12 days ago
ይህ ውሻ የመጀመርያው የሳጅንነት ማዕረግ የተሰጠው ውሻ በሚል በታሪክ ሰፍሯል።
#ethiopia | በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ከአሜሪካ ወታደሮች ጋር የተሰለፈው ይህ ውሻ ገዳይ ጋዝ (Chemical Weapons) ቀድሞ በማሸተት ጠላትን ድል ያደረገ ውሻ ነው።
ይህ ውሻ ትክክለኛ መጠርያ ስሙ ስቱቢ ሲሆን የክብር መጠርያው ደግሞ ሳጅን ስቱቢ በመባል ይጠራል።
ሳጅን ስቱቢ የጠላት ሰላዮችን በመያዝ እና የቆሰሉ ወታደሮችን በጦር ሜዳ በመፈለግ ረገድ ትልቅ ገድል መስራት የቻለ እንደሆነ ታሪኩ ይናገራል።
በታሪክ የመጀመሪያው የሰራዊት ማዕረግ (ሳጅን) የተሰጠው ውሻ ለመሆንም በቅቷል።
ይህ ውሻ በጦርነት የሚፈጠረውን ከፍተኛ ጭንቀትና ፍርሃት በመቀነስ ለወታደሮች ትልቅ የሞራል እና የስነ ልቦና ብርታት የነበረ ውሻ ነው።
በጦርነት ቦታ ውሾች ያሳዩትና የሚያሳዩት ታማኝነት የሰው እና የእንስሳት ግንኙነት ምን ያህል ጥልቅ እና አስደናቂ እንደሆነ ያሳያል።
የአሜሪካ ጀግና ተደርጎ የሚቆጠረው ሳጅን ስቱቢ ሲሞት አሜሪካዊያን ሀውልት አቁመውለታል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #america #herodog #sergeantstubby

Comments