1 month ago
ንብረት ገዝተው የስም ዝውውር ያላደረጉ ዜጎች በአስቸኳይ እንዲያጠናቅቁ ታዘዘ
#eghiopia | ከሪል እስቴት አልሚዎችም ሆነ ከግለሰቦች በሰነዶች ማረጋገጫ ንብረት ገዝተው፣ እስካሁን ወደ መሬት ተቋማት በመቅረብ የስም ዝውውር ያላደረጉ እና የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ (ካርታ) ያልያዙ ባለንብረቶች ሂደቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲያጠናቅቁ ጥሪ ቀረበ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ መኮንን ያኢ ከኤ ኤም ኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ የስመ-ንብረት ዝውውር በወቅቱ አለመደረጉ ንብረት ገዝተው የባለቤትነት ማረጋገጫ ያልያዙ ዜጎችን ለተለያዩ ከፍተኛ ጉዳቶች እና ለአደጋ እየዳረገ ይገኛል።
የስመ-ንብረት ዝውውር የመጨረሻ ግቡ ገዥው አካል ህጋዊ የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫን እንዲይዝ ማድረግ ቢሆንም፣ በተለያዩ ምክንያቶች ይህንን ሳያደርጉ የቀሩ በርካታ አካላት መኖራቸውን ቢሮው ጠቁሟል።
በመሆኑም ቀደም ባሉ ጊዜያት የመኖሪያ ቤትም ሆነ ማንኛውንም በመሬት ላይ ያረፈ ንብረት ገዝተው የስም ዝውውር ያላደረጉ ባለንብረቶች፣ መብታቸውን ለማስከበርና ለከፋ አደጋ እንዳይጋለጡ ሲባል መንግስት በአስቸኳይ እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
#ethiopia #addisababa #realestateethiopia #landmanagement #amn #propertylawyerthailand

4 months ago
"መካፈል ባህላችን ነው!"
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለሰራተኞቹ ማዕድ አጋራ
#ethiopia | የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ፣ "ሰው ተኮር ተግባራት" ተቋማዊ ባህሉ መሆኑን በተግባር አሳይቷል።
ተጠቃሚዎች
በተቋሙ ውስጥ ዝቅተኛ ደሞዝ የሚከፈላቸው 128 ሰራተኞች የበዓል ማዕድ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።
ዓላማ
በዓላትን ስናከብር ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን በማሰብና ያለንን በማካፈል መሆን እንዳለበት ተቋሙ መልዕክቱን አስተላልፏል።
መልእክት
"የትንሳኤ በዓል የፍቅርና የመስዋዕትነት በዓል በመሆኑ፣ ይህንን ፍቅር ለወገኖቻችን በማካፈል መግለጽ ይገባናል" ሲል ቢሮው ገልጿል።
በዓልን ከወገን ጋር ማክበር ድርብ ደስታ ነው!
#getu #landmanagement #eastersharing #ethiopiantradition #socialresponsibility #addisababa #humanityfirst #የመሬትልማት #ማዕድማጋራት #ትንሳኤ #ኢትዮጵያዊነት #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments