15 days ago
የኢትዮጵያ የማድረግ አቅም ልዕልና እና የዓለም አቀፍ ተፈላጊነት አዲስ ምዕራፍ
*************************
ኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎችን በጽናት ተሻግራ የራሷን የልማትና የስኬት መስመር በግልጽ በማስመር ላይ ትገኛለች። አሁን የምንገኝበት የዕድገት ደረጃ ሀገራችን በዓለም አቀፍና አህጉራዊ መድረክ ላይ ያላትን የማድረግ አቅም በተግባር ያረጋገጠችበት እና ተፈላጊነቷን በከፍተኛ ሁኔታ ያሳደገችበት ስትራቴጂካዊ ምዕራፍ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “ትናንት ከነበርንበት ከፍ ብለናል እርሱ አይካድም፤ መድረስ ከሚጠበቅብን ግን ብዙ ይቀረናል” ሲሉ ያስተላለፉት መልእክት ኢትዮጵያ የደረሰችበትን ከፍታ የሚያሳይና ለቀጣዩ ጉዞ ከፍተኛ መነቃቃትን የሚፈጥር መርሕ ነው።
አክለውም “ኢትዮጵያ ወደፊት መሄድ የምትፈልግ ከሆነ ራሷን እንደ ሳይክል ነጂ ማየት አለባት፤ አንድ ሳይክል ነጂ ሁለት ነገሮች ይጠበቅበታል ወደፊት መሄድ እና ሚዛን መጠበቅ” ሲሉ ያቀረቡት ፍልስፍና የዕድገትን ፍጥነት ከማክሮ-ኢኮኖሚ፣ ከማኅበራዊ ፍላጎቶች እና ከዘላቂ ሰላም ጋር አስተሳስሮ የመምራት ጥበብን ያሳያል።
ለዘመናት የቁጭት ምንጭ ሆኖ የቆየው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዛሬ የነጻነታችን እና የማድረግ አቅማችን ህያው ማሳያ ሆኗል።
በግድቡ አማካኝነት በጉባ ምድር የተፈጠረውና 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ የመያዝ አቅም ያለው ባለ 240 ኪሎ ሜትር ርዝመቱ የንጋት ሐይቅ፤ የአካባቢውን ሙቀት ወላፈን ወደ ነፋሻማ ኤኮ-ቱሪዝም ቀጣና ከመቀየሩም በላይ የምሥራቅ አፍሪካን የኃይል ትስስር እውን በማድረግ የኢትዮጵያን የጂኦ-ፖለቲካዊ ልዕልና እና ተፈላጊነት ከፍ አድርጎታል።
በተመሳሳይ በስንዴ ልማት፣ በሌማት ትሩፋት፣ በኢንዱስትሪና በቴክኖሎጂ የተመዘገቡት እመርታዎች የዚሁ የማድረግ አቅም ውጤቶች ናቸው።
የወደፊቷን ታላቅ ኢትዮጵያ ገጽታ የሚቀርጹ ሜጋ ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያን በቀጣናውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም ተወዳዳሪ እያደረጓት ይገኛሉ።
በዓመት እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን ለማስተናገድ የተነደፈውና የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታው እየተፋጠነ ያለው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ የሜጋ ኤርፖርት ከተማ ፕሮጀክት፣ የኢትዮጵያን የአቪዬሽን መሪነት ይበልጥ የሚያጠናክር ግዙፍ መሠረተ ልማት ነው።
በዓመት 3 ሚሊዮን ቶን ለማምረት የተነደፈው የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ እና 3.5 ሚሊዮን ቶን ድፍድፍ ነዳጅ የማጣራት አቅም ያለው የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክቶችም ሀገራዊ ምርታማነትንና ራስን የመቻል አቅምን የሚያረጋግጡ ናቸው።
