1 month ago
ኢትዮጵያ በኮንፈረንስ ቱሪዝም ዘርፍ ሌላ ታላቅ ምዕራፍ ተሻግራለች። አርባምንጭ ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚወዳደር አዲስ ገጽታን ተላብሳለች።
#ethiopia #ebc #pmabiyahmed #arbaminch
1 month ago
u1218u123bu120d u1260u1270u130du1263u122d u1290u12cd
https://youtu.be/_63EgdJOB...
#ethiopia #arbaminch #pmabiyahmed ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"ExternalUrl","__isEntity":"ExternalUrl","url":"https://l.facebook.com/l.p...
መሻል በተግባር ነው
https://youtu.be/_63EgdJOB...
#ethiopia #arbaminch #pmabiyahmed
1 month ago
1 month ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሐይቅ ላይ የተገነባ ልዩ ተንሳፋፊ ሬስቶራንት ያለው የአርባምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት ጎብኚዎች እንዲጎበኙት ጥሪ አቀረቡ
************************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመዲናችን ባሻገር የኮንፈረንስ ቱሪዝምን በማስፋፋት ኢትዮጵያን የዓለም አቀፍ መድረኮች ማዕከል የማድረግ ርዕይን የሚያጠናክረውን ዘመናዊውን "የአርባምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት" መርቀዋል።
የ‘ገበታ ለትውልድ’ መርሃ-ግብር ታላቅ ስኬት የሆነው ይህ ሪዞርት፣ ከ1 ሺህ 300 በላይ ሰዎችን የሚያስተናግድ ሰፊ የስብሰባ አዳራሽ እና በሐይቅ ላይ የተገነባ ልዩ ተንሳፋፊ ሬስቶራንትን በውስጡ ያካተተ ነው።
ፕሮጀክቱ ሀገራዊ የኮንፈረንስ ቱሪዝም አቅምን ከማሳደጉም ባሻገር ለአካባቢው ማኅበረሰብ ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ መላው የሀገራችን ሕዝብ፣ የዳያስፖራው አባላት እና የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ይህንን አዲስ የሀገራችንን ዕንቁ ስፍራ በመጎብኘትና በመጠቀም የተከፈተውን አዲስ የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ምዕራፍ በጋራ እንዲቋደሱ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
#ethiopia #arbaminch #pmabiyahmed #tourismethiopia #visitethiopia #conferenceresort

Sponsored by
Surafel
1 month ago
በሐይቅ ላይ የተገነባው የሚሽከረከር ሬስቶራንትና ግዙፉ የአርባ ምንጭ ፕሮጀክት በቅርቡ ይመረቃል
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#ethiopia | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በይፋ ስለሚመረቀው ግዙፍና ማራኪ የአርባ ምንጭ የቱሪዝም ፕሮጀክት አስደናቂ ገጽታዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በተለይም የስብሰባ፣ ኮንፈረንስና ኤግዚቢሽን (MICE) ቱሪዝምን ታሳቢ አድርጎ የተገነባ መሆኑን ገልጸው፣ በውስጡም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል እጅግ ግዙፍ አዳራሽ ማካተቱን አስታውቀዋል።
የፕሮጀክቱ አስገራሚ ገጽታ በሐይቁ ውኃ ውስጥ ገብቶ ወደ ላይ በመውጣት የሚሽከረከር ዘመናዊ ሬስቶራንት በመሆኑ ነው ብለዋል።
ይህ የሚሽከረከር ሬስቶራንት በአዲስ አበባ ከሚገኘው የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሠራ ልዩ የሥነ-ሕንፃ ጥበብ ስለመሆኑም አንስተዋል።
ፕሮጀክቱ ከአርባ ምንጭ ኤርፖርት ከአምስት እስከ ስድስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ብቻ የሚገኝና እጅግ ማራኪ በሆነ የመሬት ገጽታ አሠራር ያሸበረቀ በመሆኑ፣ ለማንኛውም ኮንፈረንስና እረፍት ተመራጭ መዳረሻ ያደርገዋል ነው ያሉት።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳብራሩት፣ ጎብኚዎች ወደ አካባቢው ሲያቀኑ በጨንቻ የፖም (አፕል) ምርትን፣ የጫሞን አሳ፣ እንዲሁም ሁለቱን ታላላቅ ሐይቆች ማለትም አባያ እና ጫሞን የሚያገናኘውን ማራኪውን የ"እግዜር ድልድይ" መመልከት ይችላሉ።
ፕሮጀክቱ የተሰራበት አካባቢ ከዚህ በተጨማሪም በነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ የሚገኙትን የሰዋይኔስ ቆርኬ፣ የሜዳ አህዮች፣ ልዩ ልዩ የአዕዋፋት ዝርያዎች እንዲሁም በማዜ ብሔራዊ ፓርክ የቢልቦ ፍልውኃን፣ የጎሽ መንጋን እና ብርቅዬውን ባለጥቁር ጋማ አንበሳ በቅርበት ማየት የሚያስችል አስደናቂ የተፈጥሮ ጸጋ የታደለ አካባቢ መሆኑን ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በይፋ የሚመረቀው ይህ ታላቅ የአርባ ምንጭ ፕሮጀክት መንግሥት ከዚህ ቀደም ከሠራቸው ሥራዎች የተማረባቸውንና ያሻሻላቸውን ጥበባዊ ልምዶች በሙሉ ያካተተበት መሆኑን ጠቁመው፣ አዲሱ ፕሮጀክት እጅግ በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስቶችን የሚስብ ግንባር ቀደም መዳረሻ እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #arbaminch #visitethiopia #pmabiyahmed #micetourism #ethiopianbroadcastingcorporation

