Logo
YenetaTube
አትሌቷ እገዳ ተጣለባት

ኬንያዊቷ ናንሲ ጄላጋት ሜቶ የተከለከለ አቅምን የሚያጎለብት ንጥረ ነገር ተጠቅማ በመገኘቷ ለሁለት ዓመታት ታገደች።

ሰኔ 5 ቀን 2016 ዓ.ም. ናንሲ ጄላጋት ሜቶ በኬንያ ውስጥ ከውድድር ውጭ በተደረገላት የልምምድ ወቅት ምርመራ 'ፉሮሴማይድ' የተባለ የተከለከለ አቅምን የሚያጎለብት ንጥረ ነገር ተገኝቶባታል።

በወቅቱ ዕድሜዋ 38 ዓመት የነበረ ሲሆን፤ እንደ ሌሎች ኤሊት አትሌቶች ሁሉ እሷም በአለም አቀፍ የክትትል ዝርዝር ውስጥ ትገኝ ነበር።
ከሦስት ዓመታት ገደማ በኋላ የአትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት (AIU) ትናንት በሰጠው መግለጫ የምርመራ ዝርዝር ሂደትን ካብራራ በኋላ ጥፋተኛ ሆና በመገኘቷ የሁለት ዓመት የዕገዳ ቅጣት ሊጥልባት ችሏል።

ምርመራው ከተደረገ ከስድስት ሳምንታት በኋላ ጁን 22 የኬንያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ የአትሌቷ ናሙና ተልኮበት ከነበረው በሉዛን ከሚገኘው የዓለም የፀረ-አበረታች ቅመሞች ላቦራቶሪ ውጤቱን ካገኘ በኋላ፤ አትሌቷ የተከለከለ ንጥረ ነገር እንደተገኘባት አሳወቃት።

በመቀጠልም ኃላፊነቱ ወደ አትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት (AIU) የተዛወረ ሲሆን፤ ተቋሙም ኦገስት 21 የተገኘውን የላቦራቶሪ ውጤት ለሜቶ አሳወቃት። እሷም ውጤቱን ያስተባበለች ሲሆን፤ በደል እንደተፈጸመባትም ተከራክራለች።

በሴፕቴምበር ወር መጨረሻ ላይ ሜቶ "የመጀመሪያው ማሳወቂያ አልደረሰኝም በማለቷ (ምንም እንኳን ማሳወቂያው የተላከው እሷ ራሷ መልዕክት እየላከችበት ባለው የኢሜይል አድራሻ ቢሆንም)፤ AIU ጉዳዩን መልሶ ለኬንያው ADAK መርቶታል። የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በጉዳዩ ውስጥ ጣልቃ በመግባቱ ይፋዊ መግለጫው እንዲዘገይ አድርጓል።

እንደ ጋዜጣዊ መግለጫው ከሆነ AIU ለአትሌቷ የቢ (B) ናሙና ምርመራ እንዲደረግላት የመጠየቅና የተገኘውን የላቦራቶሪ ውጤት የሚያረጋግጡ የሰነድ ጥቅሎችን የማግኘት ተጨማሪ ዕድል ሰጥቷታል።

በተጨማሪም አትሌቷ በጉዳዩ ላይ እንዴት መቀጠል እንደምትፈልግ እንድታረጋግጥ፤ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ደንብ ጥሰቱንና የቀረበባትን ቅጣት እንድትቀበል፤ ወይም በስፖርት የግልግል ዳኝነት ችሎት ፊት ቀርባ እንድትከራከር ዕድል ተሰጥቷት ነበር።

ማርች 13 ቀን 2026 AIU በአትሌቷ የተፈረመ የደንብ ጥሰቱን አምኖ የመቀበልና ቅጣቱን የመቀበያ ቅጽ ደርሶታል። በዚህም መሰረት የእርሷ እገዳ ከጁላይ 11 ቀን 2024 ጀምሮ ለሁለት ዓመታት የሚቆይ ይሆናል።

አሁን ዕድሜዋ 40 ዓመት የደረሰው ይህች አትሌት በመጪው ክረምት ወደ ውድድር ልትመለስ ትችላለች።

ናንሲ ጄላጋት ሜቶ የ2021 የቫሌንሲያ ማራቶን አሸናፊ እንደነበረች የሚታወስ ነው። በወቅቱ የገባችበት 2:19.31 በርቀቱ የግል ምርጥ ሰዓቷ ሆኖ ተመዝግቦላታል።

ምስጋናው ታደሰ

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.