ከሩሲያው ‘ሮሳቶም’ እና ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) ጋር በመተባበር በሁለት ሪአክተሮች እስከ 2 ሺህ 400 ሜጋ ዋት ኃይል ለማመንጨት የተያዘው የኑክሌር ቴክኖሎጂ ልማትም በሕክምና፣ በግብርና እና በኢንዱስትሪ ዘርፎች የቴክኖሎጂ ሽግግር በማምጣት የኢትዮጵያን የወደፊት አቅም ወደ አዲስ ከፍታ ያሸጋግራል።
እነዚህ ተሰናስለው የተያዙ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን የማድረግ አቅም እያደገ መምጣቱን እና በዓለም አቀፍ መድረክ ተፈላጊነቷ መላቁን የሚያስመሰክሩ ናቸው።
ኢትዮጵያ በጀመረችው የመደመር መንገድ ላይ በፍጥነትና ሚዛኗን ጠብቃ ወደፊት በምትገሰግስበት ጊዜ፣ የታለመው የበለጸገች እና በዓለም መድረክ የታፈረች ሀገር የመገንባት ራእይ በተጨባጭ እውን ይሆናል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopiarising #gerd #megaprojects #aviationhub #sustainabledevelopment

16 days ago
ጉድ በል ጎንደር ማለት አሁን ነው! 3 ጠቅላይ ሚኒስትር፣ 7 የክልል ፕሬዚዳንት፣ ፕሮጀክቱ ከተጀመረ በኋላ የተወለደው አሁን እዚያ እየሰራ ነው - 94% የደረሰው ታሪካዊው የመገጭ ግድብ! 👏 #gondar #megechdam #ethiopiannews #megaprojects #inspiration

21 days ago
የሕዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ የፈጠረው ግዙፍ አቅም
**********************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምረቃ ወቅት የተናገሩት "ከሕዳሴ ግድብ በፊት የነበረችው ኢትዮጵያ እና ከግድቡ በኋላ የምትኖረው ኢትዮጵያ አንድ አይደሉም" የሚለው ንግግር ዛሬ በተግባራዊ እውነታነት የተረጋገጠ ብሔራዊ መገለጫ ሆኗል።
በዜጎቿ የተቀናጀ ዕውቀት እና ጥረት የተጠናቀቀው ይህ ታላቅ ግድብ ለዘመናት ተጭኖብን የነበረውን የዕርዳታ እና ጥገኝነት አስተሳሰብ በመስበር ኢትዮጵያ በራሷ ብቃት እና አቅም መቆም እንደምትችል ለዓለም ያሳየችበት ታላቅ ድል ነው።
ግድቡ ከ5 ሺህ 150 ሜጋዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት የውስጥ አቅርቦትን ከ50 በመቶ በላይ ከመሸፈኑ ባሻገር፣ ለጎረቤት ሀገራት የኃይል አቅርቦት በመዘርጋት ኢትዮጵያን የምሥራቅ አፍሪካ የኢነርጂ ማዕከል አድርጓታል።
የሕዳሴው ግድብ ፍጻሜ የኃይል ማመንጫ ተቋም ከመሆን ባለፈ ባለፉት አምስት ዓመታት የደረጀውን አዲስ እና ፈጣን የፕሮጀክት ትግበራ አቅም ያበሰረ የመንደርደሪያ ምዕራፍ ነው።
እነሆ ከሕዳሴው በኋላ ያለችው ኢትዮጵያ ግዙፍ እና ፈጣን አቅም የገነባች መሆኗን በተግባር እያሳየች ትገኛለች።
ቀደም ሲል 5 ቢሊዮን ዶላር የሚፈጀውን ታላቁን የሕዳሴ ግድብ ለመገንባት ከዐሥር ዓመታት በላይ ስትታገል የነበረችው ኢትዮጵያ፣ ዛሬ በፈጠረችው ከፍተኛ የአሠራር ቅልጥፍና እና ብሔራዊ የፋይናንስ አቅም በአንድ ጊዜ 30 ቢሊዮን ዶላር የሚፈጁ አዳዲስ ሜጋ ፕሮጀክቶችን የመተግበር ግዙፍ ከፍታ ላይ ደርሳለች።
