2 days ago
ከሥርዓት ጥበቃ ወደ ዜጎች ደኅንነት፦ የፀጥታ ተቋማቱ ጥልቅ ሪፎርም
************************
የዓለማችን የፀጥታና ደኅንነት ስጋቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ውስብስብ እና ተለዋዋጭ እየሆኑ መጥተዋል። በዚህም ከባህላዊ ጦርነቶች ባሻገር ከሳይበር ጥቃት እስከ ሐሰተኛ መረጃዎች ሥርጭት ድረስ እጅግ ልዩ ባህርይ የተላበሱ ጉዳዮች በመከሰት ላይ ይገኛሉ።
ለዚህም የአሁኑ ትውልድ ጊዜውን የዋጀ፣ ውስብስብ ፈተናዎችን መመከት የሚያስችል ሁለንተናዊ ዕውቀት፣ ብቃትና ዘመናዊ ትጥቅ የታጠቀ አይበገሬ ተቋም የመገንባት ኃላፊነት ከትከሻው ላይ ወድቋል።
በሀገራችን ነባራዊ ዳራ ደግሞ፣ የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት የረጅም ዘመን የፖለቲካ ስብራታችን ዋነኛ ማሳያ ሆነው ቆይተዋል።
ከሪፎርሙ በፊት ተቋማት ነፃ፣ ገለልተኛ እና ሕዝባዊ ሆነው ከመገንባት ይልቅ፣ ውስን ርዕዮተ ዓለምን ወይም የጥቅም ቡድንን ለማስጠበቅ የቆሙ ነበሩ። በዚህም ምክንያት ሥርዓቱን ለመጠበቅ ሲሉ ለዜጎች ሰብዓዊ መብት ጥሰት መባባስ ዋነኛ መሣሪያ በመሆን አገልግለዋል።
ተቋማቱን ከፖለቲካ ወገንተኝነት በማላቀቅ “ሀገር አስቀጥል” ተቋማት እንዲሆኑ ሙያዊ ነፃነታቸውን በማረጋገጥ በዘመናዊና አስተማማኝ መሠረት ላይ ለመገንባት እንደ ሀገር የተጀመረው ሪፎርም ወቅቱ የሚጠይቀው ቁልፍ ተግባር ሆኖ ተገኝቷል።
የሪፎርሙ ውጣ ውረድ እና ጉዞ
ይህ ጥልቅ የለውጥ ጉዞ ፈፅሞ አልጋ በአልጋ አልነበረም። ለዘመናት በአምባገነን ሥርዓቶችና በኋላቀር እሳቤ ተተብትበው የኖሩት ተቋማት፣ እንኳን የፖለቲካ ሥርዓቱን መቀየር ቀርቶ ራሳቸው ጥልቅ ስብራት የነበረባቸው በመሆኑ፣ ሪፎርሙን ከውስጥ መጀመር ግዴታ ነበር።
በሌላ በኩል በተለያዩ አካባቢዎች የነበሩ በኢትዮጵያ ጠላቶች የተጠነሰሱ ግጭቶች እና የጽንፈኝነት እንቅስቃሴዎችን እየመከቱ፣ ኢትዮጵያን እያስቀጠሉ፣ ጎን ለጎን ራሳቸው በጥልቅ ሪፎርም ውስጥ የማለፍ ፈተናን ተሻግረዋል።
ይሁንና የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች እነዚህን እንቅፋቶችና ፈተናዎች ወደ ዕድል በመቀየር ተቋማቱን ከስብራት አውጥቶ ወደ ዘላቂ የሰላም አስከባሪነት አሸጋግረዋቸዋል።
ከየት ወደየት? እይታ እና ተልዕኮ
በሪፎርሙ ሂደት ተቋሞቻችን ኢትዮጵያን በብቃት ማስቀጠል ችለዋል፦
• ተቋማቱ ከርዕዮተ ዓለም ጠባቂነት ሙሉ በሙሉ ተላቅቀው፣ የኢትዮጵያ እና የዜጎቿ የጋራ ደኅንነትና ክብር ዘብ ወደመሆን ተሸጋግረዋል።
• ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ በመሆን፣ ሕገ መንግሥቱን ብቻ መሠረት አድርገው ሕዝብን በገለልተኝነት የሚያገለግሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል።
• የሪፎርሙ ርዕይ በሕዝብ አመኔታ የተገነባ፣ ለሀገር ውስጥና ለቀጣናዊ ስጋቶች የማይበገር ተወዳዳሪ ተቋም መፍጠር አስችሏል።
• በተልዕኮውም የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ፣ የሀገርን ድንበር ማስከበርና፣ ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን ከአፍራሽ እንቅስቃሴዎች አጥብቆ መከላከል ተችሏል።
የሪፎርሙ የትግበራ አግባብነት የሚለካው የሰው ኃይልን በአዲስ የሙያ ሥነ ምግባር በማነፅ እንዲሁም ግልጽነትና ተጠያቂነትን በሚያሰፍን የሕግ ማዕቀፍ ውስጥ በማስገባት ነው። ሪፎርሙ የፀጥታ መዋቅሩ ሠፊ ሕዝባዊ መሰረት እንዲኖረው ያደረገ አካታች አሠራርንም ዘርግቷል።
ዘመናዊ ጋሻ ለመሆን ቴክኖሎጂ ወሳኝ በመሆኑም ተከታታይ እርምጃዎች ተወስደዋል።
• ሰብዓዊ፣ መዋቅራዊና ቴክኖሎጂያዊ ብቃት ያላቸው የጸጥታና ደኅንነት ተቋማት ተፈጥረዋል።
• የመከላከያ ቴክኖሎጂዎችን በሀገር ውስጥ በማላመድና በመፍጠር፣ ለሠራዊቱ የሚያስፈልጉ ትጥቆችን የማሟላት ስኬት ተመዝግቧል።
• አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን፣ የቢግ ዳታ ጥልቅ ትንታኔንና የሳይበር ደኅንነትን በመጠቀም፣ ወንጀልን ከመፈፀሙ በፊት የመተንበይና የማክሸፍ የላቀ አቅም ተገንብቷል።
በአጠቃላይ በፀጥታና ደኅንነት ተቋማት ስኬታማ ሪፎርም የትናንቱን የመዋቅር ክፍተት በመጠገን፣ ኢትዮጵያን ከነባር ጠላቶች በአስተማማኝ ሁኔታ መከላከል የሚችል አቅም መፍጠር ተችሏል።
ዘመኑን የዋጀው ይህ ጋሻ የዜጎችን መብት የሚያስከብርና የሀገር ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጥ የማዕዘን ድንጋይ ነው።
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ
#ethiopia #fdredefenseforce #ethiopianfederalpolice #ethiopianairforce #ebc

