Logo
Getu Temesgen
የዓለም ጤና ድርጅት በኢቦላ ቫይረስ ምክንያት ዓለማቀፍ የጤና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ
#ethiopia | ​የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በኡጋንዳ በከፍተኛ ሁኔታ እያገረሸ የመጣውን የኢቦላ ቫይረስ ስርጭት ተከትሎ፣ ወረርሽኙን ይፋዊ የዓለማቀፍ የህዝብ ጤና ስጋት አድርጎ አውጇል።

​የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው (ኤክስ) ባስተላለፉት መረጃ፣ እስካሁን ባለው ጊዜ ውስጥ በቫይረሱ ሳቢያ የ 88 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 300 ያህል ሰዎች ደግሞ በበሽታው መያዛቸውን አረጋግጠዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የኢቦላ ቫይረስ ልክ እንደ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሁሉ የመቀጣጠልና በከፍተኛ ፍጥነት የመስፋፋት አቅም እንዳለው በማስገንዘብ፣ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ አስቸኳይና ጥብቅ የሆኑ የመከላከል ስራዎች በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲተገበሩ ጥሪ አቅርበዋል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
​#ebolavirus #publichealthemergency #who #drtedros #africahealth #globalhealth #breakingnews #thiqaheth

29 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.