ይኸውም ከ5 ቢሊዮን ዶላር ነጠላ ፕሮጀክት ትግበራ ወደ 30 ቢሊዮን ዶላር የብዙ ፕሮጀክቶች አስተዳደር የተደረገ የስድስት እጥፍ አቅም ዕድገት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማሳያ ነው።
በግድቡ ምረቃ ዕለት በጉባ የተበሰሩት እነዚህ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን ኢንዱስትሪ፣ አቪዬሽን እና ማኅበራዊ ልማት ከመሠረቱ የሚቀይሩ ናቸው።
ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በዓመት 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ያለውና የኢትዮጵያ አየር መንገድን አህጉራዊ መሪነት የሚያጸናው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጥናት፣ እንዲሁም የነዳጅ ገቢ ምርት ወጪን በማስቀረት የኢነርጂ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጡት የተፈጥሮ ጋዝ እና የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካዎች የዚሁ ግዙፍ አቅም ውጤቶች ናቸው።
በተጨማሪም የግብርናውን ዘርፍ ከውጭ ጥገኝነት ነፃ የሚያወጣው የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታው እየተፋጠነ ነው። በሚቀጥሉት 5 ዓመታት የሚገነቡት 1.5 ሚሊዮን የመኖሪያ ቤቶች የዜጎችን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሕይወት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራሉ።
ከእነዚህ የጉባ ብስራት ፕሮጀክቶች ባሻገር፣ በአዲስ አበባ ተጀምሮ ወደ 75 በላይ ከተሞች የተስፋፋው የኮሪደር ልማት የከተሞችን ምርታማነት እና የሎጂስቲክስ ቅልጥፍና በከፍተኛ ደረጃ ቀይሮታል።
የወልመል፣ የጎዴ እና የቄጦ የመስኖ ግድቦች መጠናቀቅ፣ የገጠር ሞዴል መንደሮች ልማት እና አርሶ አደሩን ሀብት አስይዞ ብድር የሚያገኝበት የግብርና ፋይናንስ ፍኖተ-ካርታ መዘርጋቱ የዚሁ ሁለንተናዊ አቅም አካላት ናቸው።
ከሕዳሴው ግድብ ማጠናቀቅ በኋላ ኢትዮጵያ ያዳበረችው አቅም የኃይል አቅርቦትን ብቻ ሳይሆን ጠንካራ ብሔራዊ የራስ መተማመንን፣ ግዙፍ የፋይናንስ እንቅስቃሴን እና የሜጋ ፕሮጀክቶች ትግበራ ጥበብን ያካተተ ነው።
በአሁኑ ወቅት የተጀመሩት የ30 ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክቶች እና የኮሪደር ልማቶች አዲሷ ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ የኢኮኖሚ እና የሎጂስቲክስ የበላይነቷን በማያወላውል መሠረት ላይ እየገነባች መሆኗን የሚያረጋግጡ ሕያው ምስክሮች ናቸው።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #gerd #megaprojects #development #africa #infrastructure