ውበቷን ገልጦ ስሟን እና ታሪኳን ያስተሳሰረ የአርባምንጭ ከተማ ኮሪደር ልማት
************************************
በኢትዮጵያ ለቱሪስት መስብነት የታደለችውና የተትረፈረፈ የተፈጥሮ ፀጋ ባለቤት የሆነችው አርባምንጭ ከተማ፣ በሀይቆች፣ በተራሮች፣ በዛፎች እና ደሴቶች ተከባ አረንጓዴ የተላበሰች የተቀናጀ ልማትን ዘርግታለች።
ስሟን እና ታሪኳን አስተሳስሮ በተሠራው በኮሪደር ልማትም ይበልጥ ሳቢና ማራኪ የቱሪስት መዳረሻ ሆናለች።
በከተማዋ በ12 ምድብ ተከፋፍሎ የተሠራው የኮሪደር ልማት ሥራ የሕዝብ መዝናኛ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ፣ የገበያ ማዕከላት፣ የህፃናት መጫዋቻ ቦታ፣ የመኪና ማቆሚያዎች እንዲሁም ታሪኳንና ስሟን የሚወክሉ 40/42 እና 63/8 የሚባሉ የደረጃ ፕሮጀክቶችንም አካትቷል።
40/42 የሚለው ስያሜ የተሰጠውም ቱሪስቶችን ወደ አርባዎቹ ምንጮች እና አርባምንጭ ደን የሚወስደው ደረጃ የአርባምንጭ አርባ ምንጮች መገለጫ ሲሆን፣ 42 ደግሞ አርባ ሁለቱን የጋሞ “ደሬዎች” ማለትም ጎሳዎችን የሚወክሉ ናችው።
63/8 ተብሎ የተሰየመው ሌላኛው ፕሮጀክት ደግሞ በ1955 ዓ.ም የተቆረቆረች አርባምንጭ ዛሬ 63 ዓመት መሆኑንና እና 8 ደግሞ ለረጅም ጊዜ የነበረውን የልማት ጥማት ከለውጡ ማግሥት ጀምሮ በርካታ ልማት የተሠራበት በመሆኑ 8 የልማት ዓመታትን ለመግለጽ ታስቦ ነው።
የከተማ ኮሪደር ልማት በተለይ የመንገድ መሠረት ልማት በየአቅጣጫው አንዱ ከአንዱ ጋር የተሳሰረ ሲሆን፣ የአንዱ ሎት (ምድብ) መነሻ ለሌላይኛው ደግሞ መድረሻ ይሆናል።
በዚህም አርባምንጭ ዙሪያዋን የከበቡ ሀይቆች፣ ተራሮች እና አረንጓዴን ለማየት አመቺ ሆኖ እየተሠራ ይገኛል።
ከ50 በላይ የሕዝብ መዝናኛዎች ያለው የአርባምንጭ ኮሪደር ልማት በርካታ የስፖርት ማዘውተሪያ፣ የአካል ጉዳተኞችና እግረኞች ምቹ መንገድ፣ የፐብሊክ ፕላዛዎች እና አንፊ ቴአትር ጨምሮ የተለያዩ የሕዝብ መገልገያዎች ያካተተ ነው።
ከተማዋን በሙሉ በማካለል እየተሠራ የሚገኘው ከ20 ኪሎ ሜትር በላይ የሚረዝመው የኮሪደር ልማት ሥራ አርባምንጭን ይበልጥ የዘመነች እና የቱሪዝም ከተማ አድርጓታል።
በትዕግስቱ ቡቼ
#ethiopia #ebc #corriderdevelopment #urbandevelopment #arbaminch

