞ መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ.ም. የጥገና ሥራ ለማከናወን ሲባል በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተማ በተወሰኑ አካባቢዎች የኃይል አቅርቦት ለተወሰኑ ሰዓታት የሚቋረጥ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።
የጊዜ ሰሌዳና አካባቢዎች፦
1. ከጠዋቱ 3:00 እስከ 10:00 ድረስ፦
የኮዬ ኮንዶሚኒየም (ከብሎክ 600 እስከ 636 በከፊል)፣ የፍሳሽ ማጣሪያ፣ ፋንታ፣ የፈጬ ማርያም መንደር፣ የቱሉ ዲምቱ ክፍያ ጣቢያ፣ የደራርቱ ትምህርት ቤት፣ የአየር ኃይል ካምፕ፣ የወርቁ ሰፈር፣ የመንገድ ትራንስፖርት፣ ገላን ጉራ፣ የባቡሩ ጀርባ፣ ሲዳሞ አዋሽ፣ ገላን መኖሪያ ቤቶች እና የገመዳ ማህበር።
2. ከጠዋቱ 2:00 እስከ 9:30 ድረስ፦
ብርጭቆ፣ የአስኮ 40 በ 60 ኮንዶሚኒየም፣ የጀሞ 2 ኮንዶሚኒየም፣ የስ ውሃ፣ የዓለምገና ማርስ ብስኩት፣ የዋልያ ብረታ ብረት፣ የጂፕሰም ፋብሪካ፣ ጣፎ፣ ኤም.ኤን.ኤስ (MNS) ሚሽን፣ 44 ማዞሪያ፣ ለገጣፎ፣ ሲዲሲ እና ኮሰሮ።
3. ከጠዋቱ 4:00 እስከ 9:00 ድረስ፦
የ700 ማህበራት፣ የቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚኒየም፣ የሸጎሌ አንበሳ ጋራዥ፣ የሸጎሌ መንደር 7፣ ፊናንስ፣ አበበ ቢቂላ፣ ኳስ ሜዳ፣ መሳለሚያ፣ ድዋ አደባባይ፣ የባልደራስ ኮንዶሚኒየም፣ አቧሬ፣ ቤለር እና የሳንፎርድ ትምህርት ቤት አካባቢዎች።
የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ ጥሪ ቀርቧል።
#getu #ethiopia #addisababa #shegercity #electricpower #maintenance #notice #utilitynews #የኤሌክትሪክአገልግሎት #የኃይልመቋረጥ #አዲስአበባ #ሸገር #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Sponsored by
Surafel
8 months ago
📣 አስቸኳይ ማስታወቂያ ለቀድሞ ሚሽከን ኮሌጅ ተማሪዎች በሙሉ!
ጉዳዩ፡- የተማሪዎች መረጃ ዝውውርን እና ማጣራትን ይመለከታል
በቀድሞ ስሙ ሚሽከን ኮሌጅ በዲግሪ እና በዲፕሎማ (TVET) ፕሮግራም ተምራችሁ ለተመረቃችሁ ወይም መረጃችሁን ለወሰዳችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡-
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ሚሽከን ኮሌጅ ያስተማራቸውን ተማሪዎች ወደ ሐጌ ኮሌጅ (Hage College) እንዲያስተላልፍ በወሰነው መሰረት፤ የተማሪዎች መረጃ ወደ ሐጌ ኮሌጅ መዞሩ ይታወቃል።
በመሆኑም የትምህርት ማስረጃችሁን ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስገብተን ለማስጸደቅ እና ለማስረከብ ስንዘጋጅ፤ ወደ ኮሌጁ ስትመዘገቡ ያስያዛችሁት የትምህርት ማስረጃ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
ስለሆነም ሁላችሁም የቀድሞ ሚሽከን ኮሌጅ ተማሪዎች፡-
1️⃣ ዋናውን የትምህርት ማስረጃችሁን በመያዝ፤
2️⃣ በሐጌ ኮሌጅ ዋናው ቢሮ በአካል በመቅረብ እንድታናግሩን እናሳስባለን።
📍 አድራሻ: የካ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 12 (ኮተቤ ካራ)፣ በሬ ተራ ፊት ለፊት፣ አያና ጋሮማ ህንጻ 2ኛ ፎቅ።
ለበለጠ መረጃ፡
📞 0975-73-77-41
📞 0934-43-34-38
መረጃው ለሁሉም ጓደኞቻችሁ እንዲደርስ ሼር በማድረግ ተባበሩን!
#hagecollege #mishkencollege #notice #students #education #addisababa #kotebe #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

