2 months ago
የመደመር መንግሥት የወጣቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ ጉዞ
***********
ወጣቶች የሀገር የወደፊት ተስፋዎች ብቻ ሳይሆኑ፣ የዛሬዋ ኢትዮጵያ የለውጥ፣ የልማትና የዕድገት ዋና አሽከርካሪዎች ናቸው። የመደመር መንግሥት ወጣቶችን ከዳር ተመልካችነት ወደ ዋና ውሳኔ ሰጭነት፣ ከጠያቂነት ወደ መልስ ሰጭነትና ሥራ ፈጣሪነት ለማሸጋገር አቅጣጫ አስቀምጦ እየሠራ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የመደመር መንግሥት የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና የአመራርነት ሚና ለማጠናከር በትኩረትና በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን በአጽንዖት ገልጸዋል። ይህ መልዕክታቸው ደግሞ የሀገር ግንባታ ዋና መሠረት ወጣቱ ክፍል መሆኑን ያረጋገጠ ጥልቅ የፖሊሲ አቅጣጫ ነው።
ወጣቶች በሀገራቸው የምክክር፣ የዕድገትና የብልጽግና ጉዞ ውስጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ የመደመር መንግሥት ዋነኛ ግብ ነው። በዚሁ አግባብ የሥራ ዕድል ፈጠራን እና የኢንተርፕረነርሺፕ ባህልን በማሳደግ በቴክኖሎጂ፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች አዳዲስ ሥራዎችን በመፍጠር ሂደት ለወጣቶች ቅድሚያ ተሰጥቷል።
እንደ “5 ሚሊዮን ኮደሮች” ኢኒሼቲቭ ያሉ ዲጂታል ኢኮኖሚን እና የኢንዱስትሪ አብዮትን ያገናዘቡ ፕሮግራሞች ወጣቱን ለዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት እያዘጋጁት ይገኛሉ። እንዲሁም አዳዲስ የፈጠራ ሐሳብ ላላቸው ወጣቶች የመነሻ ካፒታል እና የብድር አቅርቦትን በማመቻቸት ወደ ሥራ እንዲገቡ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ ነው።
በመደመር እሳቤ ወጣት ኢትዮጵያውያንን በአመራርነት ማሳተፍ ለነገ የሚተው አጀንዳ አይደለም። ወጣቶች በከፍተኛ የመንግሥት፣ የፖሊሲና የቴክኒክ አመራር እርከኖች ላይ ተሰማርተው ውጤት እንዲያመጡ የመደመር መንግሥት ዕድል ሰጥቷል።
ወጣቶችን በአመራርነት ማሳተፍ የሀገርን የትራንስፎርሜሽን ጉዞ ያፋጥናል፤ አዳዲስ አሠራሮችን ጨምሮ አዎንታዊ አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ ያስችላል።
ወጣቶች በሀገራዊ ጉዳዮች ድምፃቸው እንዲሰማና በውሳኔ አሰጣጥ በቀጥታ እንዲሳተፉ መድረኮች ተመቻችተዋል። ዕድሜን ሳይሆን ብቃትን፣ ፈጠራንና ሀገራዊ ፍቅርን መሠረት ያደረገ የአመራር ምደባ ሥርዓት መዘርጋቱ ለወጣቶች ትልቅ በር ከፍቷል።
የመደመር መንግሥት የጀመራቸው እነዚህ ተግባራት ዘላቂ ውጤት እንዲያመጡ የሁሉንም ወገን የተቀናጀ ጥረት ይጠይቃል። ወጣቶችም የቀረቡላቸውን መልካም አጋጣሚዎች በመጠቀም ዕውቀትና ክህሎታቸውን ማሳደግ፣ ሀገራዊ አንድነትንና ሰላምን በማጽናት ረገድ ግንባር ቀደም ሚና መጫወት፣ በፈጠራና በሥራ ወዳድነት ለሀገር ብልጽግና አበርክቶ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት፣ ለወጣቶች የተሰጠ ትልቅ አደራና ዋስትና ነው። ወጣቶችን በሁለንተናዊ መልኩ ማብቃትና በአመራርነት ማሰማራት ለነገዋ ኢትዮጵያ ጠንካራ መሠረት የሚጥል የመደመር እሳቤ አንዱ መገለጫ ነው።
በአድማሱ አራጋው
#ethiopia #medemer #youths #entrepreneurship #digitalization #industry #ebc

ታሪክ የሰራው የፓሪሱ የጸሎት መርሃግብር
#ethiopia | በፈረንሳይ ፓሪስ ስታድ ደ ፍራንስ በሚካሄደው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የፀሎት መርሃ ግብር ለመሳተፍ ከ80 ሺህ በላይ ወጣቶች በአንድ ሰዓት ውስጥ መመዝገባቸው ተገለፀ።
በቀጣዩ መስከረም 15 2019 ዓ.ም. ለሚካሄደው የጸሎት መርሃ ግብር ቦታ የመያዝ ሂደቱ በትላንትናው እለት ነሐሴ 4 ቀን የተጀመረ ሲሆን ከ17 እስከ 35 ዓመት የሆናቸው ወጣቶች የሚሳተፍ ይሆናል።
ከ100,000 በላይ ወጣቶች በጸሎትና በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ከጳጳሱ ጋር በሚኖራቸው ቆይታ የሚሳተፉ ይሆናል ተብሏል።
መርሃ ግብሩ ለአራት ቀን በሚቆየው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የፈረንሳይ ጉብኝት ውስጥ ከተካተቱት ዋና ዋና ኩነቶች አንዱ እንደሆነ ተገልጿል።
የፈረንሳዩ ስታድ ደ ፍራንስ ስታዲየም የመያዝ አቅም ከ80,000 በላይ ሰዎችን ቢሆንም የተዘጋጁት ቦታዎች በሙሉ በአንድ ሰዓት ውስጥ መጠናቀቃቸው እጅግ አስደናቂ ሆኗል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በፓሪስ በሚቆዩበት ጊዜ ከዚህ መርሃ ግብር በተጨማሪ በኖትር ዳም የጸሎት መርሃ ግብር የሚያደርጉ ሲሆን ታላቅ ህዝባዊ ቅዳሴም ይካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #france #visit #popeleo #youths #youthvigil #prayer #notredame #mass

