11 days ago
ዘመኑን የዋጀው ፌዴራል ፖሊስ፤ ከሀገራዊ ሪፎርም እስከ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች መከላከል ስኬት
***************
የሀገራችንን ታሪክና ልዕልና የሚመጥን ዘመናዊ የፖሊስ ተቋም ለመገንባት የተጀመረው ሀገራዊ ሪፎርም፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስን ወንጀልን አስቀድሞ የመከላከል ቁመና ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግሮታል።
የፌዴራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል እንደገለጹት፤ ተቋሙ የሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ባካሄደው ጥልቅ የሪፎርም ትግበራ አሁን ላይ ዘመኑን የዋጀና ውጤታማ ተግባራትን የሚያከናውን ጠንካራ አቅም መገንባት ችሏል።
ይህ አዲስ ተቋማዊ ቁመናም ፖሊስ ከተለዋዋጭ ሁነቶች እና ከዲጂታሉ ዓለም ፈጣን ዕድገት ጋር እኩል እንዲጓዝ ትልቅ አቅም የፈጠረለት ሲሆን፣ በተለይም በዓለም አቀፍና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ በርካታ ስኬታማ ተግባራትን ለማስመዝገብ እንዳስቻለው ተናግረዋል።
ተቋሙ በስኬት ከተወጣቸው ተልዕኮዎች መካከል በየአቅጣጫው መረባቸውን ዘርግተው በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ ተሰማርተው የነበሩ በርካታ ተጠርጣሪዎችን ከነመሪዎቻቸው እጅ ከፍንጅ በመያዝ ለሕግ ማቅረቡ ዋነኛው መሆኑን ኮሚሽነሩ አንስተዋል።
መሰል የደህንነት ስጋቶች በስፋት የሚከሰቱባቸውን ቀጣናዎች በመለየት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ያመለከቱት ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ፤ የብዙ ዜጎችን ሕይወት እየቀጠፈ በሚገኘው በዚህ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ ፖሊስ በቁርጠኝነት ያከናወነው ተግባር በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትና ዕውቅና የተቸረው መሆኑን አብራርተዋል።
በዚህም የተነሳ ተቋሙ ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለም አቀፍ ወንጀሎች ቁጥጥር ዙሪያ አይተኬ ሚናውን እየተወጣ እንደሚገኝ ነው ያመላከቱት።
የወንጀል ድርጊቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየረቀቁና በቴክኖሎጂ የታገዙ እየሆኑ ቢመጡም፣ ፌዴራል ፖሊስ በዛው ልክ ዘመናዊ ቴክኖሎጂንና ስልታዊ አደረጃጀትን በመጠቀም አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ እያጠናከረ እንደሚገኝ መግለጻቸውን የፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል።
በዘርፉ ከሚሰሩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በቅንጅትና በጋራ መሥራት መቻሉ የተቋሙን ተጽዕኖ፣ ተአማኒነትና ተደራሽነት ይበልጥ ከፍ እንዳደረገው የገለጹት ኮሚሽነር ጄኔራሉ፤ ወደፊትም ዘመኑን በዋጀ መንገድ የሕግ የበላይነትን የማስከበር፣ የዜጎችን ደህንነት የማረጋገጥና የሀገርን ሰላም ዘላቂ የማድረግ ስልታዊ ተልዕኮው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
#federalpolice #ethiopia #institutionalreform #bordersecurity #ethiopianbroadcastingcorporation

Comments