9 months ago
አየር መንገዱ በረራ ሰረዘ 
#ethiopia |የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እና ኒዮርክ የሚያደርጋቸውን በረራዎች መሰረዙን አስታውቋል።
አየር መንገዱ በረራዎቹን የሰረዘው በአሜሪካ በተከሰተው ከባድ የሆነ የአየር ፀባይ ምክንያት ነው ብሏል።
አየር መንገዱ ባሁኑ ሰአት በረራ የሰረዘው ወደ ዋሽንግተን ዲሲ እና ኒዮርክ የነበሩ በረራዎች ናቸው።
አየር መንገዱ ዛሬ ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን እንደዚሁም በነገው እለት ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ አዲስ አበባ ሊያደርጋቸው የነበሩ በረራዎች ሰርዟል።
በተመሳሳይ በነገው እለት ከአዲስ አበባ ወደ ኒዮርክ ከኒዮርክ እንዲሁም ከኒዮርክ አዲስ አበባ ያሉትም በረራዎች መሰረዙን አስታውቋል።
ደንበኞች የተፈጠረውን ሁኔታ ተገንዝበው ቲኬታቸውን ድጋሚ እንዲያስመዘግቡ አየር መንገዱ አሳስቧል።
Flight Cancellation Notice Due to Adverse Weather
Ethiopian Airlines wishes to inform its valued customers that, due to adverse weather conditions in Washington D.C and New York, the following flights have been cancelled:
• ET 500 – 24 January: Addis Ababa (ADD) to Washington, D.C (IAD)
• ET 501 – 25 January: Washington, D.C (IAD) to Addis Ababa (ADD)
• ET 514 – 25 January: Addis Ababa (ADD) to New York (JFK)
• ET 515 – 25 January: New York (JFK) to Addis Ababa (ADD)
Affected passengers will be assisted with rebooking, rescheduling, or refunds, as applicable. We sincerely apologize for any inconvenience this may cause and appreciate your understanding as we continue to prioritize the safety of our passengers and crew.
We are closely monitoring the situation and will provide updates to our customers as more information becomes available.
Passengers are kindly advised to check the status of their flights prior to travel. For updates, please visit our website or mobile app, contact our Global Customer Interaction Center at +251 11 617 9900, or email Reservation @ethiopianairlines .com
Ethiopian Airlines
Star Alliance Member
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

🚨 ከቦሌ ብራስ ወደ ኤድናሞል የሚወስደው መንገድ ለጊዜው ተዘግቷል!
#ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ እያተከናወነ ባለው የመንገድ ጥገና እና ማሻሻያ ስራ ምክንያት፣ በቦሌ አካባቢ የሚገኙ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።
ምን ተፈጠረ?
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከቦሌ ብራስ ወደ ኤድናሞል በሚወስደው መስመር ላይ ተደራቢ አስፋልት የማንጠፍ ስራ እያከናወነ ይገኛል።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
* የመንገዱ ሁኔታ፦ ስራው ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት እስኪሆን ድረስ መንገዱ ሙሉ በሙሉ ዝግ ሆኖ ይቆያል።
* የባለስልጣኑ መልዕክት፦ አሽከርካሪዎች አላስፈላጊ የእንቅስቃሴ መስተጓጎል እንዳይገጥማቸው አስቀድመው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ አሳስቧል።
* ዓላማው፦ የመንገዱን ጥራት በማሻሻል ለትራፊክ ፍሰት አመቺ ለማድረግ የታለመ ነው።
ለጉዞዎ አስቀድመው እቅድ በማውጣት የትራፊክ መጨናነቅን ያስወግዱ!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #addisababa #trafficalert #roadwork #bole #roadsafety #addisroads #notice

Comments