23 days ago
ጉድ በል ጎንደር ማለት አሁን ነው! 3 ጠቅላይ ሚኒስትር፣ 7 የክልል ፕሬዚዳንት፣ ፕሮጀክቱ ከተጀመረ በኋላ የተወለደው አሁን እዚያ እየሰራ ነው - 94% የደረሰው ታሪካዊው የመገጭ ግድብ! 👏 #gondar #megechdam #ethiopiannews #megaprojects #inspiration
3 months ago
ልክ እንደ ሕዳሴ ግድብ ሁሉ ሀገርን ከስር መሠረቱ የሚቀይሩት አዳዲስ ታላላቅ የልማት ምዕራፎች የጉባ ብሥራቶች ኢትዮጵያን ወደ የትኛው ከፍታ ያሽጋግራታል? ታላቁ የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የልማት ጉዟችን ማብቂያ ሳይሆን ይልቁንም የኢትዮጵያ አዲስ ታሪክ መጀመሪያ መሆኑን በተግባር እያሳየ ይገኛል። #ebcdotstream #gerdcompletion #renaissancedam #sovereigntyinaction #megaprojects
Sponsored by
Surafel
4 months ago
ከተግባር ከፍታ ወደ ብሔራዊ ጽናት - የኢትዮጵያ የሜጋ ፕሮጀክቶች የስኬት ዐሻራ
****************
(የዕለቱ መልእክት)
ኢትዮጵያ ታሪክን በንግግር እና በምኞት ሳይሆን፣ በተግባር እና በግዙፍ ፕሮጀክቶች የምትቀይርበት ልዩ የዕድገት ምዕራፍ ላይ ትገኛለች።
“አፍ ተናግሮ እግር ሲያፍር፣ ልብ አዝኖ ዐይን ሲያለቅስ” እንደሚሉት ሳይሆን፣ ዛሬ በሀገራችን እየታየ ያለው የቃል እና የተግባር መገጣጠም ነው።
“ከነገሩ ጽናቱ” እንዲሉ በተግባር ከፍታ የተመሰከረላቸው ግዙፍ የልማት አውታሮች የብሔራዊ ጽናታችን ማማ ሆነው በግልጽ እየታዩ ነው።
ለዚህም በቢሾፍቱ እየተገነባ ያለው ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ በኢንቨስትመንት መጠኑ እና በሥራው ግዝፈት በአፍሪካ ታሪክ ብቸኛው ፕሮጀክት መሆኑ ቀዳሚ ማሳያ ነው።
“አውቆ የተነገረ ከልብ ይደርሳል” እንደሚባለው በአዲስ አበባ ከተማ ታቅደው በአጭር ጊዜ የተጠናቀቁት እንደ ወዳጅነት ፓርክ፣ እንጦጦ ፓርክ፣ የወንዝ ዳር ልማቶች፣ የሳይንስ ሙዚየም እና የዓድዋ ድል መታሰቢያ ያሉ ታላላቅ ፕሮጀክቶች መሬት ላይ የወረዱ እውነታዎች እንጂ የሩቅ ሕልሞች አይደሉም።
ከዚህም ባሻገር ሌሊት እና ቀን የተሠራው እና እየተሠራ ያለው የኮሪደር ልማት የመንግሥትን የፕሮጀክት ፈጻሚነት አቅም ቁልጭ አድርጎ ያመላከተ ሲሆን፣ ይህ ስኬት መንግሥት ላለፉት ዓታት በትኩረት ሲተገብራቸው የቆያቸው የልማት አፈጻጸሞች ቀጣይ ማሳያ ነው።
ቀደም ሲል ይስተዋሉ የነበሩ መዘግየቶችን በመስበር እንደ ስኳር ፕሮጀክቶች ያሉ ግዙፍ ተቋማትን ማጠናቀቅ መቻሉ የመንግሥት ቁርጠኝነት በተግባር የታየበት ነው። ከሁሉም በላይ ደግሞ የኢትዮጵያውያን ዳግማዊ ዓድዋ የሆነው የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ እና በቅርቡ የተበሰሩት የጉባ ብሥራቶች፣ ሀገራችን የማይቻሉ የሚመስሉ ታላላቅ ሕልሞችን የመፈጸም አቅም እንዳላት ለዓለም የመሰከሩበት ታሪካዊ ምዕራፍ ናቸው።
በአፈጻጸም ሂደት ላይ የሚያጋጥሙ ማነቆዎችን መንግሥት በግልጽ ለሕዝብ የሚያሳውቅ ከሆነ፣ ሕዝቡ ውሳኔዎችን የመረዳት እና የመቀበል ዝንባሌው ይጨምራል። “እውነት እና ንጋት እያደር ይጠራል” እንዲሉ ግልጽነት መተማመንን ይፈጥራል።
በገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ (እንደ ወንጪ፣ ኮይሻ፣ ጎርጎራ) ፕሮጀክቶች ላይ ከሕዝብ የተሰበሰበው ሀብት እንዴት ወደ ተጨባጭ ልማት እንደተለወጠ ደረጃ በደረጃ ለሕዝቡ ይፋ መሆኑ ግልጽነትን አጠናክሯል። የመደመር እሳቤም ዋና ምሰሶ ይኸው ነው - ሀገርን በጋራ መገንባት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቢሾፍቱ እየተገነባ ያለው ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግዝፈት እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም አስመልክተው ሲናገሩ፤ "ይህንን ያህል ማሽን የሚንቀሳቀስበት ሥራ እንደ ሀገር መርተን አናውቅም፤ የመጀመሪያችን ነው። ሥርዓት ቢኖረን፣ በየቀኑ ሥራዎቻችንን ማየት ብንችል፣ አብዛኛው ፕሮጀክት በተጀመረለት ጊዜ እና ጥራት አልቆ የሕዝብን እርካታ ሊያረጋግጥ ይችላል" ብለዋል።
ይህ ተከታታይነት እና ወጥነት ያለው የፕሮጀክቶች አፈጻጸም በቁስ አካል ደረጃ ከሚታዩ ውጤቶች ባሻገር፣ በሀገራችን የአስተዳደር ሥነ ልቦና ላይ ታላቅ የባህል ለውጥ ፈጥሯል። የዘገምተኛነት እና የቢሮክራሲ ሰንሰለትን ሙሉ በሙሉ በመበጠስ፣ አሁን ላይ ሌሊት እና ቀን ሳይለዩ የማያቋርጥ ሥራ የመሥራት፣ የቀጠሮ ትክክለኛነት እና ፈጣን ውሳኔ የመስጠት አዲስ ሀገራዊ የፈጠነ ሥራ ባህል ተተክሏል።
የሜጋ ፕሮጀክቶች መሳካት ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸው በላይ የኅብረተሰቡን ሥነ ልቦና የማነጽ እና የጋራ ማንነትን የማንቃት ታላቅ አቅም አላቸው። ለረጅም ዘመናት በአንዳንዶች ዘንድ ይንጸባረቅ የነበረውን የተሸናፊነት እና የዝቅተኝነት ሥነ ልቦና ሙሉ በሙሉ በመስበር፣ “እኛም እንችላለን” የሚል የጽኑ እምነት እና የሀገራዊ ኩራት ስሜት በትውልዱ ልብ ውስጥ እንዲቀረጽ አድርጓል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሥራው ላይ ለሚታዩት ተግዳሮቶች እና የጥርጣሬ ሐሳቦች በሰጡት ምላሽ፤ "ብዙዎች ‘አትችሉም፣ ገንዘቡም አይገኝም፣ ሥራውን መምራት አይሆንላችሁም’ የሚል እሳቤ ሲያራግቡ ይሰማል። እኛ ደግሞ ‘እንችላለን፤ ይገባናል፤ የሚመጥነን ትልቅ ነገር ነው’ እያልን ነው። ማን እንደሚያሸንፍ ጊዜው ሲደርስ እናያለን" በማለት የሀገራችንን ጽኑ አቋም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ተነሣሽነት እና ብርታት በተደጋጋሚ ታሪክ እየሠሩ መሆናቸውን በተግባር አሳይተዋል።
በመሆኑም መላው ሕዝብ በተባበረ ክንድ ድህነትን ለመስበር፣ የጠለሸ ማንነትን ለመቀየር እና የበለጸገች ሀገር ለትውልድ ለማውረስ “ሳይደክሙ አይታለፍም የኑሮ አቀበት” እንዲሉ በሥራ እና በልፋት ብቻ መረባረብ ይኖርበታል።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
#ebc #ethiopia #megaprojects #pmabiyahmed

Comments