6 months ago
ታዳጊዎችን የሚያሳትፈው "ሮቦቲክስ ለበጎ ዓላማ" ይፋ ተደረገ
📌 አሸናፊዎች ስዊዘርላንድ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ ውድድር ይሳተፋሉ!
#ethiopia | በዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ህብረት አዘጋጅነት የሚካሄደውና ዕድሜያቸው ከ10 እስከ 18 ዓመት የሆኑ ታዳጊዎችን የሚያሳትፈው "ሮቦቲክስ ለበጎ ዓላማ" የሮቦቲክስ ሻምፒዮና የ2026 የውድድር ይፋ ተደርጓል።
ይህ ታላቅ ሀገራዊ ንቅናቄ በኤግዚት ሲስተምስ እና ልዩ ዝግጅቶች አስተባባሪነት የሚመራ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና በሮቦቲክስ ዘርፍ ያላቸውን ክህሎት ተጠቅመው ዓለም አቀፍ ችግሮችን እንዲፈቱ ዕድል ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ገልጿል።
የዘንድሮው ውድድር ዋና ትኩረቱን በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ወሳኝ በሆነው "የምግብ ዋስትና እና ዘመናዊ ግብርና" ላይ ያደረገ ሲሆን ተማሪዎች ክፍት ምንጭ (Open-source) የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለግብርናው ዘርፍ መፍትሄ የሚሰጡ ሮቦቶችን ዲዛይን የማድረግ፣ የመገንባት እና ፕሮግራም የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።
ይህም ወጣቶች የንድፈ-ሀሳብ እውቀታቸውን ወደ ተግባራዊ ሀገር በቀል የፈጠራ ስራዎች እንዲቀይሩ ያስችላቸዋል።
በማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ባደረጉት ንግግር፣ ይህ ውድድር በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ውስጥ ያለውን ጉልህ ሚና ገልጸዋል። መንግስት ወጣቶች በቴክኖሎጂ ታግዘው ሀገራዊ ችግሮችን እንዲፈቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ያረጋገጡት ሚኒስትር ዴኤታው፣ እንዲህ ያሉ መድረኮች ለሀገር በቀል የፈጠራ ስራዎች መጎልበት ያላቸውን ፋይዳ አጽንኦት ሰጥተውበታል።
የኤግዚት ሲስተምስ ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሔለን አቢ በበኩላቸው፣ ይህ ፕሮግራም ኢትዮጵያን ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ወደ መፍትሔ ፈጣሪነት የምትሸጋገርበት ድልድይ መሆኑን ገልጸው፤ ውድድሩ በክልል ማጣሪያዎች፣ በሜንቶርሺፕ እና በቴክኒክ ስልጠናዎች ታጅቦ ዓመቱን ሙሉ የሚቀጥል የፈጠራ ጉዞ እንደሆነ አስረድተዋል።
ሀገራዊ የማጣሪያ ውድድሩ መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም በድምቀት ይካሄዳል።
በጁኒየር እና በሲኒየር ምድቦች አሸናፊ የሚሆኑ ሁለት ምርጥ ቡድኖች በስዊዘርላንድ ጄኔቫ በሚካሄደው "AI for Good Global Summit 2026" ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የመሳተፍ ዕድል ያገኛሉ።
ለአሸናፊዎቹ ሙሉ ወጪያቸው የተሸፈነ የጉዞ ትኬት፣ የመግቢያ ፓስ እና ምግብ የሚቀርብላቸው ሲሆን፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) እና ከዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ መሪዎች ጋር የመገናኘት ሰፊ ዕድል ይኖራቸዋል ተብላል።
#roboticsforgood #aiforgood #ethiopiatech2026 #youthinnovation #stemethiopia #foodsecurityai #exitsystems #itu #roboticschallenge #futureleaders #digitalethiopialove

Comments