9 months ago
''ቴስላ ውሃ በላው''
📌 የቻይናው BYD የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሽያጭ ቴስላን በመብለጥ የዓለም ቀዳሚ ሊሆን ነው
#ethiopia | የቻይናው ግዙፍ ተሽከርካሪ አምራች BYD፣ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (EV) ሽያጭ የኤለን መስኩን ቴስላ (Tesla) ኩባንያን በመብለጥ በዓለም ቀዳሚው አምራች ለመሆን መቃረቡ ተገለጠ።
ኩባንያው ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፣ ዓመታዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሽያጩ በ28 በመቶ እድገት በማሳየት 2 ነጥብ 25 ሚሊየን ደርሷል። ይህ ውጤት BYDን በዘርፉ ቁንጮ ላይ እንዲቀመጥ ያደርገዋል ተብሏል።
የቴስላ ፈተና እና የባለሙያዎች ትንበያ🔎
ቴስላ ዓመታዊ የሽያጭ ሪፖርቱን እስካሁን ይፋ ባያደርግም፣ የዘርፉ ባለሙያዎች ኩባንያው 1 ነጥብ 65 ሚሊየን አካባቢ ተሽከርካሪዎችን ሊሸጥ እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
ይህ ከሆነ ደግሞ ቴስላ ለረጅም ጊዜ ይዞት የቆየውን የመሪነት ስፍራ ለቻይናው ተፎካካሪው ያስረክባል ማለት ነው።
ቴስላ ለገጠመው የሽያጭ መቀነስና ለገበያ ድርሻ መጥበብ እንደ ምክንያቶች የተጠቀሱት፦
* የባለቤቱ የኤለን መስክ አወዛጋቢ ፖለቲካዊ ተሳትፎዎች።
* ከቻይና ተሽከርካሪ አምራቾች እየገጠመው ያለው ብርቱ የዋጋና የቴክኖሎጂ ፉክክር።
* በተለያዩ ሀገራት የታየው የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ናቸው።
🚘 BYD በተለይም ዋጋቸው ተመጣጣኝ የሆኑ የተለያዩ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አማራጮችን ለገበያ ማቅረቡ ለስኬቱ ትልቁን ድርሻ እንደያዘ ተመልክቷል። ይህ የገበያ ለውጥ የቻይና ኩባንያዎች በዓለም አቀፉ አረንጓዴ ኢነርጂ ሽግግር ውስጥ እያገኙት ያለውን የበላይነት የሚያሳይ ነው ተብሏል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#byd #tesla #electricvehicles #evmarket #elonmusk #chinatech #automotiveindustry #greenenergy2026

Comments