አትሌት ድርቤ ወልተጂ ከውድድሩ ውጪ ሆነች
ኢትዮጵያን በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር በ 1500ሜ ለመወከል ተመርጣ የነበረችው አትሌት ድርቤ ወልተጂ ከውድድሩ ውጪ መሆኗ ተገልጿል።
አትትሌቷ ከውድድሩ ውጪ የሆነችው ሊደረግላት የነበረውን የአበረታች ንጥረነገር ምርመራ ለማድረግ ፈቃደኛ ባለመሆኗ መሆኑ ተነግሯል።
አትሌቶች አበረታች ዕፅ መጠቀም አለመጠቀማቸውን የሚቆጣጠረው "The Athletics Integrity Unit (AIU)" የዶፒንግ ምርመራ እንድትሰጥ ቢጠይቃትም ፈቃደኛ አለመሆኗ ተገልጿል።
ይህንንም ተከትሎ " AIU " አትሌቷ ከቶኪዮው የዓለም ሻምፒዮና ውጪ እንድትሆን ለዓለም አቀፉ የስፖርት ጉዳዮች ግልግል ችሎት (Court of Arbitration for Sport (CAS) ክስ አቅርቧል።
የክሱ ውሳኔው በዓለም አቀፉ የስፖርት ጉዳዮች ግልግል ችሎት የታወቀ ሲሆን አትሌት ድርቤ ወልተጂ ከውድድሩ ውጪ መሆኗ ታውቋል።
በርቀቱ ሁለተኛ ምርጥ ሰዓት ባለቤት የሆነችው አትሌቷ ለኢትዮጵያ ሜዳልያ ያስገኛሉ ተብለው ከሚጠበቁ አትሌቶች አንዷ ነበረች።
ምንጭ :- ጋዜጠኛ ብሩክ ተስፋዬ

9 months ago