2 months ago
ማያ በጎ አድራጎት ድርጅት በህፃናት የአፈጣጠር ችግር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከማያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር በአፈጣጠር ችግር ምክንያት በሚከሰቱ የጀርባ አጥንት ክፍተት (Spina Bifida) እና የአንጎል ውስጥ ፈሳሽ መከማቸት (Hydrocephalus) ዙሪያ ያተኮረ ልዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ አካሂዷል።
በመድረኩ ላይ እንደተገለጸው በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ44 ሺህ በላይ ህፃናት በእነዚህ የጤና ችግሮች ምክንያት የሚወለዱ ሲሆን፣ ለችግሩ ዋነኛው መንስኤ እናቶች በእርግዝና ወቅት የሚገጥማቸው የፎሊክ አሲድ ወይም የቫይታሚን ቢ9 እጥረት መሆኑ በሰፊው ተብራርቷል።
እነዚህ የአፈጣጠር ችግሮች በህፃናቱ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ሲሆን፣ በተለይም ለዕድሜ ልክ የሚዘልቅ የመንቀሳቀስ መገደብ እና ራስን ችሎ የመፀዳዳት ችግር እንደሚገጥማቸው ተመላክቷል።
ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመከላከል በመንግስት የተጀመረው ምግቦችን በፎሊክ አሲድ የማበልጸግ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የተገለጸ ሲሆን፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩም ይህንን ሀገራዊ ጥረት በግለሰብ፣ በማህበረሰብ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማገዝ ያለመ እንደሆነ ተጠቁሟል።
በመድረኩ ላይ የአካቶ ትምህርት እና የዜጎች ተጠቃሚነት ጉዳይም በስፋት የተነሳ ሲሆን፣ በእነዚህ የጤና ችግሮች የተጠቁ ህፃናት የማህበረሰቡ አካል መሆናቸው ታምኖበት ትምህርትን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶችን የማግኘት መብታቸው ሊከበር እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል።
መርሃ ግብሩ በእነዚህ ህፃናት ሰብአዊ መብት እና ማህበራዊ ተሳትፎ ዙሪያ ሰፊ ውይይት ያደረገ ሲሆን፣ ህብረተሰቡ ለችግሩ ተጋላጭ የሆኑ ወገኖችን ከመገለል እንዲታደግና አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ አሳስቧል።
በዚህ መርሃ ግብር ላይ የፌዴራል ጤና ሚኒስቴር ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ፣ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና የማያ በጎ አድራጎት ድርጅት መስራቾች አስተባባሪዎች ተገኝተዋል።
ከእነዚህም በተጨማሪ የጥበብ ባለሙያዎች፣ የሚዲያ አካላት፣ እንዲሁም የችግሩ ተጋላጭ የሆኑ ህፃናትና ወላጆቻቸው በመሳተፍ ስለ በሽታው መከላከያ መንገዶች እና ስላለው ተግዳሮት በቂ ግንዛቤ እንዲጨበጥ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#healthawareness #ethiopia #spinabifida #hydrocephalus #mayacharitableorganization #publichealth #folicacid #inclusion #addisababa