3 months ago
ከቦትስዋና መንደሮች እስከ ዓለም አቀፍ መድረኮች፦ የዊሊያም ላስት አስደናቂ ጉዞ
**********************
ስሙ ዊሊያም ማቡዛ ይባላል። ዓለም ግን ዊሊያም ላስት በሚለው ስሙ ይበልጥ ያውቀዋል። በዲጂታል ሚዲያው ዘርፈ አስቂኝ ቪዲዮዎችን በመሥራት ይታወቃል።
ዊሊያም የታዋቂነት ጉዞውን የጀመረው ገና በለጋነት ዕድሜው ቢሆንም፣ ዝነኝነት በቀላሉ አልመጣለትም ነበር።
በ2017 ‘ሀምብል’ በተሰኘው የኬንድሪክ ላማር ሙዚቃ ላይ የተመሠረተ ‘ፓሮዲ' ቪዲዮ ይሠራል።
ይህ ቪዲዮ በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች በመታየቱ፣ ዊሊያም ከአካባቢያዊ ኮሜዲያንነት ወደ ዓለም አቀፍ ዝነኝነት ተሸጋግሯል።
ይሁን እንጂ ዊሊያም በኮሜዲ ብቻ አልተገደበም፤ ሂፕ ሆፕን ከቀልድ ጋር እያዋዛም ተወዳጅነትን አትርፏል።
ይህ ጥረቱ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደ ትልቅ የሙዚቃ ሽልማት መድረክ እጩ ሆኖ እንዲቀርብ እና በሀገሩ ቦትስዋናም በርካታ ሽልማቶችን እንዲያገኝ አስችሎታል።
በሂደትም የአፍሪካ ወጣቶችን የፈጠራ አቅም ለዓለም በማሳየት ከማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪነት አልፎ ትልልቅ የንግድ ተቋማት የሚፎካከሩለት የብራንድ አምባሳደር ለመሆን በቅቷል።
ዊሊያም ላስት ከሰሞኑ በአዲስ አበባ በተካሄደው የመጀመሪያው የአፍሪካ ማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS 2026) ተሳታፊ ነበር።
ዊሊያምን ጨምሮ የጉባኤው ተሳታፊ የነበሩ የአህጉሪቱ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በመዲናዋና በሌሎችም አካባቢዎች የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል። ይህ ጉብኝት በሀገር ገጽታ ግንባታ ረገድ ትልቅ ፋይዳ ያለው ነው።
የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የኢትዮጵያ ጉብኝት የሀገራችንን ገጽታ ከመገንባት ባለፈ፣ አህጉራዊ ትስስርን እንዲሁም የአፍሪካን ታሪክ በአፍሪካውያን የመተረክ አቅምን የሚያጠናክር ነው።
በቢታንያ ሲሳይ
#africa #asmis2026 #addisababa #williamlast #ebc

u1260u12a0u12f2u1235 u12a0u1260u1263 u1208u12cdu1325 u12e8u1270u12f0u1290u1240u12cd u130bu1293u12ca u1272u12adu1276u12a8u122d #addisababa #asmis2026 #ralphdefellowghanains #visitethiopia #africarising #landoforigins #modernaddis ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
በአዲስ አበባ ለውጥ የተደነቀው ጋናዊ ቲክቶከር #addisababa #asmis2026 #ralphdefellowghanains #visitethiopia #africarising #landoforigins #modernaddis
3 months ago
የአፍሪካን ገጽታ እየገነቡ ያሉት የዲጂታል አምባሳደሮች
****************
የአፍሪካን ትክክለኛ ገጽታ ለዓለም የማሳየቱ ታሪካዊ ኃላፊነት ከመደበኛው የሚዲያ ተቋማት ወደ ዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎችና ማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በስፋት እየተሸጋገረ ይገኛል።
በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው የመጀመሪያው የአፍሪካ የማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS 2026) እንደሚያሳየው፣ እነዚህ ግለሰቦች ከዝና ባለፈ ለሀገራዊ ገጽታ ግንባታ እና ለኢኮኖሚ እድገት ቁልፍ ሚና እየተጫወቱ ነው።
በጉባኤው ተሞክሯቸውን ካካፈሉት መካከል አቤል ብርሃኑ በአፍሪካ 3ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ የጉዞ ቪሎገር ሲሆን፣ በቅርቡ በናይሮቢ የዓመቱ ምርጥ የአፍሪካ የጉዞ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተብሎ ተሸልሟል።
