3 hours ago
ታሪክ የሰራው የፓሪሱ የጸሎት መርሃግብር
#ethiopia | በፈረንሳይ ፓሪስ ስታድ ደ ፍራንስ በሚካሄደው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የፀሎት መርሃ ግብር ለመሳተፍ ከ80 ሺህ በላይ ወጣቶች በአንድ ሰዓት ውስጥ መመዝገባቸው ተገለፀ።
በቀጣዩ መስከረም 15 2019 ዓ.ም. ለሚካሄደው የጸሎት መርሃ ግብር ቦታ የመያዝ ሂደቱ በትላንትናው እለት ነሐሴ 4 ቀን የተጀመረ ሲሆን ከ17 እስከ 35 ዓመት የሆናቸው ወጣቶች የሚሳተፍ ይሆናል።
ከ100,000 በላይ ወጣቶች በጸሎትና በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ከጳጳሱ ጋር በሚኖራቸው ቆይታ የሚሳተፉ ይሆናል ተብሏል።
መርሃ ግብሩ ለአራት ቀን በሚቆየው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የፈረንሳይ ጉብኝት ውስጥ ከተካተቱት ዋና ዋና ኩነቶች አንዱ እንደሆነ ተገልጿል።
የፈረንሳዩ ስታድ ደ ፍራንስ ስታዲየም የመያዝ አቅም ከ80,000 በላይ ሰዎችን ቢሆንም የተዘጋጁት ቦታዎች በሙሉ በአንድ ሰዓት ውስጥ መጠናቀቃቸው እጅግ አስደናቂ ሆኗል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በፓሪስ በሚቆዩበት ጊዜ ከዚህ መርሃ ግብር በተጨማሪ በኖትር ዳም የጸሎት መርሃ ግብር የሚያደርጉ ሲሆን ታላቅ ህዝባዊ ቅዳሴም ይካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #france #visit #popeleo #youths #youthvigil #prayer #notredame #mass

Comments