1 day ago
"የህዝብ፣ በህዝብ፣ ለህዝብ የሆነ አስተዳደር ከምድረ ገጽ አይጠፋም!"— አብርሃም ሊንከን
#ethiopia |ይህ 16ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አብርሃም ሊንከን በፔንስልቬንያ በተደረገው የጌቲስበርግ ብሔራዊ መቃብር ምርቃት ወቅት ያደረጉትና የዓለምን የዲሞክራሲ ስርአት የለወጠ ታሪካዊ ንግግር ነበር።
በወቅቱ አሜሪካ በደም አፋሳሹ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ በነበረችበት ወቅት የተደረገው ይህ ንግግር እስከዛሬ ድረስ በዓለም ታሪክ ውስጥ እጅግ ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ንግግሮች አንዱ ተብሎ ይጥቀሳል።
ንግግሩ እጅግ አጭርና 272 ቃላት ብቻ የነበሩት ሲሆን ለማንበብ ከ2 እስከ 3 ደቂቃ ብቻ ነበር የፈጀው።
ከሊንከን በፊት ተናጋሪ የነበሩት ኤድዋርድ ኤቨሬት ለ2 ሰዓታት ያህል ረጅም ንግግር አድርገው የነበረ ቢሆንም ታሪክ ግን የሊንከንን አጭር ንግግር ዘክሮታል።
ሊንከን ዲሞክራሲን "የህዝብ፣ በህዝብ፣ ለህዝብ" በማለት ያቀረቡት ብያኔ እስከዛሬ ድረስ የመንግስታትና የዲሞክራሲ ዋነኛ መለኪያ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።
ንግግሩ በጦርነቱ የወደቁትን ወታደሮች ከማሰብ ባሻገር አሜሪካ አንድነቷ ተከብሮ የሰው ልጅ ሁሉ በነጻነትና በእኩልነት የሚኖርበት ሀገር እንድትሆን አዲስ ተስፋ የሰጠ ነበር።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopiaabrahamlincoln #democracy #government #gettysburgaddress #abrahamlincoln

2 months ago
"ለሌሎች ነፃነት የሚነፍጉ ሰዎች ለራሳቸውም ነፃነት አይገባቸውም!"- አብርሀም ሊንከን
#ethiopia | በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጣቸውና 16ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት አብርሃም ሊንከን ለነጻነትና ለሰብአዊ መብት መከበር የነበራቸው ቁርጠኝነት ዛሬም ድረስ በአለም አቀፍ ደረጃ በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳል።
ፕሬዚዳንት አብርሃም ሊንከን ሀገራቸውን በአስቸጋሪው የአሜሪካ የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት በብቃት በመምራት እና የባርነት ስርዓትን በመደምሰስ ረገድ የመሪነቱን ሚና ተጫውተዋል።
"ለሌሎች ነጻነትን የሚከለክሉ ሰዎች ለራሳቸውም ነጻነት አይገባቸውም" በማለት የተናገሩት ንግግር የነጻነት የእኩልነትና የፍትህ መሰረታዊ መርህ ሆኖ እስከ ዛሬ ድረስ ይገኛል።
የአብርሃም ሊንከን ንግግሮችና ጠንካራ አመራር ለአሜሪካውያን ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም ለሚገኙ የፍትህና የነጻነት ታጋዮች ትልቅ ብርታት ሲሰጡ ኖረዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #abrahamlincoln #americanicons #freedom #americanhistory #leadership

"ምንም ሁን... መልካም ሁን"
"ከጭቃ ጎጆ እስከ ነጩ ቤተመንግስት
#ethiopia | በዓለም ታሪክ ውስጥ የብዙ ታላላቅ መሪዎች ሥራ ፈጣሪዎችና ስኬታማ ሰዎች የሕይወት መሪ የሆነች አንዲት ድንቅ አባባል አለች።
በአሜሪካ አስቸጋሪ ጊዜያት አገራቸውን ከውድቀት የታደጉትና የባርነትን ሥርዓት የሻሩት የቀድሞው ፕሬዚዳንት አብርሃም ሊንከን የተናገሯት ይህች አባባል ናት።
ይህ አባባል በውስን ቃላት ብቻ የተቋጠረ ቢሆንም በውስጡ ግን የዕድሜ ልክ ጥበብን አቅፎ ይዟል።
"ምንም ሁን... መልካም ሁን" የሚል
ብዙዎቻችን በሕይወታችን ውስጥ ትልቅ ቦታ ወይም ስልጣን ካላገኘን ስኬታማ እንደማንሆን አድርገን እናስባለን።
የአብርሃም ሊንከን መልእክት ግን ይህንን አስተሳሰብ ሙሉ በሙሉ ይሰብራል።
ሊንከን እንደሚነግረን የስኬት ምስጢሩ በያዝነው ቦታ ወይም ማዕረግ ላይ ሳይሆን ባለንበት ቦታ ላይ በምንሰጠው የጥራት ደረጃ እና ቁርጠኝነት ላይ ነው።
ሊንከን ራሱ የተወለደው በኬንታኪ ከሚገኝ የጭቃ ጎጆ ውስጥ ሲሆን መደበኛ ትምህርት እንኳን ሳይማር በራሱ ጥረት በማንበብ ለታላቅነት የበቃ ሰው ነው።
እሱ ያመነው በማንኛውም ሥራ ውስጥ የተሰማራ ሰው ነጋዴ፣ ተማሪ፣ ሹፌር፣ መምህር፣ ጽዳት ወይም የሀገር መሪ የተሰጠውን ኃላፊነት በጥራት እና በታማኝነት ከተወጣ የዓለምን ትኩረት መሳቡ አይቀሬ መሆኑን ሊንከን ያምናል።
የሚያበራው የወርቅ ማዕረግ ሳይሆን የምታሳየው የላቀ ብቃት ነው።
የተቀበልከውን ትንሽ ሀላፊነት በልዩ ብቃት ስታከናውን ታላላቅ በሮች ይከፈቱልሃል ይላል።
ከሰዎች ሙገሳና ምስጋና ይልቅ ለራስህ መርህና ለእውነት ታማኝ መሆን የዘላቂ ስኬት መሠረት ነው።
ሊንከን በንግድ ከስሯል በምርጫ ተሸንፏል ነገር ግን በሄደበት መንገድ ሁሉ ምርጡን ለመስጠት በመጣሩ ውድቀቶቹ ለታላቅ ፕሬዚዳንትነት ማዕረግ አበቁት።
ዛሬ ላይ ቆመህ ህይወቴ ወዴት እየሄደ ነው ብለህ የምትጠይቅ ከሆነ መልሱ በእጅህ ላይ ይገኛል።
የምታደርገውን እያንዳንዷን ትንሽ ነገር በጥራት በፍቅር እና በታማኝነት አከናውናት።
ምክንያቱም ታሪክ የሚያስታውሳቸው ያገኟቸውን አጋጣሚዎች ሁሉ ምርጥ እና ድንቅ አድርገው የተጠቀሙበት ሰዎች ብቻ ነውና።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #usa #president #lifestyle #abrahamlincoln #politics #goldensaying #history

Sponsored by
Surafel
Comments