የትግራይን ወጣት ከብርሃን የለየው ትውልድ በላው የክፋት ቋት
****************
ሥልጣን እና የዘረፋ ገንዘብ ለማካበት ሲል የተጠነሰሰው ሕገ-ወጡ የህወሓት ቡድን፣ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በትግራይ ወጣቶች ደም መኖርን ብቸኛ የህልውናው ማረጋገጫ አድርጎታል።
ይህ የክፋት ቋት የሆነው አረመኔ ቡድን የትግራይን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መዋቅር አፈራርሶ፣ የደም ነጋዴነቱን ዛሬም ድረስ አጠናክሮ ቀጥሎበታል። ቡድኑ የትግራይን ወጣት የሰው ኃይል ለጥቂት አመራሮቹ ስግብግብ ፍላጎት እና ወታደራዊ እብደት ማሳኪያ በማድረግ በርካታ እናቶችን ያለ ጧሪና ደጋፊ ያስቀረ ጨካኝ ስብስብ ነው።
ይህ ደም መጣጭ ቡድን በይፋ ባወጣው የግዳጅ አፈሳ አዋጅ፣ ምስኪኑን የትግራይ ወጣት ወደማያባራ የጦርነት እሳት እየማገደው ይገኛል። ያልታፈሱት ደግሞ ከዚህ የክፋት ኃይል አፈና ሕይወታቸውን ለማትረፍ ሲሉ፣ ቀን ከሌት በየገደሉ እና በየጫካው እየተሽሎከሎኩ የፍርሃት ኑሮን ለመግፋት ተገደዋል።
የቡድኑን የጥፋት አዋጅ የተቃወሙ እና ልጆቻቸውን ለሞት አንሰጥም ያሉ ቤተሰቦች በእስራት፣ በድብደባ እና ከቤት ንብረታቸው በመፈናቀል ከፍተኛ ዋጋ እየከፈሉ ይገኛሉ።
ይህን በደል የጭካኔ ጥግ የሚያብለው ደግሞ፣ የሕገ-ወጡ ቡድን አመራሮች የሚሠሩት አስነዋሪ ድርጊት ነው። እነዚህ የጥፋት ሐዋርያት የገዛ ልጆቻቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን በአውሮፓ እና በአሜሪካ ታላላቅ ከተሞች በተንደላቀቀ የቅንጦት ሕይወት እያኖሩ እና በውድ ትምህርት ቤቶች እያስተማሩ፤ የድሃውን ልጅ ግን በግዳጅ አፍሰው ለጥይት ማብረጃነት ይገብሩታል። የትግራይ እናት በልጇ መርዶ ደም ዕንባ ስታለቅስ፣ የአመራሩ ልጆች ግን በምዕራቡ ዓለም በዘረፉት የሕዝብ ሀብት ይንደላቀቃሉ።
በዚህ የክረምት ወቅት በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚገኙ ወጣቶች የወደፊት ብሩህ ሕይወታቸውን የሚገነቡበት ወርቃማ ዕድል አግኝተዋል። በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በተጀመረው እና ዒላማውን ወደ ሰባት ሚሊዮን ባሳደገው የ"አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች" ታላቅ ሀገራዊ ኢኒሼቲቭ፣ መላው የሀገሪቱ ወጣቶች በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በዳታ ሳይንስ፣ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዘርፎች ነፃ የሥልጠና ዕድል እየተጠቀሙ መጻኢውን ዓለም እየተቀላቀሉ ነው።
ሆኖም በዚህ አጥፊ ቡድን የታገተው የትግራይ ወጣት ከዚህ ወርቃማ የዕረፍት ጊዜ እና ሀገራዊ የቴክኖሎጂ አብዮት ተነጥሎ በሞት ጥላ ሥር እንዲያልፍ ተፈርዶበታል።
ይህ ፀረ-ሕዝብ ቡድን የትግራይን ወጣት ከዲጂታሉ ዓለም እና ከሥልጣኔ አግልሎ፣ ትምህርት ቤቶችን የጦር ካምፕ አድርጎ፣ ዛሬም የሕዝብን ስቃይ ለፖለቲካ ቁማር እና ለልመና ንግድ እየተጠቀመበት ነው።
ልክ በ1977ቱ የድርቅ ጊዜ ለእርዳታ የመጣውን እህል ሸጦ ሕዝብን ለርሃብ እንደዳረገው ሁሉ፣ አሁንም በፈጠረው ቀውስ ኅብረተሰቡን ለዕርዳታ ጥገኛ አድርጎታል። ይህ ደግሞ መጻኢውን የክልሉን ሁኔታ እጅግ አሳዛኝ ወደሆነ አቅጣጫ እየመራው ይገኛል።
ስለሆነም የትግራይ ሕዝብ እና ወጣቱ ይህን የክፋት ምንጭ እና ትውልድ ገዳይ ተባይ ከላዩ ላይ አራግፎ በመጣል፣ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ ጋር የሰላም፣ የትምህርት እና የልማት ተጠቃሚ ወደሚሆንበት ብርሃናማ መንገድ ሊወጣ ይገባል።
#ethiopia #tigray #youths #ethiocoders #digitalethiopia #ebc

Comments