አቤል በአማርኛ የሚያቀርባቸው ይዘቶች የሀገር ውስጥ ባህልን ከዓለም አቀፋዊ እውነታ ጋር በማገናኘት ረገድ ትልቅ አቅም አላቸው።
ታዋቂው ጋናዊ ዎዴ ማያ አፍሪካን በተስፋ መነጽር ለዓለም በማሳየት የሚታወቅ ሲሆን፣ አዲስ አበባን ለሥራው መነሻ በማድረግ የኢትዮጵያን የልማት እንቅስቃሴዎችና የኢንቨስትመንት አማራጮች በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ተመልካቾች አሳይቷል።
ናይጄሪያዊው ቪክቶር አዱዋ በቴክኖሎጂና በጊግ ኢኮኖሚ ላይ ትኩረት በማድረግ ወጣቶች በዲጂታል ክህሎት ራሳቸውን እንዲለውጡ የሚያስተምር ሲሆን፣ ኮንጎአዊቷ ማጊ ሙኩታ ደግሞ የአህጉሪቱን ፋሽን ለዓለም ታስተዋውቃለች።
ዩጋንዳዊው ስቲቭ ካንባ ወጣቶች ወደ ዘመናዊ ግብርና እንዲመለሱ የሚያነሳሱ ይዘቶችን ያቀርባል።
በሀገራችንም እንደ ሄኒ የሻነውና ሸገር ዲጂታል ያሉ ፈጣሪዎች በሥራ ፈጠራና በቴክኖሎጂ ላይ ያላቸው ተሳትፎ ከፍተኛ ነው።
እነዚህ እና ሌሎችም ዲጂታል አምባሳደሮች ከመደበኛው ሚዲያ በበለጠ ወደ ወጣቱ የመድረስ አቅም ያላቸው ሲሆን፣ የአፍሪካንና የኢትዮጵያን ታሪክ በአዲስ ዕይታና ወጥ በሆነ መንገድ ለዓለም ለማስተዋወቅ ቁልፍ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ።
በንፍታሌም እንግዳወርቅ
#ethiopia #africa #asmis2026 #digitalambassadors #contentcreators #ethiopianbroadcastingcorporation

የአፍሪካን ታሪክ በአዲስ መልክ እየጻፉ ያሉት የአህጉሪቱ ዲጂታል አምባሳደሮች
**************
በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ ታሪክ የሚነገርበት መንገድ ከመደበኛው ሚዲያ ባለፈ በዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች (Content Creators) እጅ እየወደቀ ይገኛል።
በአህጉሪቱ መዲና አዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው የመጀመሪያው የአፍሪካ የማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS 2026) እንደሚያሳየው፣ እነዚህ ግለሰቦች ከዝና ባለፈ ለአህጉራዊ ገጽታ ግንባታ እና ለኢኮኖሚ ዕድገት ቁልፍ ሚና እየተጫወቱ ነው።
በጉባኤው እየተሳተፉ ካሉ የአህጉሪቱ የማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች መካከል የተወሰኑትን እናስተዋውቃችሁ፡-
አቤል ብርሃኑ በአፍሪካ 3ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ የጉዞ ቪሎገር (Travel Vlogger) ሲሆን፣ በቅርቡ በናይሮቢ በተካሄደው 'Africa Golden Awards 2026' የዓመቱ ምርጥ የአፍሪካ የጉዞ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተብሎ ተሸልሟል። አቤል በአማርኛ ቋንቋ የሚያቀርባቸው ይዘቶች የሀገር ባህልን እና ዓለም አቀፋዊ እውነታዎችን በማገናኘት ረገድ ትልቅ አቅም አላቸው።
ዎዴ ማያ (Wode Maya) ጋናዊ የአፍሪካ ተቆርቋሪ ሲሆን፣ አፍሪካን "በተስፋ እና በኩራት" መነጽር ለዓለም በማሳየት ይታወቃል። አዲስ አበባን ለሥራው እንደ መነሻ (Launchpad) በመጠቀም የኢትዮጵያን የልማት እንቅስቃሴዎች፣ ዘመናዊ ከተሞች እና የኢንቨስትመንት አማራጮች በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ተመልካቾቹ አሳይቷል። የእርሱ ይዘቶች የአህጉሪቱን አሉታዊ ገጽታ በመቀየር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እና ቱሪዝምን በማበረታታት ረገድ ቀዳሚ ናቸው።
ቪክቶር አዱዋ (Victor Adua) ናይጄሪያዊ ወጣት ነው። በቴክኖሎጂ እና ማርኬቲንግ ዘርፍ ወጣቶች እንዴት በዲጂታል ክህሎት ራሳቸውን መለወጥ እንደሚችሉ ያስተምራል። በተለይም በጊግ ኢኮኖሚ (Gig Economy) ላይ ያለው ልዩ ትኩረት ለኢትዮጵያ ዲጂታል ስትራቴጂ ጠቃሚ ትምህርት ይሰጣል።
ማጊ ሙኩታ (Maggie Mukuta) የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ተወላጅ ነች። በአፍሪካ የጨርቃ ጨርቅ ውጤቶች እና በሴቶች የንግድ ተሳትፎ ላይ በማተኮር የአህጉሪቱን የፋሽን ኢንዱስትሪ ለዓለም ታስተዋውቃለች።
