የአፍሪካን ገጽታ እየገነቡ ያሉት የዲጂታል አምባሳደሮች
****************
የአፍሪካን ትክክለኛ ገጽታ ለዓለም የማሳየቱ ታሪካዊ ኃላፊነት ከመደበኛው የሚዲያ ተቋማት ወደ ዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎችና ማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በስፋት እየተሸጋገረ ይገኛል።
በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው የመጀመሪያው የአፍሪካ የማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS 2026) እንደሚያሳየው፣ እነዚህ ግለሰቦች ከዝና ባለፈ ለሀገራዊ ገጽታ ግንባታ እና ለኢኮኖሚ እድገት ቁልፍ ሚና እየተጫወቱ ነው።
በጉባኤው ተሞክሯቸውን ካካፈሉት መካከል አቤል ብርሃኑ በአፍሪካ 3ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ የጉዞ ቪሎገር ሲሆን፣ በቅርቡ በናይሮቢ የዓመቱ ምርጥ የአፍሪካ የጉዞ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተብሎ ተሸልሟል።
አቤል በአማርኛ የሚያቀርባቸው ይዘቶች የሀገር ውስጥ ባህልን ከዓለም አቀፋዊ እውነታ ጋር በማገናኘት ረገድ ትልቅ አቅም አላቸው።
ታዋቂው ጋናዊ ዎዴ ማያ አፍሪካን በተስፋ መነጽር ለዓለም በማሳየት የሚታወቅ ሲሆን፣ አዲስ አበባን ለሥራው መነሻ በማድረግ የኢትዮጵያን የልማት እንቅስቃሴዎችና የኢንቨስትመንት አማራጮች በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ተመልካቾች አሳይቷል።
ናይጄሪያዊው ቪክቶር አዱዋ በቴክኖሎጂና በጊግ ኢኮኖሚ ላይ ትኩረት በማድረግ ወጣቶች በዲጂታል ክህሎት ራሳቸውን እንዲለውጡ የሚያስተምር ሲሆን፣ ኮንጎአዊቷ ማጊ ሙኩታ ደግሞ የአህጉሪቱን ፋሽን ለዓለም ታስተዋውቃለች።
ዩጋንዳዊው ስቲቭ ካንባ ወጣቶች ወደ ዘመናዊ ግብርና እንዲመለሱ የሚያነሳሱ ይዘቶችን ያቀርባል።
በሀገራችንም እንደ ሄኒ የሻነውና ሸገር ዲጂታል ያሉ ፈጣሪዎች በሥራ ፈጠራና በቴክኖሎጂ ላይ ያላቸው ተሳትፎ ከፍተኛ ነው።
እነዚህ እና ሌሎችም ዲጂታል አምባሳደሮች ከመደበኛው ሚዲያ በበለጠ ወደ ወጣቱ የመድረስ አቅም ያላቸው ሲሆን፣ የአፍሪካንና የኢትዮጵያን ታሪክ በአዲስ ዕይታና ወጥ በሆነ መንገድ ለዓለም ለማስተዋወቅ ቁልፍ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ።
በንፍታሌም እንግዳወርቅ
#ethiopia #africa #asmis2026 #digitalambassadors #contentcreators #ethiopianbroadcastingcorporation

3 months ago