5 months ago
አሳዛኝ_ዜና!
በጋሞ ዞን በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሶስት የአንድ ቤተሰብ አባላት ሕይወት አለፈ!
በጋሞ ዞን ቦንኬ ወረዳ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሶስት የአንድ ቤተሰብ አባላት (እናት እና ሁለት ልጆች) ሕይወታቸውን በአሳዛኝ ሁኔታ አጥተዋል!
በአባወራው አካል ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት በአሁኑ ጊዜ በቦንኬ ጋዜሶ ጤና ጣቢያ የመጀመሪያ ደረጃ የሕክምና እርዳታ እየተደረገለት ሲገኝ በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።
Gamo ArbaMinch

#የጥንቃቄ_መልዕክት !
ትናንት ሰኞ እኩለ ሌሊት ጀምሮ እስከ ዛሬ ማክሰኞ ጧት 3:00 ሰዓት በጣለ ከባድ ዝናብ ምክንያት የሐሊላ ወንዝ ሞልቶ በጋሞ ዞን ካምባ ወረዳ ባልታ ከተማና ህዝብ ንብሬት ላይ ጉዳትና የጎርፍ መጥለቅለቅ አስከትሏል!
Via: Gamo Arbaminch

12 months ago
ኢትዮጵያ በቀኝ በግራ እየተሰራች ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#ethiopia | ኢትዮጵያ በቀኝ በግራ እየተሰራች የማንሰራራት ዘመኗ የሚታይ የሚጨበጥ ሆኗል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄዱ ያሉ የልማት ሥራዎችን እና የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝቱ ወቅት፤ ኢትዮጵያ እየተሰራችና እያንሰራራች ያለችበትን ሂደት ያልተገለጠላቸው አካላት በሂደት ይገለጥላቸዋል ብለዋል፡፡
አርባ ምንጭ ንፁህ እና ነዋሪዎቿም ከተማዋን ጠብቀው የሚኖሩባት ከተማ ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህም ትልቅ ተስፋ እንዲኖርን አድርጎናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
ያማረ ተራራ፣ ያማረ ጫካ እና ውሀ ተሰናስሎ የሚታይበትን ይህን ስፍራ፤ ማስተካከል እና ማስዋብ ከተቻል አርባምንጭ ካሉን ምርጥ ቦታዎች አንዱ ሊሆን ይችላል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
አርባ ምንጭ፣ ጅማ፣ ባህርዳር፣ ድሬድዋ ላይ የሚታየው ነገር ከአዲስ አበባ ውጭ አማራጭ ቦታዎች እየሰፉ እንደሚገኝ ያመላክታል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
በሀገራችን ያሉንን ቦታዎች ማልማት ከቻልን የትም ቦታ ሄደን ምርጥ ነገር መመልከት እንችላለን ሲሉም አክለዋል፡፡
በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሚታዩት ነገሮች የራሳቸው ውበት አላቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህን በማልማት ለልጆቻችን ማረፊያ፣ መዋያ፣ ገንዘብ ማምጫ፣ ማሰቢያና ማሰላሰያ ስፍራን መፍጠር እንችላልን ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በሐይማኖት ከበደ
#ebc #pmoethiopia #pmabiy #arbaminch

Comments