ወጣቶች ወደ ግብርና እንዲመለሱ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ እርሻ እንዲያካሂዱ የሚያነሳሱ ይዘቶችን የሚያቀርበው አፍሪካዊ ወጣት ደግሞ ኡጋንዳዊው ስቲቭ ካንባ (Steve Kamba) ነው።
እንደ ሄኒ የሻነው (Henny Yeshanew) እና ሸገር ዲጂታል (Sheger Digital) ያሉ የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎችም በኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለማሳደግ እና የሥራ ፈጠራን ለማስፋት በሚደረገው ጥረት የራሳቸው አበርክቶ ይኖራቸዋል።
እነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች ከመደበኛው ሚዲያ በበለጠ ወደ ወጣቱ የመድረስ አቅም አላቸው። እነዚህ ዲጂታል አምባሳደሮች ከማዝናናት ባለፈ የአፍሪካን እና የኢትዮጵያን ታሪክ በአዲስ መልክ የመጻፍ (Narrative Transformation) ኃይል አላቸው።
በንፍታሌም እንግዳወርቅ
Ethiopian Broadcasting Corporation #africa #ethiopia #contentcreators #asmis2026 #narrativetransformation #ebc

5 months ago
ኢትዮጵያ የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤን (ASMIS) ልታስተናግድ ነው!
#ethiopia | ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደውን የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (Africa Social Media Influencers Summit - ASMIS) በአዲስ አበባ እንደምታስተናግድ ተበሰረ።
ዛሬ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ (POA) እና ኤ.ጂ.ኤ ቴክ (AGA-Tech) በጋራ በሰጡት መግለጫ የጉባኤውን ዝርዝር ይፋ አድርገዋል።
የጉባኤው መርሃ-ግብር
ቀን፦ ግንቦት 7 እና 8 ቀን 2026 (እ.አ.አ)
ቦታ፦ አዲስ አበባ፣ የዓድዋ ድል መታሰቢያ
መሪ ቃል፦ ''ተፅዕኖ ለተሻለች አፍሪካ''
የጉባኤው ዋና ዋና ዓላማዎች
የጋራ መድረክ መፍጠር፦ የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ድምፆችን ከመገናኛ ብዙኅን፣ ከፖሊሲ አውጪዎችና ከንግድ መሪዎች ጋር ማገናኘት።
ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና ቴክኖሎጂ፦ በፈጣን ዕድገት ላይ ባለው AI እና በዲጂታል ይዘት ፈጠራ ዙሪያ ልምድ መለዋወጥ።
የአፍሪካን ታሪክ መግለጥ፦ ስለ አህጉሪቱ መፃኢ ተስፋና ታሪክ ጥራት ያላቸው የይዘት ሥራዎችን ለማስተጋባት አቅም መፍጠር።
ቢዝነስ እና ትስስር፦ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን ከታላላቅ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ የንግድ ድርጅቶች ጋር ማገናኘት።
በአህጉሪቱና በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ከ200 በላይ ታዋቂ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በጉባኤው ላይ ይታደማሉ።
እንዴት መሳተፍ ትችላላችሁ
የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ባዩሽ ማሞ እንደገለጹት፣ የጉባኤው ይፋዊ ምዝገባ በቅርቡ ይጀመራል። የይዘት ፈጣሪዎችና ፍላጎቱ ያላቸው አካላት የሚከተለውን ድረ-ገጽ በመከታተል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፦
🔗 www.asmis.org
ይህ ጉባኤ አዲስ አበባን የአፍሪካ የዲጂታል ዲፕሎማሲ ማዕከል ከማድረጉም በላይ፣ የአህጉሪቱን የፈጠራ አቅም ለዓለም ለማሳየት ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።
#asmis2026 #socialmediainfluencers #africadigital #addisababa #adwamemorial #ethiopia #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

Comments