4 months ago
✈️ የጀግኖች መፈልፈያ
- የኢትዮጵያ አየር ኃይል አካዳሚ የበረራ ትምህርት ቤት! 🇪🇹
#ethiopia | የ90 ዓመታት የጀግንነት ጉዞ እና የ5ኛው ጀነሬሽን ቴክኖሎጂ ሽግግር
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ስሙ ሲነሳ አብረው የሚነሱት እንቁ አብራሪዎቹ ናቸው። ከእነዚህ ጀግኖች በስተጀርባ ደግሞ በፍፁም ወታደራዊ ዲስፕሊን እና ጥብቅ ስልጠና የሚያበቃው የ90 ዓመታት ታሪክ ያለው የአየር ኃይል አካዳሚ የበረራ ትምህርት ቤት አለ።
አየር ኃይሉን ለ28 ዓመታት ያገለገሉት፣ የSU-27 Interceptor ተዋጊ አውሮፕላን አብራሪ እና የL-39 Jet Trainer አስተማሪ የሆኑት የአካዳሚው የበረራ ት/ቤት አዛዥ ኮሎኔል ጃንቦ አዛገ እንደገለጹት፤ አካዳሚው አሁን ላይ የአምስተኛውን ጀነሬሽን (5th Generation) ቴክኖሎጂ በመታጠቅ ዘመኑን የዋጁ ብቁ አብራሪዎችን እያፈራ ይገኛል።
የአየር ኃይል አካዳሚን የስልጠና ሂደት እና የቴክኖሎጂ አቅም የሚያሳይ ሙሉ ቪዲዮ ለመመልከት ይህን ሊንክ ይጫኑ፡
👇👇👇
https://youtu.be/HiHLqaF1V...
ክብር ለሀገር ጠባቂ ጀግኖቻችን! 🫡🇪🇹
#ethiopianairforce #airforceacademy #aviation #ethiopia #militarystrength #su27 #heroes #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

5 months ago
የጥቁር አንበሳ የአየር ላይ ትርዒት
#ethiopianairforce #airshow #ethiopia #airforcelive #ethiopiandefense #blacklionairshow2026
#ethiopianairforce #airshow #ethiopia #airforcelive #ethiopiandefense #blacklionairshow2026
5 months ago
✈️ የአቪዬሽን ኤክስፖ 2026 🇪🇹
"የወደፊቱን የአቬሽን አቅም በጋራ እንገንባ!"
#ethiopia | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፤ የኢፌዲሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው "የአቪዬሽን ኤክስፖ 2026" የመክፈቻ መርሐግብር ላይ ተገኝተዋል።
የኤክስፖው ዋና ዓላማዎች፡-
✅ የኢትዮጵያን የአቪዬሽን እና ኤሮስፔስ ልማት ማፋጠን
✅ ዓለም አቀፍ ትብብርን በማጠናከር የቀጣናው የፈጠራ ማዕከል መሆን
✅ በክህሎት ልማት እና በዘላቂ እድገት አህጉራዊ ተፅእኖ መፍጠር
ይህ ኤክስፖ ሀገራችን በአቪዬሽን ዘርፍ ያላትን ጽኑ አቋም እና ለወደፊት የቴክኖሎጂ እድገት ያላትን ዝግጁነት የሚያሳይ ነው።
#ethiopianairforce #aviationexpo2026 #pmabiyahmed #ethiopia #aviation #aerospace #90thanniversary

Comments